ለሁሉም የአማራ የማህበረሰብ አንቂዎችና የF.B ተጠቃሚዎች‼(ህዝበ ሒሚሪያት)


እንምታውቁት አማራ ከወልቃይት፣ ከራያና ከመተከል እንዲሁም በቅርቡ ከደራ የማንነት ጥያቄዎች ይመለሱልኝ ጋር በተያያዘ ብዙ ነገሮች ተከናውነዋል።
በተለይ ከሐምሌ 5ቱ የተጋድሎ ቀን ጀምሮ በጎንደር፣በጎጃም በወሎና በሸዋ በርካታ ወንድሞቻችን በጥይት ተደብድበው ሞተዋል። ልብ አርጉ ይህ ግድያ ህገመንግስታዊ መብቱን ለጠየቀው የአማራ ህዝብ የተሰጠ ህገመንግስታዊ መልስ መሆኑ ነው።


ይባስ ብሎ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በምድረገኝ/ኬሚሴ፣አጣዬና ማጀቴ፤ በራያ በኩል በአላማጣ፣ ቆቦ፣ ዋጃ፤ በመተከል በጃዊ እና ማንዱራ … እንዲሁም በደራና በወልቃይት ያለውን ትኩሳት እና የተዳፈነ እሳት እስከመጨረሻው የሚያጠፍው አካል ባለመኖሩ በየወቅቱ እያገረሸ የወንድሞቻችንን ህይወት ነጥቋል፤ነገም ይነጥቃል።


በነዚህ ቦታዎች ችግሮች ሲፈጠሩ የመላው ኢትዮጵያ ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶች እና ፓለተከኞች ምን አይነት አስተሳሰብ ነበራቸው ብሎ መገምገሙና ማስተዋሉ እጅግ ጠቃሚ ይመስለኛል። ማናቸውም ስለአማራ መበደል፣መሞት እና መፈናቀል እንዲሁም መዘረፍ ትንፍሽ አላሉም። መንግስትም ቢሆን ከዚህ የተለዬ አቋም እንደሌለው መገንዘብ ይቻላል። ሌሎቹ እንደዚህ ካሰቡና ካደረጉ እኛስ ምን ስናደርግ ነበር? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ደግሞ እጅግ ጠቃሚና ካለፈው ተምረን ለነገው እናስተካክላለን ብዬ አስባለሁ።


እስከአሁን የመጣንበት መንገድና የአክቲቪዝሙ ስህተቶች በእኔ አረዳድ የሚከተሉት ናቸው።
1ኛ. የግንባረ ሰው አለመኖር /lack of Activist members- ማለት አንድ አይነት አስተሳሰብ እና መረጃ (የተቀራረበ ) ሊሰጥ እና ሊመራ የሚችል እኛም ልንከተለው የምንችለው Puplic figure የሆነ አካል/ቡድን መጥፍት ይህ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የመረጃ መደበላለቅ እና ያለመናበብ ችግሮችን አስከትሏል። በዚህም የተነሳ ታማኝ ያልሆኑና አቅጣጫ የሚያስቱ መረጃዎች በመሃል እንዲገቡና ልፍታችን መና እንዲቀር አድረገዋል።
2ኛ. Unprofessional Activism – ከክልሉና ከፌደራል የመንግስት ተቋማትና አመራሮች ጋር ጫፍ የወጣ መካርር ውስጥ መግባት፤ አለፍ ሲልም መዝለፍ፣ ማንቋሸሽ እና ሃይለቃላትን እየተጠቀሙ የአማራው ጠላት አድርጎ መመልከትና መሳል። ይህ ደግሞ እንዳየነውና እንደተመለከትነው በችግር ላይ ችግር ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አላየንም‼
ለምሳሌ:- መከላከያን፤የሚዲያ ተቋማትን እና አመራሮችን…
3ኛ. Prejudice against other people – ስለ አማራ ሀገር ሰሪነት፣ መሪነትና መንግስት መስራችነት እንዲሁም አስተዳደር አዋቂነት እየሰበኩ ሌሎች ህዝቦችን አማራው እንዲጠላቸውና ጠላቱ እንደሆኑ በሰፊው መስራት አክሳሪ አካሄድ መሆኑን መረዳት ለነገ የማይባል ጉዳይ መሆን አለበት ብዬ አስባለሁ።
4ኛ. Failure to hid information – ልብ ብላችሁ ተመልክታችሁ ከሆነ የአማራ አክቲቪዝም የሚደበቅ ሚስጥር የለም። ሁሉም ነገር እውነት ይሁን ውሸት ጠቃሚ ይሁን ጎጂ እንደጉድ ሳይበሩ ላይ ይዥጎደጎዳል። ይህ የቤት ሚስጥር አደባባይ የማውጣት ጉዳይ ሊካካስ የማይችል እና ለወሬ የማይመች መስዋዕትነት አስከፍሎናል።
4ኛ. Lack of lasting unity/ጎጠኝነተ- ወጥ የሆነ አማራዊ አንድነት አለመኖር … ይህንን ችግር ሳስበው ስለሚያመኝ ብዙም አላብራራውም።
5ኛ. Self-promotion የተወሰኑ አካላት የዚህ አመለካከት ተጠቂዎች ናቸው። ልጥቀስ እንዴ?😄
እና ሌሎችን ከመፍትሔዎቻቸው ጋር እመለስበታለሁ።

Advertisements

የዐቢይ፣ ኦነግ እና ሜጫና ቱለማ ትብብር፦ (ጌታቸው ሺፈራው)

አንድን ተቀናቃኝ ኃይል ለማዳከም ጠንካራና ደካማ ጎኑን መለየት የመጀመርያው ስራ ነው። ባላንጣው መሰረቱን ለመናድ ያስችላል ያለውን ጠንካራ ጎን ለመጉዳት ይጥራል። ሰሞኑን በአማራው ላይ እየተፈፀሙ ካሉት ጉዳዮች መካከል አንዳንዶቹን ብናይ ይህን የባላንጣዎች ተግባር እናገኘዋለን።

የኦነግ መሰረት የሆነው ሜጫና ቱለማ የሚባል ድርጅት ነው። ይህ ድርጅት ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ ተስፋፊዎች ቤተ አማራ/ወሎ ድረስ የሚለጥጡትን ካርታ በባነር ሰቅሎ አሳይቷል። ከሳምንት በፊት የሜጫና ቱለማ ውላጅ የሆነው ኦነግ የተባለ የፅንፈኞች ድርጅት “ወሎ የኦሮሞ ግዛት ነው” ብሎ መግለጫ ሰጥቷል። ሁለቱም የለየላቸው ፅንፈኛ ተቋማት ናቸው። የጥላቻ ተቋማት ናቸው። ሁለቱ ድርጅቶች ግን የተወጡት የተለያዩ ሚና ነው። ኦነግ በመግለጫው ቃል በቃል ቤተ አማራ/ወሎን የኦሮሞ ግዛት ነው አለ። የኦነግ መመልመያና መፍለቂያው ሜጫና ቱለማ ደግሞ ካርታውን አሳይቶ ከኦነግ አነስ ያለ የመሰለ የፅንፈኝነት ሚናውን ተወጥቷል።

የኦሮሞ ፅንፈኛ ድርጅቶች አቋም የተለመደ ነው። የስግብግብነትና የመስፋፋት አባዜ የተጠናወታቸው ናቸው። የሚገርመው የሁለቱን ፅንፈኛ ድርጅቶች አቋም አነስ ባለ በሚመስል ነገር ግን አደገኛ በሆነ ተግባቦት ለመወጣት የሚጥረው መንግስታዊ መዋቅር ነው። የፅንፈኞችን አላማ የተጋራው በቀን አስር ጊዜ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ሲያወሳ የሚውል ሰው መሆኑ ደግሞ ጉዳዩን የባሰ አሳፋሪ ያደርገዋል። ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ያደረጉትን እጅግ አስነዋሪ ንግግር መጥቀስ ይቻላል።

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ሰኔ 8/2011 ዓም ወደ ቤተ አማራ/ወሎ አቅንተው ነበር። ይህ የሆነው ኦነግ “ወሎ የኦሮሞ ግዛት ነው” ብሎ መግለጫ ካወጣ ከሳምንት በኋላ ነው። ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ ቤተ አማራ ያቀኑት ሜጫና ቱለማ የተባለው የኦነግ መሰረት የሆነ ድርጅት ቤተ አማራን የኦሮሚያ አካል የሚያደርግ ካርታ የታተመበት ባነር ሰቅሎ መግለጫ የሰጠ ሰሞን ነው። ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ ቤተ አማራ መሄዳቸው ችግር አልነበረውም። በስብሰባው ወቅት የተናገሩት ግን ከኦነግና ከሜጫና ቱለማ ጋር የሚያስማማቸውን አቋም ማራመዳቸው፣ የፅንፈኞቹን አላማ አንግበው የሄዱ መሆናቸውን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው።

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ቤተ አማራ/ወሎን እንደ አንድ ማንነት አድርገው በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተሰምተዋል። ቤተ አማራ/ ወሎን ከአማራ ማንነት ነጥለው በተደጋጋሚ ተናግረዋል። ጭራሽ ቤተ አማራ ከአማራ ማንነት ተለይቶ የአማራና የትግራይ እንዲሁም የኦሮሞና የአማራ ድልድይ የሆነ የተለየ ማንነት ያለው አስመስለው እጅግ አሳፋሪ አቋም አንፀባርቀዋል።

የጠቅላይ ሚ/ር ዐቢይ ይህን አቋም ሲያንፀባርቁ ሆን ብለው መሆኑን የውይይቱን ቪዲዮ ያየ ሁሉ የሚገነዘበው ነው። ጠ/ሚ ዐቢይ ይህን አቋም ሲይዙ ብቻቸውን አይደለም። ከሌሎች ድርጅቶች ጋር የተባበሩበት አውድ ይታያል። ኦነግ ቤተ አማራ/ወሎን የኦሮሞ ግዛት ነው ባለ በሳምንት ውስጥ፣ የኦነግ መነሻ የሆነው ሜጫና ቱለማ ቤተ አማራ ድረስ የሚደረሰውን የተስፋፊዎች ካርታ ዘርግቶ መግለጫ በሰጠበት ሰሞን ቤተ አማራን ከአማራ ነጥለው የአማራና የሌሎች ድልድይ የሆነ የተለየ ማንነት ያለው ለማስመሰል የጣሩት ጠ/ሚ ዐቢይ የተወጡት ሶስተኛ ሚና ነው። ኦነግ በግልፅ የአማራው ዋና እምብርት የሆነውን ቤተ አማራን የኦሮሚያ ግዛት ነው አለ። ኦነግ የወጣበትና ራሱን ሲቪክ ማኅበር ነኝ የሚለው ሜጫና ቱለማ ኦነግ በመግለጫው ኦሮሞ ነው ያለውን ቤተ አማራ ካርታ ወደ ኦሮሚያ አጠቃልሎ በሚዲያ አሳየን። ሜጫና ቱለማ ከኦነግ ለስለስ ባለ መልኩ ተስፋፊነቱን ሲገልፅ መንግስት የሚባለውን የሚመሩት ጠ/ሚ ዐቢይ ደግሞ የአማራውን እንብርት ቤተ አማራን ከአማራ የተነጠለ ማንነት እንዳለው አስመስለው አሳፋሪ የሆነ አቋማቸውን ሲገልፁ ውለዋል።

የሶስቱ ኃይሎች አላማ ግልፅ ነው። ሚናቸውም የተቀናጀ ነው። የመንግስት ግዴታ አለብኝ ያሉት ሰው የአማራው አንጓ የሆነውን ቤተ አማራ ከአማራነት ማንነት ነጥለው ለማሳየት ሞከሩ። ሲቪክ ማሕበር ነኝ የሚለው ሜጫና ቱለማ ካርታውን ስሎ በሚዲያ አሳየ። ከሜጫና ቱለማም የለየለት ፅንፈኛው ፀረ አማራ ኦነግ የተባለ ድርጅት የአማራውን አንጓ፣ ቤተ አማራን የኦሮሞ ግዛት ነው ብሎ ከጠ/ሚ ዐቢይም ከሜጫና ቱለማም ላቅ ያለና የለየለት አቋሙን ገልፆ መግለጫ ሰጠ። የሶስቱ አካላት ልዩነት የሚና መለያየት ነው። ፕሮፖጋንዳቸው የተለያየው በታክቲክ ብቻ ነው። አንደኛው ለጣራ ሲጠይቅ ሌላኛው ከዛም ከፍ ላለ፣ ሌላኛው ለሰማይ ይጠይቃል። ሁሉም ኃይሎች አንድ አላማ አላቸው ቤተ አማራን ከአማራው በመነጠል የአማራውን አንጓ መምታት ነው።

በተለይ የአማራ ብሔርተኝነት ሲጠነክር እንደነ ዐቢይ አህመድ የደነገጠ ያለ አይመስለኝም። ጠ/ሚ ዐቢይ ትህነግ/ሕወሓትን ለማስደሰት ሲሉ የወልቃይት ጥያቄ የመሰረተ ልማት ጥያቄ ነው ሲሉ ተቃውሞ ገጠማቸው። ወደ ጎንደርና ባሕርዳር በመሄድ የአማራውን አቋም አለሳልሰው ለመመለስ ጥረት አደረጉ። ያዩት ግን ማመን ያልሉትን ብሔርተኝነት ነው። አማራው አዳራሽ ውስጥ ቀልድ ስለቀለዱለትና የማይጨበጥ ተስፋ ስለሰጡት ብቻ ሽብርክ የሚል እንዳልሆነ ሲያውቁ ሌላ እቅድ ነደፉ። የመጀመርያው ከአማራው አብራክ የወጡትን ለዘብተኛ አቋም የያዙ ታዋቂ ግለሰቦች በመላክ ለማቀዝቀዝ ጥረዋል። እነዚህ ግለሰቦች ውጤታማ መሆን አልቻሉም። ሁለተኛው እቅድ የአንድነት ኃይል ነን የሚሉትን ድርጅቶች መጠቀም ነው። ይህኛውም ውጤታማ ሊሆን አልቻለም። በሶስተኛ ደረጃ በጎጥ ማሕበርና በእምነት ስንጥቅ ለመፍጠር የተጣረ መሆኑንም የምናጣው አይደለም።

በአራተኛ ደረጃ አዴፓ/ብአዴን የአማራውን ንቅናቄ እንዲያቀዘቅዝ ማዘዝ ነው። ይህኛውም እስካሁን ቀላል አልሆነም። ለአዴፓ/ብአዴን ከአማራው ንቅናቄ ጋር የመላተምን ያህል ራስን የማጥፋት ተግባር ያለ አይመስልም። ይህን አዴፓም የሚረዳ ይመስላል። በእርግጥ ይህን የእነ ዐቢይ ተልዕኮ ለመወጣት የሚጥርበት አጋጣሚ የለም ማለት ይከብዳል። ግን አጥጋቢ የሆነላቸው አይመስልም። አምስተኛው አማራጭ የለየለትን አቋም መውሰድ ነው። ከኦሮሞ ፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ሚና ለይቶ በአማራው ላይ መዝመት ነው። ሰኔ 8/2011 ዓም ጠ/ሚ ዐቢይ ያደረጉት እጅግ አስነዋሪ ንግግር የሚያስረዳው ከኦሮሞ ፅንፈኞች ጋር በመተባበር የአማራውን አንጓ ለመምታት ሚና መከፋፈላቸውን ነው።

ከወራት በፊት ቤተ አማራ ወሎ አካባቢ ለተደረገው ጥቃት የኦሮሞ ኃይሎች እጅ እንደነበረበት ግልፅ ነው። ለዚህ ደግሞ የገዥውና ዐቢይ የሚመሩት ድርጅት እጅ የለበትም ለማለት አይቻልም። ምድረገኝ/ከሚሴ ውስጥ ሽብር የፈጠሩ አመራሮች ከታሰሩ በኋላ የኦሮሞ ኃይሎች ተቀናጅተው አዲስ ጥቃት ለመፈፀም እቅድ ነበራቸው። ለጊዜው ሳይችሉ ቀርተዋል። እነዚህ ኃይሎች በአማራው ላይ ያደረጉትን ቅስቀሳ በጆሮዬ አዳምጫለሁ። የኦሮሞ ኃይሎች ጉዳዩን ወደሚዲያ ለመጎተት ያደረጉትን ጥረት አይተናል። ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎ የታሰሩት ይፈቱ እያለ የሚወተውት የኦሮሞ ገዥ ድርጅት መዋቅርም እንዳለ እየተገለፀ ነው። ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ ደሴ በሄዱበት ወቅት ይህን አጀንዳ አያነሱም ማለት አይቻልም።

አማራው የሚጠቃባቸው ስስ ክፍሎች በኩል እሳት ሲጫር ቆይቷል። አንደኛው ምደረገኝ ነው። በየቦታው እሳት ሲያቃጥል የከረመው ማን እንደሆነም እስከመቸውም ተደብቆ የሚቀር አይደለም። የአማራው አንደኛውና ጠንካራው አንጓ ቤተ አማራ ነው። ስስ በሆነው በምድረገኝ በኩል እሳት ለመለኮስ የጣሩት ሲያዙ የኦሮሞ የፖለቲካ ቡድኖች ዋናውን ቤተ አማራን፣ የአማራውን አንጓ ለማጥቃት የተለያየ ሚና ወስደው ዘምተዋል። መንግስት የሚባልን የሚመሩት ዐቢይ አህመድ ቤተ አማራን ከአማራ ለመነጠል ያስችላል ያሉትን ንግግር ሲደጋግሙ ዋሉ። ሲቪክ ማኅበር ነኝ የሚለው ካርታውን ዘርግቶ መግለጫ ሰጠ። ከሁለቱም የባሰው ኦነግ አፉን ሞልቱ “ወሎ ኦሮሞ ነው” አለ። ይህ የስስቱ ትብብር በአማራው ላይ የተቃጣ ነው፣ ባላንጣነት ነው። ዐቢይ አህመድ፣ ኦነግ እና ሜጫና ቱለማ!

የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን (State Owned Enterprises [SOEs]) ወደ ግል ይዞታነት ማዟዟር (Privatization) አንድምታ [ባየ ተሻገር]


————–
ክፍል (፩)
————–

በተለያዩ ምክኒያቶች እና በተለያዩ ጊዜያቶች ወደ አንድ መቶ አሥር (110) የሚጠጉ የዓለም አገራት በመንግሥት ይዞታ ሥር የነበሩ የልማት ድርጅቶችን ለግለሰቦች ወይንም በአክሲዮን ለሚተዳደሩ መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ሸጠዋል። በተለይ እንደ ማርጋሪት ታቸር ያሉ ገናና እና አወዛጋቢ አገረ-ገዥዎች በነበሩበት የአውሮጳ አህጉር እ.ኤ.አ በ1960ዎቹ እና በ1980ዎቹ ፕራይቬታይዜሽን ፋሺን ተደርጎ የተከናወነ የኢኮኖሚክስ አጀንዳ ነው። በመሆኑም ተፅዕኖው በውል የሚታወቅ ጥንካሬውም ድክመቱም በጥናት የተረጋገጠ የሰነበተ ጉዳይ ነው። ምናልባት በልዩነት መታየት የሚገባው ነገር ቢኖር በርካታ አጥኝዎች ትኩረት አድርገው የተመራመሩት በአውሮጳና በአሜሪካ (በተለምዶ ምዕራባዊያን የሚባሉትና የሰለጠኑት) ያለውን ተፅዕኖ በመሆኑ እንደ ኢትዮጵያ ያለ ህግና ሥርዓት ለማስፈን ያልቻለ እና የታወቀ የኢኮኖሚ መርሃ-ግብር በሌለው አገር ወደፊት ይኼ ይፈጠራል ወይንም ሊፈጠር ይችላል ብሎ መገመት አዳጋች ነው፤ ሳይንሳዊ ቲኦሪዎችን መሠረት አድርጎ የሚሰላ ግምት እና አናሊሲስ መነሻው የአገራቱ የፖለቲካ እና በአጠቃላይ የአገዛዝ ሥርዓት በመሆኑ በኢትዮጵያ ሊፈጠር የሚችለው በምዕራባዊው የአክዳሚክ ልኬት ተገማች አይሆንም።

ፕራይቬታይዜሽንን ኢትዮጵያ ከአፍሪቃ አገራት ጭምር ዘግይታም ቢሆን በስፋት ሄዳበታለች። ህወሓት መራሹ የወያኔ መንግሥት የደርግ መንግሥት ከተወገደ በኋላ ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል ፕራይቬታይዜሽን በግንባር ቀደምነት ሊጠቀስ የሚችል ሲሆን ይህ እርምጃ ከወያኔ በፊት የመንግሥት ፍላጎት (government will) ያልታየበትን ዘርፍ ሁሉ የነካካ ነበር። ቢሆንም ግን አይነኬ የሆኑ እንደ አየር መንገድ፣ ቴሌኮሙኒኬሽን ወዘተ ዘርፎች ለፕራይቬይታይዜሽን ዝግ ነበሩ።

ከ1984 ዓ.ም እስከ 1992 ዓ.ም በነበረው ጊዜ ውስጥ ከ223 በላይ ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታነት ተዘዋውረዋል። እስከ 1996 ዓ.ም ባሉት አራት ዓመታት ውስጥ ይህ ቁጥር ወደ 362 አድጎ ነበር። ወደ ግል ይዞታነት ከተዘዋወዋሩት ግማሽ ያክሉ (160) በማኑፋክቸሪግ ሴክተር (ጨርቃጨርቅ፣ ትንባሆ፣ ምግብና መጠጥ፣ ቆዳና ሌጦ) የተሰማሩ ነበሩ። ቀሪዎቹ ደግሞ ልዩ ልዩ አገልግሎት የሚሰጡ እንደ ሆቴል (ጊዮን ሆቴል፣ ራስ ሆቴል፣ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል፣ ኢትዮጵያ ሆቴሎች፣ ፍልውሃ)፣ ሱፐር ማርኬት (ጣና ሱፐር ማርኬት፣ ጅንአድ)፣ ኩራዝ ማተሚያ ወዘተ ይገኙበታል።

ከላይ የተጠቀሱት ከ360 በላይ የሚሆኑ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታነት መዘዋወራቸው ያስከተለው ለውጥ ምንድነው በሚለውም ጥናቶች ተካሂደውበታል። ምንም እንኳን ፕራይቬታይዝድ ከሆኑት መካከል ግማሽ ያክሉ (50%) ትርፋማ ናቸው ቢባልም የምርታቸው መጠን፣ ጥራት፣ ተደራሽነት መቀነሱ ታይቷል። ወደ ሰላሳ ሁለት (32%) በመቶ የሚሆኑት ጭራሽ ኪሳራ ውስጥ ያሉ ናቸው። ቀሪዎቹ ኪሳራም ትርፍም የሌላቸው ዕድገትም ያላስመዘገቡ ናቸው።

እንዲያውም በመንግሥት ይዞታነት ሥር ያሉት (SOEs) ወደ ግል ይዞታነት ከተዘዋወሩት በአገልግሎትም በምርትም የተሻሉ ሆነው የተገኙ ሲሆን ወደ ግል ይዞታነት የተዘዋወሩት ምርታማነት በአስራ አራት በመቶ (14%) መቀነሱ ተረጋግጧል። በዚህም ምክኒያት ፕራይቬታይዜሽን ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ አቆልቁሎ የተወሰኑት ወደ መንግሥት ይዞታነት እንዲመለሱ ተደርጎ ነበር።

በማይክሮ ኢኮኖሚው (Micro-economics) ዘርፍ ፕራይቬታይዜሽኙ የፈጠረው ተፅዕኖም የሚያኮራ አልነበረም። የማምረቻ ዕቃ ለባለሙያ ምጥጥን (equipment per person ratio) በግሉ ዘርፍ ዝቅተኛ ነበር፤ ፕሮዳክቲቭ አሴት የሚባሉትም (value of productive assets) እንዲሁ በግሉ ዘርፍ ዝቅተኛ ነበር። የሚያሳዝነው ወደ ግሉ ዘርፍ የተዘዋወሩት ድርጅቶች የመቅጠር አቅም/መጠን በአስራ ሁለት በመቶ (12%) የቀነሰ ሲሆን የምርት ደረጃቸው ደግሞ በአስራ አራት በመቶ (14.21%) መቀነሱ ተረጋግጧል። ለምርት መቀነሱ ዋነኛ ምክኒያት ተደርገው የቀረበት ደግሞ የጥሬ ዕቃ አለመኖር፣ የማምረቻ መሳሪያዎች ማርጀት እን መበላት ነበሩ።

የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግሉ ዘርፍ ማዞር የማኔጅመንት ፍልስፍና መሻሻል ያመጣል ተብሎ ተገምቶ የነበረ ቢሆንም ከአውቶክራሲ ወደ ዴሞክራሲ የተሸጋገሩት ሰላሳ አምስት (35%) የሚሆኑት ብቻ ናቸው። የሰራተኞችን ስልጠና በተመለከተ ደግሞ ግማሽ ያክሉ ሙያዊ ስልጠና መስጠት እንደቻሉ ተረጋግጧል።

በማክሮ-ኢኮኖሚው (Macro-economy) ዘርፍ የተደረገውን ለውጥ ለመገምገም በተደረገ ጥናት በፕራይቬታይዜሽን እና በበጀት ጉድለት (budget deficit) መካከል ያለው ቁርኝት ደካማ ሲሆን የግንኙነት ጠቋሚው (correlation coefficient, r) በጣም ዝቅተኛ (0.224) ነበር። ይህም ማለት ፕራይቬታይዜሽኑ የበጀት ጉድለቱን የማሻሻል አቅም አልነበረውም።

በተመሳሳይ ፕራይቬታይዜሽኑ የገበያ ውድድሩን ነጻ በማድረግ ኢኮኖሚውን ነፃነት ይሰጠዋል( economic liberation) ቢባልም የዚህ ዘርፍ ጠቋሚም በጣም ዝቅተኛ (0.099) ነበር (no correlation between privatization and openness of economy)። ይህም ማለት ወደ ግል ይዞታ ማዞር በማክሮ ኢኮኖሚው ዘርፍ የነበረው ተፅዕኖ ዝቅተኛ በመሆኑ ምንም የካፒታል አኩሙሌሽን ማምጣት አልቻለም።

ታዲያ ማንን ጠቀመ የሚል ጥያቄ መነሳቱ ስለማይቀር እስካሁን የተካሄደው ፕራይቬታይዜሽን ማንን ጠቀመ የሚለውን መመልከት ተገቢ ነው። ምንም እንኳን አጠቃላይ ፕራይቬታይዜሽን የአገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ ያላሻሻለ ቢሆንም አንጻራዊ በሆነ መልኩ ለተወሰኑ ቡድኖች ጥቅም ያስገኘበት ሁኔታ ግን ነበር። የመጀመሪያዎቹ ተጠቃሚዎች የወያኔ ባለስልጣናት ናቸው! ይኼውም የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ይዞታነት በማዘዋወር ወደ አራት መቶ አስር ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር (USD 410 million) ከሽያጭ የተገኘ ሲሆን በገቢው መንግሥታቸውን ለማጠናከው በተለይ ወታደራዊ ኃይላቸውን ለማሻሻል እንዳዋሉት ይታወቃል። ሁለተኛዎቹ ተጠቃሚዎች የትግሬው ጥረት (EFFORT) እና የሼክ አላሙዲ ሚድሮክ ናቸው። በ1987 ዓ.ም የተቋቋመው ኢፈርት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወደግል ይዞታ ይዘዋወሩ በሚለው ሴራ ተጠቃሚ እንዲረግ ስለተመቻቸ በ’Sub-Saharan’ አፍሪቃ ተወዳዳሪ የሌለው የኢኮኖሚ ማማ ላይ ተቀምጧል፤ በግንባታ መሳሪውያዎች፣ በቆዳ፣ በጨርቃጨርቅ፣ በጋርመንት፣ በማዕድን፣ በባንክ፣ በኢንሹራንስ፣ በመድኃኒት ወዘተ ዘርፎች በመሰማራት አገሪቱን ምጥምጥ አድርጎ ዘርፏል። መንግሥታዊ ባልሆነ የህዝብ የተራድዖ ድርጅትነት (non-governmental public charity) ሆኖ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀሰው ጥረት አንድ ጊዜ እንኳን ኦዲት ሆኖ አያውቅም። ሚድሮክ በተመሳሳይ ከሁለት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር (USD 2 billion) የሆነ መዋዕለ ንዋይ የሚገመት ካፒታል በሆቴል፣ በወርቅ ማዕድን፣ በብርጭቆ፣ በፕላስቲክ፣ በለስላሳ መጠጥ፣ በግል አየርመንገድ፣ በቤትና ቢሮ ፈርኒቸር እና ምግብ ማቀነባበሪያ ዘርፍ በመሰማራት በከፍተኛ መጠን ተጠቃሚ ሆኗል!

ከአሁን በፊት የተደረገው ፕራይቬታይዜሽን ያመጣው ውጤት እየታወቀ ለምን ሌላ ዙር አገራት ፕራይቬታይዜሽን ለማከናወን ታሰበ የሚለውን ቀጥለን እንመለከታለ።

ፕራይቬታይዜሽን እንዲከናወን ዋናው ገፊው ምክኒያት (Privatization Motives) የመንግሥት የልማት ድርጅቶች (SOEs) በገበያ ሁኔታ ተወዳዳሪ መሆን ሲያቅታቸው እና ይህም በደንብ (regulation) ውስብስብነት ወይም ጥብቀት (overregulated economy) ምክኒያት መሆኑ ሲታመንበት ዘርፎቹ ለውድድር ክፍት እንዲሆኑ በማሰብ የልማት ድርጅቶቹ ወደ ግል ይዞታነት እንዲዘዋወሩ ለማድረግ ነው። ይህ ኢኮኖሚክ ሊብራላይዜሽን (economic liberalization) የሚባለው ነው። ይሁን እንጅ የአሁኑ ፕራይቬታይዜሽን ትርፋማ የሆኑትን እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትዮ-ቴሌኮም ያካተተ በመሆኑ ሊበራላይዜሽን ገፊ ምክኒያት እንዳልሆነ ተጨባጭ ማሳያ ነው። በመሆኑም ሌሎች ምክኒያቶች ከጀርባው እንዳሉ መገመት አያዳግትም። የሚከተሉትን በዋናነት መውሰድ ይቻላል።

ሀ) ከፍተኛ የሆነ የብድር መጠን መኖር (large public and external debt)

ህወሓት መራሹ የወያኔ መንግሥት አገሪቱን እንደ መዥገር ተጣብቆ እንደ አለቅት ደሞን መምጠጡ የተረጋገጠ ሃቅ ነው። በተለያዩ የዜና አውታሮች እንደተረገው በርካታ ቢሊዮን ዶላር ከአገሪቱ እንዲወጣ ተደርጓል። ይህም ተረኛውን የኦሮሞ የበላይነት አስፋኝ አገዛዝ ባዶ ካዝና እንዲረከብ አስገድዶታል። በመሆኑም ካዝናውን ለመሙላት እና ተረኝነቱን ለማጠናከር የብድሩን መጠን መቀነስ ስላለበት ጥሩ ዋጋ ሊያወጡ የሚችሉ ድርጅቶችን ለመሸጥ ተገዷል።

ለ) ለጋሽ አገሮች በመደራደሪያነት ፕራይቬታይዜሽንን ማቅረባቸው (Donor Conditionality)

ኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀቷን በራሷ ማሟላት የማትችል መናጢ ደሃ አገር ናት። መንግሥት ነኝ የሚለው ፀረ-አማራ ገዥ መደብ በልመና የሚተዳደር የምዕራባዊያኑ ተመፅዋች ነው። የተረኛው የአብይ አህመድ ኦሮሟዊ መንግሥት ከተሾመ በኋላ በህዝብ ንብረት በተገዛ ቅንጡ አውሮፕላን እየተሽከረከረ ከአረቦች፣ ከቻይኖች ከሌሎችም አገሮች ልመናውን አጧጡፎታል። የትኛውም አገር በነፃ ገንዘብ አይሰጥም፤ ገንዘብ ሲሰጥህ በምላሹ የሚጠቀምነት ነገር እንዲመቻችለት ይፈልጋል። በመሆኑም የአሁኑ ፕራይቬታይዜሽን ኢትዮጵያን በግኝ ግዛት ውስጥ ለማድረግና ሪሶርሷን ለማሟጠጥ ለጋሽ አገሮች ያቀረቡት መደራደሪያ ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም።

ሐ) የኢፈርትን ፈለግ የሚከተል የኦሮሞ የንግድ ኢምፓየር ለመገንባት (ተረኝነት!)

ኦህዴድ የህወሓትን አሻራ በመከተል ላይ ያለ እንዲያውም በአንዲት ጀንበር ህዝቡን ሁሉ ውጨ ሰልቅጨ ኢትዮጵያን ኦሮሞ ካላደረኩ የሚል በግልፅ ተረኝነቱን የሚሰብክ ድርጅት ነው። ከህወሓት ሊማሩት የሚችሉት ነገር ደግሞ የኢኮኖሚ ብልጫ መሆኑ ምን ያህል የመግዛት አቅም እንዲሚያጎናፅፍ ነው። በመሆኑም ህወሓት የመንግሥት ልማት ድርጅቶችን ሸጦ ኢፈርትን እንደመሰረተ ሁሉ ተረኞቹ አዲስ ተመሳሳይ ድርጅት መፍጠር ስላስፈለጋቸው እንደሚሆን መላምት ማቅረብ ይቻላል።

ይቀጥላል …


ማጣቀሻዎች/Reference
1) Solomon Deneke (2001) – Private Sector Development in Ethiopia

2) Gebeye Worku, Alemu Getnet, Alemu Seyoum, Mekonen Alemu, Tesfaye Eyob, Ayele Gezahegn & Ishak Diwan (2000) – Has Privatization Promoted Efficency in Ethiopia?

3) Selvam J. (2008) – Privatization Programme in Ethiopia: is the cause justified?

4) Selvam J., Meenaksh, & Iuappan (2005) Privatization and Capital Accomulation: Emperical Evidences from Ethiopia

5) Tadesse Wodajo & Dawit Senbet (2017) – Does Privatization Improve Productivity? Emperical Evidence from Ethiopia

6) Wondwosen Teshome-Bahiru (2009) – Political Finance in Africa: Ethiopia as a Case Study

7) Ismail, Z. (2018). Privatisation of SoEs in Ethiopia since the1991. K4D Helpdesk Report.

የኢትዮጵያ አማራ ነገሥታት ከአፄ ልብነ ድንግል እስከ አፄ ፋሲል። (አጭር ሐተታ)

ልጅ ተድላ መላኩ ወረደ

ይኸን የምነግራችሁን ልብ በሉ፣ የሆነውንም አስተውሉ። የምነግራችሁ ሐቁን ነው፣ በዚያን ጊዜ የነበረውንና የተደረገውን የሚናገረው ነኝ። ለምታውቁትም ሁሉ ንገሩ።

የቤተ አምሓራው አፄ ልብነ ድንግል ቤተ መንግሥቱ ከነበረበት ከበራራ ከሸዋ አምሓራ ከአሕመድ ግራኝ ጋር ባደረገው ጦርነት ወደ ሰሜን ካፈገፈገ በኋላ እና የሸዋ አምሓራ መንግሥት በጦርነቱ ከፈረሰ በኋላ የቤተ አምሓራው ዙፋን (ከሸዋ እና ከዛሬው ደቡብ ወሎ) ወደ ጣና፣ ከዚያም ወደ ጎንደር ዞረ። ልብነ ድንግልም የሓበሻው ሰሎሞናዊ መንግሥት ሲወረር “ወደ ንጉሣዊ ሥልጣናችን መገኛ ወደ አባቶቻችን አምሓራ ነገሥት ምድር ሄደን ቤተ አምሓራን እስከሞት እንከላከል” ያለ ነው።

ይህ የሆነው ከአራት መቶ አመት በፊት ነው። በዚያን ጊዜ በዋቢ እና በጁባ ሸለቆዎች በኩል ከደቡብና ከምስራቅ ኦሮሞዎች ሉባ በሚባሉ መሪዎቻቸው እየተመሩ በሓበሻው መንግሥት ግዛት ውስጥ እየፈለሱ መግባት ጀመሩ። በሸዋም በአሕመድ ግራኝ ጦርነት ምክኒያት በፈራረሰው መንግሥት ስፍራ ላይ ሰፈሩበት። የአፄ ልብነ ድንግል ልጅ አፄ ገላውድዮስ የአሕመድ ግራኝን የዐረብና የቱርክ ጦር በጥቂት የፖርቱጋል ጦረኞች ድጋፍ ተዋግቶ ድል አደረጋቸው። አሕመድ ግራኝንም ገደለው። እርሱም ጦርነት ላይ ተሰውቶ አንገቱን አርደው ጭንቅላቱን ለአሕመድ ግራኝ ሚስት መበቀላቸውን ሊያሳዩ ወሰዱ። አስከሬኑም አምሓራ ሳይንት ተቀበረ።

እርሱን ተክቶ የልብነ ድንግል ልጅ የገላውዲዮስ ወንድም አፄ ሚናስ ነገሠ። ቀደም ብሎ እርሱን አሕመድ ግራኝ የኃይል ድጋፍ ለማግኘት ለየመን ሡልጣን በሽልማት መልክ አሳፍኖ በመውሰድ አሰጥቶት ነበር። ገላውዲዮስ ደግሞ የአሕመድ ግራኝን ልጅ በወይና ደጋ ጦርነት ይዞ ወንድሙን ሚናስን እንዲያስመልስ አስደረገው። ሸዋ ሲወረር ዙፋኑን መጀመሪያ ወደ ጎጃም አሽሽተው ሚናስን በጎጃም ከደብረ ወርቅ በስተ ደቡብ መንግሥቶ በሚባለው ቦታ ቅብዐ ንግሥ ቀብተው አነገሡት። ሚናስ ባሕር ነጋሹ ጋር ግጭት ተፈጥሮ ከርሱ ጋር ውጊያ አካሄደ ፤ በውጊያው ወቅት አትሮንሰ ማርያም በሚባለው ቦታ ተሞ አረፈ። እርሱን ተክቶ የልብነ ድንግል የልጅ ልጅ፣ የሚናስ ልጅ አፄ ሠርፀ ድንግል ከእቴጌ አድማስ ሞገሳ ተወልዶ ዘውድ ደፋ። አባቱ ሚናስ ሲዋጋው የነበረውን ባሕር ነጋሽ ይስሐቅን የኢትዮጵያን መንግሥት በኦቶማን ቱርክ እያስወረረ ስለነበር አባቱን ተክቶ ወጋው። በዚህ ጊዜ ኦሮሞዎች በሓበሻው ግዛት ላይ እየተስፋፉ ስለነበር ሠርፀ ድንግል በርሱ መንግሥት ላይ የመጣውን መጽዐት በጦር መዋጋት ጀመረ። በሰሜን የቱርክን ወረራ በውጊያ ድባቅ መታ። በደቡብ ደግሞ የኦሮሞ ሉባዎች ወረራ አካሂደው በከፍተኛ ውጊያ እያስጣለ ሕዝቡን ከምጽዐት ተከላከለ። አባ ባሕርይ መሲሕ ሠርፀ ድንግል ብለው መስክረውለታል። እርሱም አረፈ።

እርሱን የተካው የርሱ ልጅ አፄ ያዕቆብ (ዳግማዊ መለክ ሰገድ) ነበር። እርሱ ከእቴገ ማርያም ሰና የተወለደ ነበር። የርሱ የሥልጣን ተቀናቃኝ ልዑላን ያጎቱ ልጆች አፄ ዘድንግል እና አፄ ሱስኒዮስ ነበሩ። አፄ ሱስኒዮስ ከመንገሱ በፊት አባቱ፣ የአቤቶ (ልዑል) ያዕቆብ ልብነ ድንግል ልጅ፣ አቤቶ ግራም ፋሲል ያዕቆብ ከኦሮሞዎች ጋር ውጊያ እያደረገ ጦርነት ላይ ተገድሎ ያስራ ስድስት አመት ወጣት የነበረውን ሱስኒዮስን ኦሮሞዎቹ ይዘው ወሰዱት። በዚህ መሃል የሠርፀ ድንግል ወንድም የአቤቶ ልሣነ ክርስቶስ ልጅ አፄ ዘድንግል ነገሠ። እርሱም በኋላ የአፄ ሱስኒዮስ ሚስት እና የአፄ ፋሲል እናት የምትሆነውን የመራቤቴዋን እቴጌ ወለተ ሠዓለ (የንግሥና ሥም ሡልጣነ ሞገሳ) አግብቶ ነበር። እቴገ ማርያም ሰና ዘድንግልን ደቅ ደሴት ላይ እንዳይነግሥ አሳስራው ነበር። ዘድንግል አምልጦ ጎጃም በተራሮች ላይ ተሸሽጎ ቆየ። ከዚያም ያዕቆብ (ዳግማዊ መለክ ሰገድን) ተክቶ ነገሠ። ነገር ግን በቤተ መንግሥቱ በደንቀዝ የዤዝዊት ፖርቱጋል ካቶሊክ ፔድሮ ፓኤዝ ካቶሊክ ሃይማኖትን እንዲቀበል ስላሳመነው ዘሥላሴ የሚባል መሪ በጎዣም ተቃውሞና አመጽ እንዲነሳበት አደረገው። በዚህ መሃል ውግያ ተነስቶ በውጊያው ላይ ዘደንገል ተገደለ። አስከሬኑ ሦስት ቀን ሳይነሳ በጦር ሜዳ ላይ ወድቆ ቀረ። አንድ ገበሬ ካንዲት ዛፍ ስር ያንድ ሰው ቁመት የምታክል ቤተ እምነት ሰርቶ እዝያ ቀበረው።

በዚህ ጊዜ ኦሮሞዎች አባቱን ግራም ፋሲልን ገድለው እርሱን ይዘው የወሰዱት ሱስኒዮስ ኦሮምኛ ለምዶ ሥልጣን ለመያዝ የኦሮሞውን ኃይል ተጠቅሞ ያዕቆብን (ዳግማዊ መለክ ሰገድን)ወጋው (ኦሮሞው ምሑር ሙሓመድ ሓሰን ሱስኒዮስን ሲገልጸው “ኦሮምኛ መናገር የቻለው የመጀመሪያው አማራ ልዑል” ይለዋል)። ራስ አጥናተዎስና ዘሥላሴ አፄ ያዕቆብን ደግፈው ጦር አሰማሩ። ሱስኒዮስ ግን በጌምድር ላይ የዘሥላሴን ጦር አጠቃው። ከዚያም በጎጃም በሱስኒዮስና በአፄ ያዕቆብ መካከል ጦርነት ተካሄደ። በዚህ ጦርነት ራስ አጥናቴዎስና አፄ ያዕቆብ ተገደሉ። ከዚያም ያዕቆብን ተክቶ አፄ ሱስኒዮስ ነገሠ። ይኸም የሆነው እንዲህ ነው። ያዕቆብን ገድሎ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ አፄ ሱስኒዮስ ከኦሮሞዎች ጋር ታላቅ ጦርነት አደረገ። በአፄ ሱስኒዮስ የአማራ ጦር በኩል አራት መቶ ሰው ሲሞት፣ በኦሮሞው ጦር በኩል አስራ ሁለት ሺህ ሰው ሞቶ ሱስኒዮስ ድል አደረገ። የኦሮሞውን ኃይል ድል ካደረገ በኋላ በአክሱም ተሸሽጎ የነበርና “ያዕቆብ (ዳግማዊ መለክ ሰገድ) አልሞትም፣ እኔ እርሱ ነኝ” ብሎ (መልኩ እንዳይታይ “ፊቴ ቆስሎ ሸፍኘዋለሁ” ብሎ) በማታለል የነበረን ሰውና የርሱን ኃይል በዋልድባ በኩል ዘምቶ ድል አደረገው። ከዚያም ሱስኒዮስ በአክሱም ከተማ በቅብዐ ንግሥ ዘውድ ደፋ።

ዙፋኑ ከሸዋ ወደ ጎጃም፣ ከዚያም ሳይቆይ ወደ በጌምድር ዞሮ ማዕከሉን በበጌምድር አደረገ። አፄ ሱስኒዮስ ከልብነ ድንግል የልጅ ልጅ ከግራም ፋሲል እና ከእመቤት ሐመልማለወርቅ ነበር የተወለደው። ከነገሠ በኋላ የዘድንግል ሚስት የነበረችውን የመራቤተዋን ወለተ ሠዓል አግብቶ አፄ ፋሲለደስን ይወልዳል። እርስዋም በንግሥና ስሟ ሡልጣን ሞገሳ ትባል ነበር። የሱስኒዮስም ቤተ መንግሥት የነበረው የዘድንግል በነበረበት በደንቀዝ ነበር። የኢትዮጵያን ወሰን በሱዳን በኩል ከዳግማዊ አብደል ቀድር ጋር ባደረገው ውግያ አስፍቶት ነበር። የኦሮሞውን ኃይል ለመዋጋት የዤዝዊቶችን የመሳርያ ድጋፍ ለማግኘት እርሱም እንደ ዘድንግል ካቶሊክ እምነትን ተቀብሎ የኢትዮጵያ ይፋዊ ሃይማኖት እንዲሆን አደረገው። የካቶሊክን እምነት ይፋዊ ካደረገ በኋላ ብዙ ችግር መጥቶ አምባገነን መሆን ጀመረ። በመጨረሻም ዙፋኑን ለልጁ ለፋሲለደስ ለቅቆ ሲሞት በገነተ ኢየሱስ ተቀበረ።

የሱስኔዮስ ልጅ ፋሲለደስ (ዓለም ሰገድ)በመገዘዝ (ቡልጋ ሸዋ) ተወልዶ የጎንደር ከተማን መሰረተ። የመጀመሪያ እርምጃው የዤዝዊት ካቶሊክ አውሮፓዊያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የማጥፋት ተልእኮና ተጽእኖ ካለ ምንም ርኅራኄ ማስወገደ ነበር። ከቤተ መንግሥት ዙሪያ ተነቅለው እንዲወጡና ተጽእኖ እንዳይኖራቸው፤ ወደ ትግራይ እንዲሰደዱና ብዙዎቹ ከሀገር ለቀው እንዲወጡ አድረገ። የዤዝዊቶች ተጽእኖ ሰርጾ ገብቶና ሕዝብን እየለወጠ ስለነበር አውሮፓዊያን በአማራ ምድርና በመላው የኢትዮጵያ መንግሥታዊ ግዛት ለተወሰነ ጊዜ ከመግባት ተወገዱ። የየመን ኢማሞችን፣ የሳዋኪምና ምጽዋ ፓሻዎችን አስነግሮና ተደራድሮ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡን ሚሽነሪዎች እንዳያሳልፉ አስደረገ። አፄ ፋሲል አዲስ የኢትዮጵያን መንግሥት ዋና ከተማ በጎንደር ምድር ላይ ቆረቆረ። ይህን ያደረገው ከኦሮሞ ወረራ የአማራን ዙፋን ለማራቅና ለመጠበቅ ነበር:: ከጎንደር በፊት ዋና ከተሞች የሽዋ ግዛት ላይ ስለነበሩ፣ ለኦሮሞ ወረራ ይጋለጡ ነበር። እዚያ ምድር ላይ አፄ ፋሲል ከወራሪው ኃይል የአማራንና የኢትዮጵያን መንግሥት ሥልጣንና ፖለቲካዊ ማዕከሉን ጠብቆ በተሻለና በተጠናከረ መንገድ ለማቆየት በሚያስችል መልክ ጠንካራ ምሽግና ታላቁን ቤተ መንግሥት ገነባ። በዚያም ቦታ ነገሥታቱ እስከ አፄ ሣሕለ ድንግል ዘመን ድረስ ኖረዋል። ቤተ መንግሥቱ በጣም ዘመናዊና ትልቅ ገንዳ የነበረው ጠንካራና ባለ ታላቅ ግርማ ንጉሣዊ ቤተ መንግሥት ነው።

ዘርዓ ፋሲል

(በክፍል ፪ ከአፄ ፋሲል ቀጥሎ ያሉትን እናያለን)

ዐማራነትና ኢትዮጵያዊነት፦

ጊዜው የደረሰ የዐማራ ብሔርተኝነት የዐማራ ብቸኛ መዳኛ የሆነበት ዘመን ላይ ነን፡፡
ነጮች ጊዜው የደረሰን አሳብ ማንም ሊያቆመው አይችልም ይላሉ፡፡ ጊዜው የደረሰ አሳብ የሚባለው ቀደም ባሉት ዘመናት ወይም ዓመታት የሚያፈልቀው ጠፍቶ ወይም ደግሞ ቢፈልቅም ኅብረተሰቡ ሊቀበለው ሳይፈቅድ ቀርቶ ነገር ግን በሌላ ዘመን ብቅ ሲል ነባራዊና ኅሊናዊ ሁኔታዎች ለተፈጻሚነቱና ተግባራዊነቱ ተሟልተው የሚገኙበት አሳብ ማለት ነው፡፡ የዐማራ ብሔርተኝነትም ብቅ ያለው ይህን በመሰለ ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡ ዛሬ ጊዜው እንዲህ የደረሰውና ብሶትና መከፋት፡መከራና ስቃይ፡ መገፋትና መገለለል፡ መሞትና መጥፋት የወለደው ለጋውና የዐማራው ብቸኛው የመዳኛ መንገድ የዐማራ ብሔርተኝነት ገና በጥዋቱ ፍሬ ማፍራት ጀምሯል፡፡

ይሁንና በዚህ ሁኔታ በተነቃቃው የዐማራ ብሔርተኝነት አማካይነት ዐማራው እንደሕዝብ መብቱን ሲጠይቅ ወይም ደግሞ በማንነቱ ልደራጅ ሲል ከወዲሁ ለማሽማቀቅ ዘረኝነት፣ ጎሠኝነትና የሌሎች ፍረጃዎች ሰለባ ሲሆን ይታያል፡፡ በተለይም ደግሞ ዐማራው ለአንድ ሕዝብ ቅንጦት ስለሆኑት ነጻነት፣ እኩልነት፣ ዴሞክራሲ፣ ሉዓላዊነትና ሕዝባዊ ጥቅሞች ደልቶት የሚጠይቀው ሳይሆን ቀደም ብሎ ባለመደራጀቱ በመፈጸመው ታሪካዊ ስህተት እና ታሪካዊ ጠላቶቹ ከግራና ከቀኝ፣ ከፊትና ከኋላ ተወግቶ ቅርቀር ውስጥ (DEADEND) የገባውን ህልውናውን ለመታደግ ብሎ ተፈጥሯዊ የሆነውን ራስን የመከላከል ወይም የአልሞትባይ ተጋዳይነት (SELF DEFENCE) የሞት ሺረት ትግል በሚያደርግበት ወቅት እንበለምክንያት ሁሉም ተነስቶ ዘረኛ፣ ጎሠኛ፣ የኢትዮጵያዊነት ጠላት ሌላም አፉ አንዳመጣ ይከሰዋል፡፡ አሁን አሁን ደግሞ እንዲያውም እንድ የዐማራ ልጅ ማነህ ስትለው ዐማራ ነኝ ካለ ዐብን ነህ ይሉታል ወይም ከሌላ ጋር ማወዳጀት ተጀምሯል፡፡
ይሁንና ዐማራ የሚያራምደው የተቀደሰውን፣ በምክንያት የሚያምነውን፣ የተከበረውን፣ ጊዜው የደረሰውን እና የዐማራው ብቸኛ መደኛ፤ የኢትዮጵያዊነት መድኅን፣ ለጠላቶቹ ደግሞ ኮሶና ደማሚት የሆነውን የዐማራ ብሔርተኝነት ነው፡፡ የዐማራ ብሔርተኝት ስንልም የዐብን ወይም የአዴፓ አጀንዳ ብቻ አይደለም፣ የ50 ሚሊዮን (የአምሳ ሚሊዮን) እና ከዚያ በላይ የሆነው የእያንዳንዱ ዐማራ የህልውና ጉዳይ እንጅ፡፡ በርግጥ ማንም ሊክደው የማይችልው ሓቅ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ዐብን የዐማራ ሰቆቃ፣ ብሶትና መከራ አምጦ የወለደው የዐማራው የጭንቅ ቀን ልጅ መሆኑን ነው፡፡

በሌላ በኩል ዐማራ ዐማራ አትበሉ፣ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ በሉ ይሉናል፡፡ ነገሩ መልካም ነው ግን እውነት ዐማራ ኢትዮጳያን ዘንግቶ ወይም ጠልቶ ነው ዐማራ ዐማራ የሚለው የሚለውን በአግባቡ መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ዐማራ ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ የዐማራነትን ስያሜ ይዞ፣ ወጥ በሆነ ፖለቲካዊ ሥርዓት ታቅፎ፣ በጠበቀ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ግንኙነት የተቆራኘ ማኅበረሰብ ለመፍጠር በሺህ ለሚቀጠሩ ዘመናት ፍልሚያ ያደረገ፣ ለዚህ ግብ መሳካትም መተኪያ የሌለው የደም፣ የዐጥንትና የሕይዎት ዋጋ የከፈለ፣ ሁለትና ከዚያ በላይ እልፍ ዓመታትን የፈጀው ተመሳሳይ አገራዊ አስተሳሳብ የመፍጠር ጥረቱ ተሳክቶ ሀገረ ኢትዮጵያን ያበጃጀ፣ ለኢትዮጵያም ፍጹም የሞተላት ሕዝብ ነው። የዐማራ ሕዝብ ለኢትዮጵያ የዋለውን ውለታ ዘርዝሮ ለመጻፍ ምድር ወረቀት ብትሆን ውቅያኖስ ቀለም ቢሆን እንጨቶች ሁሉ ብዕር ቢሆኑ ሺህ ዓመታትንም ቢሞከር የሚቻል አይደለም፡፡
ስለሆነም ኢትዮጵያዊነት በዐማራ ልብ ውስጥ ተዘርቶ የበቀለና ትርጓሜውም፡-

 1. ኢትዮጵያዊነት ከጎሰኝነትና ዘረኝነት በላይ የሆነ የማንንት መገለጫ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት የደጋው ብርድና የቆላው ሙቀት የሚገናኙበት፣ የደጋው ዝናብ ከቆላው ወንዝ ጋር የሚዛመዱበት ኃይል ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ለሙሴ፣ ለክርስቶስና ለመሐመድ የተጤሰው እጣን በዕርገት መጥቆ የሚደባለቅበት እምነት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት በቄጠማ ጉዝጓዝ ላይ የሚታዬው መተሳሰብ፣ መፈቃቀርና መተዛዘን ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት የአስተዋይነት፣ የሚዛናዊነትና የጨዋነት ባሕርይ፣ ኩራትና ትህትና፣ ረዠምና ገና ተጽፎ ያላለቀ ታሪክም ማለት ነው፡፡ የዐማራው ኢትዮጵያዊነት ይህ ነው፡፡
 2. ኢትዮጵያዊነት ዜግነት ነው፣ አገራዊ ማንነት ነው፣ ጎሳ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያዊነት መነቀል፣ መፈናቀል፣ ያለፍርድ መታሰር፣ ያለበቂ ምክንያት መገደልም ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ለእናት አገር ፍቅር ተንቦግቡጎ መንደድ፣ ለብሔራዊ ስሜትም ደምን ማፍሰስ፣ ዐጥንትን መከስከስ፣ አካልን በፈንጅ አረር ማስቦደስም ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ለእምነት መታሰር፣ መማረክና መጋዝም ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት በአንድ ምላጭ ሳይቀቀልና ሳይሞረድ መላጨት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት በአንድ ጠባብ ጨለማ ክፍል ውስጥ እየተገረፉ በግዳጅ መታጎር፣ መታሰር ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት በቄጤማ ጉዝጓዝ ላይ ከዳሱ ሥር ተቀምጦ በአንድ ገበታ መቁረስ ነው፤ በአንድ ሽክና መዝናናት፣ በአንደ ጀበና ቡን አፍልቶ መጠጣትም ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ላመኑበት ነገር ደረትን ለጥይት ሰጥቶ በመትረየስ መደብደብ፣ የታጠቁትን ሽጉጥ መጠጣት፣ ከጠላት ፊትም ሳይሸሹ ቀርቶ አንገትን እስከማስቀላት ድረስ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ጥቃትን በጋሻ መክቶ፣ በጦርና በሽመል መፋለም ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ቅጠል በጥሶ፣ ሥር ምሶ፣ ጠበል ተጎንጭቶ፣ ጭዳ ገብሮ፣ አዋቂ ጠይቆ፣ ምስ ሰጥቶ፣ ደብር ደውሎ፣ ሕቅ እንቁን አንብቶ ንስሓ መግባት ነው፡ ሰቆቃና መከራ ያልፈታው የዐማራ ኢትየጵያዊነት ይህ ነው፡፡
 3. ኢትዮጵያዊነት በመጽሐፍ ቅዱስ፣ በቁራንና በታሪክ የተጠቀሰችወን ኢትዮጵያንና ፍጥረተ-ባሕርይዋን በሕይዎት መኖር፣ ከጥቅም ጋር ሳይሆን ከሰውነትና ከሥነልቡና ታላቅነት ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ መንፈሳዊና ማንነታዊ አስተሳሰብ ነው፡፡ ባጠቃላይ ኢትዮጵያዊነት መለኮታዊ ከፍታም ጭምር ነው፡፡ ላይነጣጠል በኪዳን ተዋህዶ የተሸመነው የዐማራ ኢትየጵያዊነት ይህ ነው፡፡

ስለሆነም ላለፉት ስድሳ (60) እና ከዚያ በላይ ዓመታት የፖለቲካ ምኅዋሩ የሚሽከረከርበት ዋናው እንዝርት የብሔር ፖለቲካ በሆነባት አገር ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች የየራሳቸውን አገር መሥርተው በልባቸው ሽሺገው መኖር ከጀመሩ ይኸው ግማሽ ምእተ ዓመት ሲሞላቸው ዐማራው ከብሔርተኝነት ራሱን አርቆ እንደጨው ሟምቶ፣ ከሞላው ሰው መሀል ብቻውን ቀርቶ፣ እንደቄጠማ ልሞ፣ ለባሰ ውርደትና የበታችነት ተጋልጦ፣ ጭው ወዳለ ምድረበዳ ተጉዞ፣ አውላ ሜዳ ላይ ወድቆ፣ የአውሬ ሲሳይ ሆኖ እኖረ እና መጠጊያ ያጣው ሁሉ ጎጆ መውጫ ሲያደርገው እንኳ ላፍታም ኢትዮጵያዊነቱን ያልዘነጋ፣ ወደፊትም የማይዘነጋ፣ ከኢትዮጵያዊነት ውጭ ሕይዎት አኝ ብሎ የማያስብ ድንቅ ሕዝብ ነው፡፡ ዐማራ ኢትዮጵያን ከሞት መንጋጋ ፈልቅቆ የሚያወጣ ታላቅ የአገር ባላደራ ሕዝብ ነው፡፡ እንዲያውም ዐማራው ከዚህ ብሔርተኝነቱ እርቆ በመኖሩ ምክንያት በሱ ላይ የደረሱ ችግሮች በሙሉ የኢትዮጵያ ችግሮች ሁነው የኢትዮጵያን ሕልውና ሲፈታተኗት መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡

ስለዚህ የዐማራ መደራጀት ለኢትዮጵያ አንድነት ፍቱን መደኃኒት እንጅ ሥጋት ባለመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊደግፈው፣ ሊያበረታታውና ሊያከብረው የሚገባ ነው፡፡

ኢትዮጵያ : የሃገሪቱት እዳ ክምችት አሳሳቢ እንደሆነ ተገለጸ!!


ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአራተኛ አመት የስራ ዘመኑ በስድስተኛ ልዩ ስብሰባው የገንዘብ ሚኒስቴርን የ 2011 ዓ.ም በጀት አመት የአስር ወራት አቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጧል፡፡
የሃገሪቱ እዳ ክምችት ከኤክስፖርት አፈጻጸሙ ጋር ሲነጻጸር አሳሳቢ መሆኑን የገንዝብ ሚኒስቴር ሚስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የመስሪያ ቤታቸውን የአስር ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ተናግረዋል፡፡
የኤክስፖርት አፈጻጸም ውስንነትን በዘላቂነት ለመፍታት የግል ሴክተሩን በከፍተኛ ደረጃ በማሳተፍና አላሰራ ያሉ ማነቆዎችን ለይቶ በመንቀሳቀስ ኤክስፖርት ተኮር ስራዎችን መስራት እንደሚገባም አቶ አህመድ ገልጸዋል፡፡
የኤክስፖርቱ ገቢ አፈጻጸም ከአመት አመት ማሽቆልቆል የማክሮ ኢኮኖሚው ጤናማ አለመሆን መገለጫ መሆኑን ያነሱት አቶ አህመድ ፤ የኢኮኖሚ ሚዛን ክፍተቶችን ለመሸፈን በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡
በ2011 በጀት አመት አስር ወራት ውስጥ ከኤክስፖርት 2.1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ቢገኝም ከ 2010 በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 2.3 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነጻጸር በ 187.1 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ ማሳየቱን አቶ አህመድ ገልጸዋል፡፡
በማዕከላዊሰ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ መሰረት በሚያዚያ ወር 2011 ዓ.ም የአስራ ሁለት ወራት ተንከባላይ አማካይ ሃገራዊ አጠቃላይ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ እድገት 12.6 በመቶ መሆኑንም አቶ አህመድ ጠቅሰዋል፡፡
የዋጋ ንረቱ በአንድ አሃዝ እንዲገደብ ለማድረግ ያልተቻለ ቢሆንም በዝቅተኛው የሁለት አሃዝ እንዲረጋጋ ለማድረግ እንደተቻለም ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡
በዋናነት ለዋጋ ንረቱ የአቅርቦት ችግር ፤ ውስጣዊ የፖለቲካ አለመረጋጋትና የህግ የበላይነት አለመከበር ምክንያቶች እንደሆኑ አቶ አህመድ ተናግረዋል፡፡
የውጭ ክፍያ ሚዛን መዛባት ለማክሮ ኢኮኖሚው አለመረጋጋት ከሚጠቁሙት የኢኮኖሚ መሳሪያዎች ውስጥ አንዱ መሆኑን የጠቀሱት አቶ አህመድ ፤ ለሃገራችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ አስፈላጊ የሆኑ ሸቀጦችንም ሆነ የካፒታል እቃዎች በሃገር ውስጥ ማሟላት እንዳልተቻለና ከውጭ ማስገባት ግዴታ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የውጭ ምንዛሬ አቅርቦታችን አስተማማን ምንጭ የሆነው የሸቀጦች የውጭ ንግድ አፈጻጸም ችግር እንደገጠመው ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡
የኢኮኖሚ ሚዛንን በመጠበቅ የማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋትን ለመፍጠር በተደረገው ጥረት ባለፉት አስር ወራት የመንግስትን ወጪ በገቢው እንዲሸፈንና የእዳ ጫናን ለማቃለል የሚያስችሉ ተግባራት እንደተከናዎኑ አቶ አህመድ ተናግረዋል፡፡
በኢኮኖሚው ውስጥ እድገት ቢኖርም የእድገት ፍጥነቱ ግን እየቀነሰ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2011 ዓ.ም በጀት አመት እሰበስባለው ብሎ ካቀደው ብር 235.7 ቢሊዮን ውስጥ 160.4 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ እንደተቻለም ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡
የወጣቶች ተዘዋዋሪ ፈንድ እስካሁን ደንብና መመሪያ አልወጣለትምና አፈጻጸሙ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከምክር ቤት አባላት ጥያቄ ተነስቶላቸዋል፡፡
ገንዘቡን የሚያስተዳድሩት ክልሎች ስለሆኑ የተዘዋዋሪ ፈንዱ አፈጻጸም በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ የተጠቃለለ ሪፖርት እንዳልደረሳቸውና መመሪያና ደንብም በቅርብ እንደሚወጣለት ተናግረዋል፡፡
የሃገራችን የውጭ እዳ ክፍያን ለማቃለል ከቻይና ጋር የተደረጉ የዲፕሎማሲ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸው ፤ 188 የፌደራል ባለበጀት መስሪ ቤቶች ኦዲት ሪርት እንዲመረመር መደረጉን ቋሚ ኮሚቴው በጥንካሬ ከጠቀሳቸው መካከል ናቸው፡፡
በሌላ በኩል የውጭ እዳ ክፍያ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆኑና ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት በቂ ስራ እየተሰራ አለመሆኑን ቋሚ ኮሚቴው በእጥረት አንስቷል፡፡
ምክር ቤቱ ዶ.ር ንጉሴ ምትኩ ገላው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲሾሙ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ.ር ዐቢይ አህመድ የቀረበለትን ሹመት በአብላጫ ድምጽና በአራት ድምጸ ተዓቅቦ አጽድቆታል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚውም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ- መሃላ ፈጽመዋል፡፡
አንድ የምክር ቤት አባል የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ከስራቸው የለቀቁበት ምክንያት እንዲገለጽላቸው ሹመቱን ያቀረቡትን የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነትን ቢጠይቁም የቀድሞው ዋና ስራ አስፈጻሚ የለቀቁበትን ምክንያት ቋሚ ኮሚቴው ያውቀዋል፤ በገዛ ፈቃዳቸው ስራቸውን እንደለቀቁ ሰምተናል በማለት ሁኔታውን በዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

”የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፈተና እና የአማራው የዲፕሎማሲያዊ አማራጭ” (ጌታቸው ሺፈራው)

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ቃለመሃላ ሲፈፅሙ

ሰሞኑን ከአንዳንድ ወዳጆቼ ጋር ስለ ውጭ ጉዳይ ሚስትር መስርያ ቤቱና በአቶ ገዱ የሚኖረው ጫና ላይ እያወራልን ነበር። ዛሬ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መካከል አለመግባባት እንዳለ እየተዘገበ ነው። በእርግጥ ይህ ጉዳይ የውጭ ጉዳይን ለሚያውቅ ብቻ ሳይሆን ከኦዴፓ አንፃር ምን እየተሰራ እንደሆነ ለሚገመት አዲስ አይሆንበትም። ባለፉት 27 አመታት የውጭ ጉዳይ ሲዘወር የኖረው በሕወሓት ሰዎች ነው። አብዛኛዎቹ ኤምባሲዎች በሕወሓት ሰዎች አሊያም ታዛዦቹ ተይዘው ቆይተዋል። የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎችን ሊያግዙ ይችላሉ፣ ወይንም ይተላለፉባቸዋል የተባሉት ሀገራትና አካባቢዎች በሕወሓት አንጋፋ ታጋዮች ወይንም ወታደራዊ ኃላፊዎች የተያዙ ነበር። ሱዳን፣ ሶማሊ ላንድ፣ ደቡብ ሱዳንን ጨምሮ ጎረቤት ሀገራት እንዲሁም ለሕወሓት የኢኮኖሚ ጥቅም የሚያስገኙ እንደ ቻይና ያሉ ሀገራት፣ በተጨማሪም ተቃዋሚዎች ቦታ ያገኙባቸዋል የተባሉ የምዕራባዊያን ሀገራት በልዩ ትኩረት የሕወሓት ዲፕሎማሲ መዳፍ ስር ነበሩ። የሕወሓት ሰዎች አምባሳደር ባይሆኑ እንኳ ከአምባሳደር ባነሰ ማዕረግ ከአምባሳደሩ በላይ ሆነው ሲሰሩ ኖረዋል። የአብዛኛዎቹ ኤምባሲዎች የደሕንነትና ወታደራዊ አታሼዎች የሕወሓት ሰዎች የተያዙ ነበሩ። የደሕንነትና ወታደራዊ አታሼ ትልቁ የኤምባሲ ስራ ሲሆን ከሕወሓት ውጭ ላሉት ይፈቀድ የነበረው የኢኮኖሚያ ባሕል ነክ ጉዳዮች ናቸው። ከሕወሓት ውጭ የሆነ አምባሳደር አብዛኛው ስራ የሕወሓትን ስራ ማስተባበልና ከደሕንነትና ፖለቲካ ስራዎች ውጭ ያሉትን መከወን ነበር። በአንፃሩ የደሕንነትና ወታደራዊ አታሼዎች አምባሳደሩን እየዘለሉ መረጃዎቹን ለሕወሓት ቁልፍ ባለስልጣናት ሲያቀብሉ ኖረዋል። የደሕንነትና ወታደራዊ አታሼዎች ከአምባሳደር አንዳንዴም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እያለፉ ለሕወሓት ቁልፍ ባለስልጣናት ሪፖርት ሲያደርጉ እንደነበር ኦዴፓ/ኦህዴድም በአቅም አልባነት ሲታዘበው የቆየ ጉዳይ ነው።

ይህን ሆኖ ግን የኦሮሞ ብሔርተኞች በዲፕሎማሲው የነበራቸው ንቁ ተሳትፎ ኦዴፓ/ኦህዴድ እንደ ድርጅትም ሆነ ኦሮሞ እንደ ሕዝብ በዲፕሎማሲው ባዶ እጁን እንዳይቀር አድርገዋል። በሀገር ውስጥ የሚገኙት የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ኤምባሲዎችና ድርጅቶች ጋር የነበራቸው ግንኙነት ቀላል የማይባል የነበረ ሲሆን በውጭ የሚገኙት ደግሞ ሕወሓት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚፈፅመውን በደል ከማሕበራዊ ሚዲያ ሳይቀር ለቃቅመውና ተርጉመው ተቋማቱን የሚወተውቱ ነበሩ። የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች ሪፖርት ከማቀበል አልፈው እነሱ የሚፅፉትን የሀሰት ትርክት የሚያሳምንላቸው በርካታ የውጭ ፀሃፊና ጋዜጠኛ አፍርተዋል። ስለ ኦሮሞ ሕዝብ የሚፃፍበትና የሚነገበት፣ የፃፉትን ሁሉ የሚያቀርቡበት ጥናት ማሕበርም ጭምር አላቸው። በዚህ ሂደት ሕወሓት ዲፕሎማሲውን ጠቅልሎ እንዳይወስደው አድርገዋል። የሕወሓትን ተግባር ሲከታተል የነበረው ኦህዴድ/ኦዴፓ አልፎ አልፎ ከብሔርተኞቹ ጋር የሚያደርገው ቀጭን ግንኙነት የኦሮሞ ዲፕሎማሲ የከፋ ብልጫ እንዳይወሰድበት አድርጓል። ከምንም በላይ ባለፉት ጥቂት አመታት ወርቅነህ ገበየሁ የውጭ ጉዳይ ሲሆን ኦህዴድ/ኦዴፓ ሕወሓት ይጠቀምበት የነበረውን ተቋም ወደራሱ ለማዞር ብዙ ርቀቶችን ሂዷል። ባለፈው የ”ለውጥ” ወቅት ደግሞ ኦዴፓ የውጭ ጉዳይ መስርያ ቤቱን ሙሉ በሙሉ ወደራሱ እንዲያዞር ወርቃማ እድል አግኝቷል። የመጀመርያው እርምጃ ሕወሓት ይዞት የነበረውን የወታደራዊና ደሕንነት አታሼ መቆጣጠር ሲሆን ቀጥሎም በሕወሓት ዘመን በአክቲቪስትነት የኦሮሞ ሕዝብን በደል ለዓለም ዐቀፍ ማሕበረሰብ በማድረስ ሕወሓት በውጭ ጉዳይ የሚያደርገውን ለመደገዳደር ላይ ታች ይሉ የነበሩትን “አክቲቪስቶች” ሳይቀር አምባሳደር በማድረግ በእየ ኤምባሲው በማስገባት ተቋሙን ለመንጠቅ ጥሯል።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የውጭ ጉዳይ ሆነው ሲሾመ እነ ዐቢይ አዴፓ/ብአዴን ምንም አያመጣም ከሚል እንጅ ሀገራዊ ተቋም እንዲሆን ፈልገው አይደለም። በሕወሓት ዘመን የደሕንነትና ወታደራዊ አታሼዎች አምባሳደሩን አልፈው ለቁልፍ ባለስልጣናቱ ያደርሱ እንደነበረው ሁሉ በኦዴፓ ዘመንም ከአምባሳደር ያነሰ ስልጣን የተሰጣቸው የኦዴፓ ሰዎች የእየ ኤምባሲዎቻቸውን አምባሳደሮች ብቻ ሳይሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን አልፈው ለጠ/ሚ ዐቢይ፣ ለጀኔራል ብርሃኑ ጁላ፣ ለምክትል ደሕንነት ኃላፊው ደመላሽ ሪፖርት የሚያደርጉበት አጋጣሚ ሰፊ ነው። ይህን ከሕወሓት ተምረዋል። በርካታ ነገሮችን ከሕወሓት ሲወርሱ ቀዳሚ የሚያደርጉት ተቋማዊ አሰራሩን ዘልሎ በድርጅት መረጃን መቀያየርንም ነው።

ጉዳዩን የባሰ የሚያደርገው ደግሞ በተቋሙ ውስጥ ያሉ የአማራ ባለሙያዎች የማይጋፉና ከሕግ ውጭ ሲሰራም “ይህን ነገር አላይም” ብለው የሚሸሹ መሆኑ ነው። ይባስ ብሎ በሕወሓት ዘመን የኦሮሞ ብሔርተኞች በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ እየወተወቱ በዲፕሎማሲው ተወዳዳሪ ከሆኑት በተቃራኒ የአማራ ምሁራንና ፖለቲከኞች ስለ ሕዝባቸው በደል የተቋማትን በር በማንኳኳት፣ ታዋቂ ግለሰቦችንና ሚዲያዎችን በመወትወት ስንፍና የተጠናወታቸው መሆኑ ነው። የአማራ ምሁራን በአንድ ብሔርተኝነቱን የያዙትን ታናናሾቻቸው በመናቅ እነሱ ሕዝብ ላይ በሚወረወረው ጭቃ ሲዳክሩ ዳር ቆመው ከማዘን አልፎም የሌላውን ስላቅና ሳቅ በታናናሾቻቸው ላይ ከማዳመቅ ያለፈ ስራ ሲሰሩ አይታይም። የአማራው ጉዳይ ያገባናል የሚሉት እንኳን ሌሎቹ ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ ያለውን ሀቅና ሪፖርት ለቃቅመው ደጅ መጥናት ቀላዋጭነት የሚመስላቸው ሰነፎች ናቸው። በቅርቡ እንኳ የኦሮሞ ብሔርተኞች በዓለም ተፅዕኖ ፈጣሪ የተባሉ ተቋማትን በእነ እስክንድር ነጋ ላይ ሳይቀር አሉታዊ አቋም እንዲይዙ የሀሰት መረጃ ሲያቀብሉ ቀሪው የኦሮሞ ብሔርተኞች እየፈፀሙ ያለውን ጭካኔ ለማሳወቅ የረባ ርቀት አልሄደም። በተለይ የአማራ ምሁራንና ፖለቲከኞች ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ እንዳለው በደልና ስቃይ በዲፕሎማሲው እያሳዩት ያለው ስንፍና ቅጥ ያጣ ሆኗል። የኦሮሞ ፅንፈኞች በኢትዮጵያ ለውጥ ያመጣው ቄሮ መሆኑን ለዓለም ደግመው ደጋግመውና አጋንነው በነገሩት መሰረት ብዙዎቹ ይህን ጉዳይ ወደማመን ደርሰዋል። በአንፃሩ የአማራው ምሁር፣ ፖለቲከኛና ጠያቂ አማራው የነበረውንና ያለውን አስተዋፅኦ በሚገባ መናገር አልቻለም። በተቃራኒው በኦሮሞ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን……የተጋነነለት ቄሮና የለውጥ ኃይል የተባለው ስህተትና ጭካኔ ሲፈፅም የሚያጋልጥና ለዓለም የሚያሳውቀው እምብዛም ነው። ይህን ለማጋለጥ እድሉ ያለው ሳይቀር እንደሌላው ታዝቦ፣ ሲያልፍም ከኢትዮጵያውያን ጋር ተወያይቶበት ይቀራል እንጅ ወደ ዲፕሎማሲ ሜዳው አይወስደውም።

በዚህ የተነሳ በየ ኤምባሲው ያሉት አማራዎች ታዛዥ ከመሆናቸው በላይ የረባ ሽፋን የማያገኙና የተጋለጡ ናቸው። በዚህ መሃል ደግሞ የአማራው ዲፕሎማሲ ባዶውን እንዲቀር ሆኗል። አማራው ከሚፈፀምበት በደል አንፃር በቅርብ እነ ቴዎድሮስ ትርፌ ካደረጉት ውጭ ይህ ነው የሚባልና የአማራውን በደል የሚመጥን የዲፕሎማሲ ስራ አልተሰራም። ሕወሓት ባለፉት 27 አመታት በያዘው መዋቅር ያፈራቸው መዋቅሮችና ሰንሰለቶቹ አሁንም ተወዳደሪ ሆኖ እንዲቀጥል አድርጎታል። ቢያንስ ከአዴፓና ከአማራው የተሻለ ነው። ዲፕሎማሲውን ኦዴፓና ሕወሓት የተቆጣጠሩት ስለመሆኑ ድብቅ ከሆኑት የዲፕሎማሲ ውጤቶች ለብዙሃኑ ግልፅ ባይሆን እንኳ መደበቅ ከማይቻለው ኢንቨስትመንት መገንዘብ የምንችለው ወደ ትግራይና ኦሮሚያ የሚሄዱትን ለአፍታ ስናስብ ነው።

ሕወሓት ተቋማቱን ተጠቅሞ የዳያስፖራ አባላቱን አጠናክሯል። ጠንካራ ቡድኖችን፣ ተቋማትንና ግለሰቦች ጋር ግንኙነት አለው። መስርቷል። ኦዴፓ በቅርቡ የሕወሓትን የቀድሞ ተቋም በባሰ ሁኔታ በየ ኤምባሲው አክቲቪስት እየመደበም ጭምር ይዞታል። በዚህ ሂደት የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ሚና ወደ ምንም የሚጠጋና ከነበረው ግፊትና ትችት ለማምለጥ አማራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ይዟል እንዲባል ያለመ ብቻ ነበር። ይህን እውነታ አቶ ገዱ የተቀበሉት አይመስልም።

ሌላውና ትልቁ ችግር የጠ/ሚ ዐቢይ ባሕሪ ነው። እነ መለስ የለየላቸው አምባገነኖች ናቸው ተብለው ይፈራሉ። የተፈራ ምንም ቢያደርግ ከሚጠበቀው አንፃር የተለየ ትዝብት ውስጥ ላይገባ ይችላል። ያም ሆኖ ግን ለይምሰል ፕሮቶኮል ለማክበር ይጥራሉ፣ ወይንም ያከበሩ ይመስላሉ። የእነ ዐቢይ አካሄድ ከዚህ የተለየ ነው። አምባገነን እንዳልሆኑ ለማሳየት እየሞከሩ ነው። እነ ገዱ ጋር ይቅርና ከዛም ያነሰ ስልጣን ካላቸው ሰዎች ብሎም ከሕዝብ ወኪሎችና ከሕዝብም ጋር ጥሩና ቀለል ያለ ቅርርብ አላቸው እንዲባሉ እየጣሩ ነው። በዚህም መሰረት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩና አምባሳደሮች ጋር ብቻ ሳይሆን የሚጠቅሟቸው የኤምባሲ ሰራተኞች ጋር ይህ ግንኙነት መኖሩ የማያጠራጥር ነው። በዚህ ግንኙነት መሰረት ደግሞ ፕሮቶኮልም ሆነ ሌላ የአሰራር መመርያ ይልቅ በቀጥታ መረጃ መቀበልን የሚመርጡበት መንገድ ብዙ ነው። ሕወሓት በድብቅ ሲያደርግ የነበረውን እነ ዐቢይ በቅርርብ፣ ብዙ ሴራና መደባባቅ ሳይታከልበት ከደሕንነትና የመከላከያ አታሼ መረጃ የሚቀበሉበት አጋጣሚ ሰፊ ነው። ይህ ከእነ ዐቢይ ጋር የለውጥ ኃይል እየተባሉ ለተወደሱት እነ ገዱ ላይዋጥ ይችላል። በእርግጥ ይህ ፈተና በገዱ የጀመረ አይደለም። አቶ ደመቀ መኮንን በዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ መሆናቸውን በቅርቡ እያሳዩት ካለው አቋም መገንዘብ ይቻላል። አቶ ደመቀ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙነት መድረክ ሳይቀር ውስጠ ወይራ ሲናገሩ መስማት የተለመደ ሆኗል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አቶ ደመቀ እያሳዩት ያለው አቋም ቤተ መንግስት ውስጥ እየተሰላቹ መሆኑን የሚያሳብቅ ነው። አቶ ደመቀ በመለስ ዜናዊ ዘመንም ለቤተ መንግስት ቅርብ ነበሩ። የሚፈራው መለስ ዜናዊ በነበረበት ዘመን የሚሰጣቸውን ቦታና “ክብር” በቃኝ ብለው፣ አንዳንዴ የተጨመረላቸው ሲመስላቸውም ተደስተው አሳልፈው ይሆናል። በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ዘመን ደግሞ የተሻለ ቦታና ነፃነት ነበራቸው። ዐቢይ አህመድ ተቋማዊ ከሆነው አሰራር ይልቅ ሕዝብ የሚወድላቸውንና ለታይታ የሚያጋልጣቸውን ሲሰሩ የእነ ደመቀን ቦታም እየረገጡ ጭምር ነው። ቀደም ባለው ጊዜም ከእነ ዐቢይ የተሻለ ወደ ቤተ መንግስት የቀረቡት አቶ ደመቀ በዚህ ተግባር ዐቢይን መታዘባቸው አልቀረም። ከእነ ዐቢይ የተሻለ ቤተ መንግስትና አሰራሩን አውቀዋለሁ ሲሉ በዘፈቀደ ሲሰራ ትዝብት ከማዳበራቸው ባለፈ አድሏዊ አሰራሩንና ስግብግብነቱን በቅርብ ሲመለከቱ ቆይተዋል። አቶ ደመቀ ከነበራቸው ልምድ አንፃር በእነ አብይም ሆነ በሕዝብ የለውጥ ኃይል ተብለው የተወደሱ እንደመሆኑ በዘፈቀደ የሚሰራውን ኃይል አቤት ብሎ መቀበሉ የሚያስከፋቸው መሆኑ ግልፅ ነው። የኦሮሞ ብሄርተኞች በሚፈጥሩት ጫናም ሆነ በይሁንታ የሚሰራው ስራን በቅርብ ከማየት ባለፈ ይህ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠትና መከራከር ሲመጣ አንዳንዴ አደባባይ ላይ ሲገለጡ ከምናያቸው የእነ ዐቢይ ባህሪ የከፉ ነገሮች ቤተ መንግስት ውስጥ መፈጠራቸው የሚገመት ነው። በዚህ ሂደት ያሉት አቶ ደመቀ ጠ/ ሚ በተገኙበት ሳይቀር ጎሸም ሲያድርጓቸው ታይቷል። ይህን የሚያደርጉት ቤተ መንግስት ውስጥ የሚታፈኑትን በአደባባይ ሕዝብ እንዲገምትላቸው ይመስላል። ከሳቸው ባለፈ ግን ሌሎች ምን ሊገጥማቸው እንደሚችል መምከር የሚችሉ ይመስላሉ። በተለይ በቅርቡ በጫና ቁልፍ ወደሆነው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሄዱት አቶ ገዱን ምን እንደሚገጥማቸው የቤተ መንግስቱን ጉድ በቅርብ ከሚያውቁት ከአቶ ደመቀ በላይ የሚያሳውቃቸው ሰው ያለ አይመስልም። የጠ/ሚ ዐቢይን አካሄድ በቅርብ የሚያውቁት አቶ ደመቀ አቶ ገዱ አዲስ ሆነው ግራ ቢጋቡ እንኳን መብታቸውን እንዲጠቀሙ መገፋፋታቸው የሚቀር አይመስልም። አቶ ገዱ እነ ዐቢይ በፈለጉት ሳይሆን ተቋማዊ በሆነ መንገድ እሰራለሁ ማለታቸው ደግሞ ለእነ ዐቢይ የማይወጥ ጉዳይ ነው። እነ ዐቢይ የሚያስቡትና ተቋማዊ አሰራሩ መጋጨቱ ግልፅ ነው። አቶ ገዱ ተቋማዊ አሰራርን ሲመርጡ ከሕወሓት በወረሱት፣ ከኦሮሞ ብሔርተኞች በሚመጣባቸው ግፊትና ኦዴፓ የሚያስብበት የተረኝነት አመለካከት ለግጭት የሚዳርግ ነው።

ይህ በተቋምና በመንግስት ባለስልጣናት መካከል ያለ ግጭት ግን በኢህአዴግ ፖለቲከኞች መካከል ያለና የሚቀር ግጭት ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም። ኦዴፓ አክቲቪስትና ፅንፈኛውን ሳይቀር በየቦታው የሚሰገስገው ለግል ስልጣን ብቻ ብሎ እንዳልሆነ ግልፅ ነው። ይልቁንም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሀሰት ትርክቱን መሰረት በማድረግ የፅንፈኞቹ ጥቅም እውን ለማድረግ ተቋማቱን መጠቀማቸው የማይቀር ነው። ይህ ደግሞ ገዱን ወይንም አዴፓን ረግጦ በማለፍ የሚበቃ አይደለም። የአማራን ብሎም የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥቅም የሚጎዳ እንጅ። የኦሮሞ ፅንፈኞች በሕዝብ ላይ የሚፈፅሙትን በደል፣ በአዲስ አበባ፣ በአማራው፣ በአፋሩ፣ በደቡቡ፣ በሶማሊው……ፅንፈኞቹ የሚፈፅሙትን በደል እነ ገዱ አንሸፋፍንም ቢሉ ከአምባሳደር ያነሰ ቦታ ተሰጥቷቸው በየቦታው የተቀመጡትና የኦዴፓ አምባሳደሮች ከቁልፍ ባለስልጣናት ጋር ሆነው ይሰሩታል። በተቃራኒው አዲስ አበባ ላይ፣ በአማራውና በሌላው መልካም ስራ የሚሰሩትን እነ ገዱ ስማቸውን አናጠለሽም ቢሉ ኦዴፓ ባለው መዋቅር ያስፈፅማል።

ይህ የዲፕሎማሲ ውድቀት ያብቃ ከተባለ ሁሉም የሚችለውን ሊያደርግ የግድ ነው። በዋነኝነት የአዴፓ አሰራር የማይመቸውም ሆነ እምነት የሌለው በአንድ ወቅት የኦሮሞ ምሁራንና ፖለቲከኞች ከማሕበራዊ ሚዲያ እየለቃቀሙ ሲወተውቱ እንደነበረው መኮፈሱን ትቶ መወትወት ይጠበቅበታል። ይህ ትልቁና ዋናው አማራጭ ነው። አዴፓ የአማራውን ሕዝብ በደል በይፋ ለዓለም ለማሳወቅ ድፍረት የሚኖረው ድርጅት አይደለም። በመሆኑም የአማራ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን፣ አክቲቪስቶች ያላቸው አማራጭ ተጠቅመው ስለ አማራው በደል ማሳወቅና መወትወት ነው።

በወልቃይት፣ መተከል፣ ራያ፣ ደራ፣ አዲስ አበባ……የሚፈፀሙትን በደሎች በሶስትና አራት ገፅ አጠቃልሎ ለተቋማት፣ ለፖለቲከኞች፣ ለሚዲያዎች………ማቀበልና መወትወት ምን ያህል ዋጋ የሚያስከፍል ሆኖ ነው? የኦሮሞ ፅንፈኞች የሀሰት ትርክትን ለማስረዳት በሚታትሩበት፣ ምዕራባዊያኑ በአብዛኛው ሀገር ገንቢ ባሕልን እያበረታቱም ወትዋቾቹ ስለመገንጠል ምክንያታዊነት ሲያስረዱ የመኖርና የአካል ደሕንነቱን ስላጣ፣ ዋና እና ዓለም አቀፍ ከተማውን ልንጠቅህ የሚባልን ሕዝብ ጉዳይ ይዞ ዲፕሎማሲ መስራት ምን ያህል ከባድ ሆኖ ነው? ጨፍጫፊና አስጨፍጫፊዎች የሰብአዊ መብት ተሟጋቹንና የተጎጅውን ስም ለማጠልሸት ላይ ታች ሲሉ፣ ስለተበደለ ሕዝብ መወትወት ምን ያህል ከባድ ቢሆን?

ድርጅቶቹ እምነት የማይጣልባቸው እንደመሆናቸው ሁሉም የሚፈፅሙትን፣ በሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን ለዓለም ማሳወቅ ተኪ የሌለው ተግባር ነው። ሆኖም ከድርጅቶቹ መካከል ስግብግብ የሆነው ኦዴፓና አጃቢ ፅንፈኞቹ ጉዳይም በተጨማሪነት ለዓለም ማሳወቅ ይገባል። ይህ ሲሆን ተቋማቱ ውስጥ ባለው ግብ ግብም ሁሉንም ጨፍለቀው ያለፈውን የሕወሓት መንገድ ሊደግሙ አይችሉም። መዘንጋት የሌለበት ሌላኛው ጉዳይ ግን አማራው ተቋማቱንና በልፍስፍሱን ድርጅትም ረስቶ ውጤታማ መሆን የማይችል መሆኑ ነው። የኦሮሞ ብሔርተኞች ተቋማት ውስጥ ካሉ ባለሙያዎችና ተሿሚዎችም ጋር አብረው ሲሰሩ እንደኖሩት ሁሉ አማራውም ተቋማቱንና ባለሙያዎቹን መጠቀም የፖለቲካ ነውር አያመጣበትም። የአማራ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ እና ያገባኛል የሚሉ ሁሉ የአማራውን በደል ለዓለም ሕዝብ ለማሳወቅ የሰቀዛቸውን ስንፍና እና ቸልተኝነት ማቆም ካልቻሉ አማራው በዲፕሎማሲው ባዶ እጁን እንደሚቀረው ሁሉ ተቋማቱ፣ ተቋማት ውስጥ ያሉት ግለሰቦችና ተሿሚዎችን ተጠይፎ የሚያመጣው ለውጥ ምንም ነው። ይልቁን ከእነዚህ አካላት ጋር ተለጥፎ ሳይሆን ለሕዝብ መጠቀሚያ በሚያደርግበት መንገድ መስራት ካልቻለ አማራው ለቀጣይ የአገዛዝ ዘመንም በዲፕሎማሲው ሜዳ ተሸናፊ ሆኖ እንዳይቀጥር ያሰጋል።

የኃያላኑ ቀስት እንደምን ተሰበረ?

በአንድ ወቅት አይደለም ጦር ተሰብቆበት በሠላም ጊዜ እንኳን በሠገነቱ ላይ ከሠፈሩት ርግቦች ላባ ፍላፃን የሚያበጅ፥በጓሮው ከበቀለው የዘንባባ ዝንጣፊ የጦር ሶማያ የሚሰራው አማራ፤ጥቃትን የሚሸከም ትከሻ የሌለው፥በራሱ ባይሆንለት ልጁን ”ደም መላሽ” ብሎ በልጁ ጥቃቱን የሚወጣ አማራ ዛሬ ላይ ጥቃትን አሜን ብሎ መሸከም እንደምን ተለማመደ?የእኛ ያልሆነን የተሸናፊነትንና የተንበርካኪነትን የተገዢነትና የተሳዳጅነትን ቀንበር ለጫንቃችን እንዴት አስተማርነው? ይባስ ብሎ ህልውናችን የቁልቁለት ጉዞውን በአስፈሪ ፍጥነት ሲወርድ እያየን የሚገባንን ያህል ለማድረግ እንዴት ይህ በቂ መነሳሻ /adequate stimulus/ ሊሆነን አልተገባም?

መልሱ በውስጥ እና በውጭ የገጠሙን ተግዳሮቶች /Challenges/ ናቸው የሚል እምነት አለኝ።እነዚህን ውስጣዊ እና ውጫዊ ተግዳሮቶች በትክክል ከለየንና መቅረፍ ከቻልን የአማራ ህዝብ ትግል ፍሬ የማያፈራበት፣አማራነት ወደ ቀደመ ክብሩ የማይመለስበት፣አማራዊም የአባቱን ሀገር ግዮናዊውን የአማራ ሀገር የማይመሰርትበት እና የሚመኘውን እንደሰው የመኖር መብቱን የማይጎናፀፍበት አንዳችም ምክንያት አይኖርም።

 1. ውስጣዊ ተግዳሮቶች /Internal Challenges/፡- ይህ በመወለድ አማራዊ ከሆኑ ከራሳችን ወገኖች የሚመነጩ ተግዳሮቶችን ያካትታል። ሀ. የባሮክ እንቅልፍ /Change Blindness/፡-

በቅዱስ መጽሐፍ ብቻ ሳይሆን በእስራኤል የታሪክ ድርሳናት ውስጥ ከተፃፉት ታሪካዊ ትርክት መካከል የባሮክ ታሪክ አንዱ ነው።ነብዩ ኤርምያስ በነበረበት ዘመን ባሮክ እና አቤሜሌክ የሚባሉ ደቀ-መዛሙርት ነበሩት።ሁለቱም በየዕለቱ ወደ ፈጣሪ ሲፀልዩ ”አቤቱ የኢየሩሳሌምን ጥፋት አታሳየን” ይሉ ነበር።ኤርምያስም ከዕለታት በአንዱ ቀን ሁለቱንም ወደ ተለያየ ቦታ ላካቸው።ባሮክ ከተላከበት ቦታ ሲመለስ የፀሐዩ ንዳድ ይበረታበት እና በአንዲት ዛፍ ስር እንደተጠለለ ያሸልበዋል።እግዚአብሔርም በዚያ ባሮክን ለስድሳ ስድስት /66/ ዓመታት በፅኑ እንቅልፍ ጣለው።ነገር ግን ባሮክ ባሸለበባት በዚያች ቅፅበት የባቢሎን ወታደሮች የኢየሩሳሌምን ቅጥር አፈራርሰው በመግባት ነብዩ ኤርምያስን ጨምሮ እስራኤላውያንን በሙሉ በግዞት ወደ ባቢሎን ወሰዷቸው።

ፀሎቱ ሰምሮለት የኢየሩሳሌምን ጥፋት ያላየው ባሮክ ከረጅም እንቅልፉ እንደተነሳ ለ66 ዓመታት መተኛቱን ስለማያውቅ፤ለውጡንም ስላልተረዳ ያኔ የሚያውቀውን የኢየሩሳሌም መንገድ መፈለግ ጀመረ። ፈልጎም ስላላገኘ ግራ ተጋብቶ እያለ አንድ ሽማግሌ ሰው ያገኝና የኢየሩሳሌም መንገድ በየት ነው? ብሎ ሲጠይቅ ያ አረጋዊ ሰውም ”ኢየሩሳሌም በጠፋች በስድሳ ስድስት አመቷ የኢየሩሳሌምን መንገድ ትጠይቀኛለህን?” አለው።

እኛም ዛሬ እንዲህ እንላለን፡- ከረጅሙ እንቅልፍህ ነቅተህ ”ኢትዮጵያ፣ኢትዮጵያዊነት፣አንድነት…” የምትል አማራዊ ለውጡን አስተውል! ኢትዮጵያ ከጠፋች ዘመናት አልፈዋል።የሸዋ መኳንንት የምኒልክን ሞት ምስጢር አድርገውት አመቺ ጊዜ ሲመጣ ይፋ እንዳደረጉት ሁሉ ወያኔም ኢትዮጵያ የምትላትን ሞቷን በአዋጅ ሊነግርህ አመቺ ጊዜ ብቻ ነው የሚጠብቀው።እንደ ኖህ ዘመን ሰው የጥፋት ውሃ መዝነብ ሲጀምር ነው መርከብ መስራት የምጀምር አትበል።መርከብህ የሆነውን ግዮናዊውን የአባትህን የአማራን ሀገር ለመስራት መነሳት ያለብህ ዛሬ ነው።ኖህ ከጥፋት ውሃ የዳነው መዝነብ ከመጀመሩ በፊት መርከቡን ቀድሞ ስላዘጋጀ ብቻ ነው።

አንድ ስሩ ተቆርጦ የሞተንና የደረቀን ዛፍ አርቲፊሻል ቅጠልና አበባ ብታለብሰው ከሩቅ ለሚያየው ሰው ዛፉ በህይወት ያለ ሊመስለው ይችላል።የዛሬዋ ኢትዮጵያም እንዲሁ ወያኔ ጊዜ ለመግዣ ባለበሳት አርቲፊሻል ቅጠልና አበባ በህይወት ያለች ብትመስልም ዳሩ ከሞተች ዘመናት አልፈዋል። ለመሞቷም ያንተ እጅ ስለሌለበት፡-

        ''ይሆናል ብለን ወፍ አጠመድን፥
        ሳይሆን ሲቀር ግን ፈተን ለቀቅን።'' 

ብለህ ወደ ወገኖችህ ተመልከት።የሞተችውን ኢትዮጵያ በህይወት እንዳለች አስመስሎ በራሱ ምናብ የሚቃዥውን የአማራ ተወላጅም ከሰማህ አንቃው አለበለዚያ ግን ሎጥ ወደ ምትጠፋው ሰዶም እና ገሞራ ዞሮ እንዳላየ ሁሉ አንተም የቅዠቱ ተካፋይ ላለመሆን ዞረህ ሳታይ ሊመጣ ካለው መከራ ለመትረፍ ወደ ተስፋ ምድርህ ወደ ግዮናዊው የአባትህ ሀገር ምስረታ ተሰብሰብ።

        ለ. የሹላማይቷ ሴት ምላሽ /Bystander Effect/፡- 

ጠቢቡ ሰሎሞን ከፃፋቸው መጽሐፎች መካከል በአንዱ ውስጥ የሹላማይቷ ሴትና የወዳጇ ታሪክ ይገኝበታል።

የሌሊቱ ግርማ በሚያስፈራ፣ጠል በሚወርድበት በዚያ ምሽት ሹላማይቷ ሴት በአልጋዋ ላይ ነበረች፤እንቅልፍ ግን አልወሰዳትም።ካስፈሪው ጨለማ፣ከሚወርደውም ጠል ለመጠለል ወዳጅዋ የሆነው ሰው የቤቷን መዝጊያ እያንኳኳ ልብን በሚነካ ቃል ”እኅቴ፥ወዳጄ፥ርግቤ፥መደምደሚያዬ ሆይ፥በራሴ ጠል፥በፀጉሬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ።” እያለ ሲማፀናት ከወዳጅ የማይጠበቀውን ምላሽ እንዲህ ስትል ትመልስለታለች፡- ”ቀሚሴን አወለቅሁ፤እንዴት እለብሰዋለሁ?እግሬን ታጠብሁ፤እንዴት አሳድፈዋለሁ?”

ተልካሻ ምክንያት እየደረደረች እንደማትከፍትለት ያወቀው ሰውም ራሱን ለማትረፍ ሲል እጁን በበሩ ቀዳዳ አሾልኮ ለመክፈት ሞከረ፤አልሆንለት ሲልም ተስፋ ቆርጦ ሄደ።እሷም ጅብ ከሄደ ውሻ… እንደሚባለው እንዲህ ትላለች ”አንጀቴም ስለ እርሱ ታወከ።ለውዴ እከፍትለት ዘንድ ተነሣሁ፥ውዴ ግን ሄዶ ነበር።ነፍሴ ከልመናው ቃል የተነሳ ደነገጠች፤ፈለግሁት፥አላገኘሁትም፤ጠራሁት አልመለሰልኝም።ከተማይቱን የሚዞሩ ጠባቂዎች አገኙኝ፤መቱኝ፥አቆሰሉኝም……” እያለች ከረፈደ በኋላ ነገሮችን ለማስተካከል ስትሞክር አልሰምር እያለ እንዴት ዋጋ እንዳስከፈላት ትናገራለች።

አማራዊ ሆይ!ዛሬ ወገንህ አማራ በመሆኑ ብቻ የቀን ጨለማ ውጦት፤የመከራ ዶፍ እየወረደበት አንተ ልጁ ከሚያሳድዱት እንድታስጥለው መሸሸጊያ ቤቱን እንድትከፍትለት በደጅ ቆሞ እየተማፀነህ ነው።ዛሬ ልትደርስለት ሲገባ ”ቀሚሴን እንዴት እለብሳለሁ?፤እግሬንስ እንዴት አሳድፋለሁ?” በሚል ተልካሻ ምክንያት የወገንህን ሰቆቃ ችላ ብትል ዛሬ ወገንህን እያጠፉ ያሉት ነገ አንተንው እንደ ሹላማይቷ ሴት ያጠፉሃል።

አማራዊ የሆንክ የወገንህ ጥቃት ያንተም ጥቃት ነው።ከዳር ሆነህ በወገንህ አጥንት እና ስጋ እየነደደ ያለውን እሳት የምትሞቅበት ወቅት ማብቂያው አሁን ነው።ከዳር ሆነን የምናይበት ጊዜ ሊያበቃ ግድ ነው።አንዱ አማራዊ ስለሁሉ አማራዊ፥ሁሉ አማራዊም ስለ አንዱ አማራዊ የሚቆምበት ጊዜ ዛሬ ነው።በአማራዊነትህ ተነስ፥የወገንህ ጥቃት ያስቆጣህ!

       ሐ. ራስን አግዝፎ የማየት አባዜ /Delusion of Grandeur/፡- 

ባለፈው ሰሞን አንድ የዳያስፖራ ቴሌቪዥን ጣቢያ በአማራ ጉዳይ የሚሰሩ ግለሰብን ቃለ-ምልልስ ሲያደርግ እያየሁ ነበር።እናም ጋዜጠኛው ”ለምንድነው አማራ የራሱን ሀገር መመስረት አለበት የምትሉት?፤ከትግሬ ውጪ ሁሉም አማራን ይፈልገዋል እንዲያውም ደቡብ እኮ አማርኛ ቋንቋን ነው የሚጠቀም” እያለ ጉንጭ አልፋ ክርክር ሲያደርግ ሳይ ምርጫ 97 ነው ወደ አዕምሮዬ የመጣው።በምርጫው ማግስት ቅንጅት የሚባለው ድርጅት ፓርላማ እንግባ አንግባ እያለ ሲወራከብ ህብረት የሚባለው ድርጅት ሊቀመንበር የሀድያ ተወላጁ በየነ ጴጥሮስ በአ.አ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበረውን ዶክተር ተጠምቀ የተባለውን ትግሬ ከስዩም መስፍን ጋር ካላገናኘኸኝ ሞቼ እገኛለሁ ይለዋል።ዶክተሩም አገናኘው።በየነስ ስዩምን ምን አለው? ”ስልጣናችሁን ለአማራ አሳልፋችሁ እንዳትሰጡ፤እኔ መረራን አሳምኜ ህብረት ፓርላማ እንዲገባ አደርጋለሁ።” አለ።አደረገውም። እንግዲህ ኦሮሞዎቹ ብርትኳን ሚደቅሳ፣ዶ/ር አድማሱ እና በግማሽ ሀይሉ ሻውል፤ጉራጌዎቹ ዶ/ር ያዕቆብ እና ብርሃኑ ነጋ፤ትግሬው ኃይሉ አርአያ በበላይነት የሚመሩትን ቅንጅትን ነው እንግዲህ በየነ አማራ እንዳይመጣብን ብሎ አቧራ ያስነሳው።

እውነት ደቡቡ አማራን የሚፈልግ ቢሆን ገፍፎ እና ዘርፎ ከወያኔ ጋር በማበር ከክልሉ ያባርረው ነበር? ይህ ”ሌሎች ይወዱኛል፤ሌሎች ይፈልጉኛል” የሚል አባዜ ስር የሰደደ ችግር እንጂ የአንድ ጋዜጠኛ ችግር ብቻ አድርገን አንውሰደው።

አማራዊ የሆንክ ከእንደዚህ አይነት የቀን ቅዠት ውጣ!ካንተ ከአማራዊ ወገንህ ውጪ ማንም አይፈልግህም።ሊፈልግህ ቢችል እንኳ በሁለት እግርህ ራስህን ችለህ ስትቆም እንጂ ዛሬ ዛፍ እንዳጣ አሞራ እየተቅበዘበዝክ፣እየተሳደድክ እና በየጎዳናው እየታደንክ ባለህበት ሁኔታ አይደለም። አማራዊ ሆይ በመጀመሪያ ራስህን አድን፣ቤትህን ስራ ማረፍያህን አዘጋጅ።ላለፉት ሃያ ስድስት አመታት ያሳለፍከው የመከራ ተሞክሮ የሚያሳይህ ሌሎች በቁስልህ ላይ ጥዝጣዜን ሲጨምሩብህ እንጂ ቁስልህን የሚጠርግ አንድም ሳምራዊ አላገኘህም። ”ሌሎች ይወዱናል፤ሌሎች ይፈልጉናል” በሚል የቀን ቅዠት የሚዋልለውን ወገንህን በተቻለህ መጠን አንቃው፥መራራውን እውነት እንዲያይ እርዳው።አሻፈረኝ ካለህ ግን ራስህን ለይ እና ወደ አማራዊ ወገኖችህ፥ወደ ወጣህበት መንጋ ተቀላቀል።

              መ. ራስን መካድ /Self-Denial/:-

አንድ የወይን እርሻ የነበረው ሰው ነበረ።እንዲህም አደረገ ”በዙሪያው ቆፈረ፥ድንጋዮችንም ለቅሞ አወጣ፥ምርጥ የሆነውንም የወይን ሐረግ ተከለበት፥በመካከሉም ማማ ሰራ፥ደግሞም የመጥመቂያ ጉድጓድ ማሰበት፤ወይንንም ያፈራ ዘንድ ተማመነ፥ዳሩ ግን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ።”

ትናትናም ይሁን ዛሬ አማራዊ አባት ልክ እንደ የወይን እርሻው ባለቤት ሁሉን አድጎላቸው ከፍ ካለ ማማ ላይ የሰቅሏቸው ልጆቹ በምላሹ ጣፋጭ ወይንን ከማፍራት ይልቅ ራስን በሚያስክድ አባዜ ተጠልፈው መራራን ነገር ሲያፈሩ ታዝበናል፤እየታዘብንም ነው።

ትናንት የአማራ ህዝብ እረኛ እንደሌለው መንጋ በማንም ተኩላ እየተነጠቀ እየታረደ በነበረበት ወቅት ጥቃትህ ጥቃቴ ነው ብሎ እንደምሁር መንጋውን መምራትና ማደራጀት ሲገባው ”ጥናት አጥንቼ ደረስኩበት” ባለው ሸውራራ ዕውቀቱ እየተገፋ ”አማራ የሚባል ነገር የለም” እያለ የአራጆቻችንን ቢላ ሲስል አይተናል።ትናንት ትግሬ ተራበ ብሎ አኮፋዳ ሸክፎ በየሀገሩ እየዞረ ደጅ እንዳልጠናላቸው በምርጫ 97 ማግስት መምህር ገብረኪዳን ደስታ የሚባለው የትግሬ ፀሐፊ በአማርኛ ባሳተመው ፀረ-አማራ መጽሐፉ ላይ በፕሮፌሰሩ ላይ እንዲህ እያለ ነበር መርዷቸውን ያረዳቸው ”ሂትለር ከአይሁዳዊት ሴት ልጆች ቢወልድ የአይሁዶች ለሂትለር ያላቸው አመለካከት እንደማይቀየር ሁሉ፤ፕሮፌሰር መስፍን ከትግራይ ሴት ልጆች ስለወለደ ጠላቱን ጠንቅቆ የሚያውቀው የትግራይ ህዝብ ለፕሮፌሰሩ ያለውን አመለካከት አይቀይርም።” ነበር ያለው።

ዛሬም የፕሮፌሰሩ መንፈስ የተጠናወታቸው ራሳቸውን የካዱ አማራውያን በሚዲያዎቻቸው አማራ ተፈናቀለ ከማለት ይልቅ ”አማርኛ ተናጋሪ ህዝቦች ተፈናቀሉ” ይላሉ።የአማራ ታጋዮች ከማለት ይልቅ ”የነፃነት ኃይሎች” ይላሉ።

እስኪ የሚሉትን በሌላ ምሳሌ እንየው።የራሽያ ቋንቋ ሩስኪ ይባላል።ይህን ቋንቋ ከራሽያ ጀምሮ የማዕከላዊ ኤዥያ ሀገራት የሆኑት ካዛኪስታን፣ኡዝቤክስታን፣ቱርክሜንስታን፣ታጃኪስታን፣ኪርጊስታን እንዲሁም የካውካሰስ ሀገራት የሆኑት አዘርባይጃን፣ጆርጂያ እና አርሜንያ ወደ ላይ ደግሞ የቦልቲክ ሀገራት የሆኑት ሌቲቪያ፣ኢስቶንያ፣ሉቶንያ እና ቤላሩስ እንዲሁም የምስራቅ አውሮፓዎቹ ሞልዶቫ እና ዩክሬን ይናገሩታል።ይባስ ብሎም ግማሽ የሚሆነው የእስራኤል ህዝብ ከእነዚህ ሀገራት ወደ እስራኤል የተመለሰ በመሆኑ ሩስኪን አቀላጥፎ ልክ እንደራሻዎቹ ይናገራል።ታድያ አንዱ ተነስቶ ፑቲን ሩስኪ ተናጋሪ ህዝቦችን እየበደለ ነው ቢል ምን ትርጉም ይሰጣችኋል?ትርጉም የሚኖረው ፑቲን የራሽያ ህዝብን እየበደለ ነው ቢባል ነው።ምክንያቱም ሩስኪ የሚናገሩ ህዝቦች ሁሉ በፑቲን አስተዳደር ስር ያሉ ስላልሆኑ። በአማራ ህዝብ እና በአማርኛ ተናጋሪ መካከልም ያለው ልዩነት እንዲሁ ነው።አማራዊ ዜጎቻችን ሲበደሉ የአማራ ህዝብ ብሎ ከማለት ይልቅ አማርኛ ተናጋሪ ህዝቦች እያሉ የሚያናፍሱ የራሳችን ሰዎች በህዝባችን ላይ ተደጋጋሚ ክህደትን እየፈፀሙ እንዳለ ሊታወቅ ይገባል።

አማራዊ የሆንክ ወገናችን!ሌላውን አስደስታለሁ ወይ እጠቅማለሁ ብለህ ራስህንና ወገንህን ክደህ ስለሌላው ብትሞት፣አይደለም ቆዳ ተሸክመህ ለጠኔያቸው ማስታገሻ ምግብ መለመን ቀርቶ ቆዳህን እንኳን ገፈህ ብታነጥፍላቸው ላንተ ያላቸው ጥላቻ እና ንቀት መቼውንም አይቀየርም።መቼውንም!!!

ፕሮፌሰሩ በትግሬ ህዝብ ዘንድ እንደባለውለተኛ ሊመሰገኑ ሲገባ ከሂትለር ጋር እንዴት እንዳመሳሰሏቸው ትምህርት ይሁንህ።አበበ ገላው የሚባለው ጋዜጠኛ /አማራ ማለት ከብዶት አማርኛ ተናጋሪ፣የነፃነት ኃይሎች የሚለውን ተቋም በበላይነት የሚመራው/ ጃዋርን አጋር ያደረገ መስሎት ሚኒሶታ ድረስ ሄዶ እጆቹን እያመሳቀለ ”ዳዎን ዳዎን ወያኔ” ሲል ቢውልም አመሻሹ ላይ ጃዋር በራሱ ቋንቋ አበበን እንዴት በማጅራቱ በኩል እንዳረደው ትምህርት ይሁንህ።ገንዘብህን፣ዕውቀትህን፣ጊዜህን ለአማራ እና ለአማራ ብቻ አውል!ራስህን አክብር፤ያንተ የሆነን ነገር ዋጋ ስጠው!ከልጅነት ጀምሮ ወይንን እንድታፈራለት ተንከባክቦ ላሳደገህ አማራዊ ዜጋ ወይን ነህና ጣፋጭ ወይንን አፍራ!!!

     ሠ. የኤማሁስ መንገደኞች /Day-Dreamers/፡- 

ክርስቶስ ከሞት በተነሳበት ዕለት እንዲህ ሆነ።ከተከታዮቹ ሁለቱ ከኢየሩሳሌም አቅራቢያ ወደምትገኝ ኤማሁስ ወደምትባል ስፍራ መንገድ ጀመሩ።ክርስቶስም ሌላ መንገደኛ መስሎ ቀረባቸው እና የሚያወሩትን ሲሰማ ስለምን እንደሚናገሩ ጠየቃቸው።እነሱም ስለሱ የሆነበትን ሁሉ ከነገሩት በኋላ ለዚህ ርዕስ የሚስማማውን ነገር ተናገሩ፡- ”እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤…. ።”
ያሉትን ነገር ይበልጥ ግልጽ ላድርገውና በወቅቱ እስራኤል መንግስቷ ፈርሶ በሮማውያን ቅኝ ተይዛ ነበር።እናም እነሱ የሚያስቡት ሮማውያንን አባሮላቸው እስራኤልን ነፃ ሀገር እንዲያደርግላቸው ነበር።ፈጣሪ ያሳያችሁ ሶስት ዓመት ሙሉ ስለ ሰማያዊው የእግዚአብሔር መንግስት እና ለመንፈሳዊ ተልዕኮ እንጂ ምድራዊ የሆነውን ስራ ለመስራት እንዳልመጣ ሲያስተምራቸው ቢኖርም የነሱ ሃሳብ እና ፍላጎት ግን ሌላ ዓለም ውስጥ ነበር ያለው።

ይህ እጅና እግርን አጣምሮ ፈጣሪ ያደርገዋል የሚል አመለካከት በእስራኤላውያኑ ዘንድ ስር የሰደደ ችግር ስለነበር ለ ሁለት ሺህ አመታት ሀገር አልባ ሆነው እንዲንከራተቱ አድርጓቸዋል።ነገር ግን በ1897 ዓ.ም. የጽዮናውያን እንቅስቃሴን ሲጀምሩ ፈጣሪም ረድቷቸው 50 ዓመት በሆነ ጊዜ ውስጥ መንግስት መመስረት ቻሉ።

እኔ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን እንደሆንኩት ሁሉ ሌላው አማራዊም የሚፈልገውን እምነት ቢከተል ችግር የለውም።ነገር ግን የራሳችንን የስራ ድርሻ ዘንግተን ፈጣሪ እንዲያከናውንልን መጠበቅ ፍፁም ስህተት ነው።

ውሃውን በበትር የመታው ሙሴ ነው፤ለሰው የማይቻለውን ባህሩን የከፈለው ግን ፈጣሪ ነው።የአልዓዛርን የመቃብር ድንጋይ ሰዎች እንዲያነሱት ነው የተደረገው፤ለሰው የማይቻለውን አልዓዛርን ከሞት ያስነሳው ግን ክርስቶስ ነው። እኛ የራሳችንን ድርሻ ማንሳት ከቻልን የማንም ዕንባ ባለዕዳ ያልሆነው ፈጣሪያችን በነፃነት እንድንኖር ለምናደርገው የነፃነት ትግል እንደሚረዳን ምንም ጥርጣሬ ሊገባን አይገባም።

የአማራ ህዝብ የሞራል ልዕልና እንዲኖረው ካስቻሉት ነገሮች አንዱ እምነት ያለው ህዝብ መሆኑ ነው።ነገር ግን እስራኤላውያን ለሁለት ሺህ አመታት የሰሩትን ስህተት ላለመድገም ቀን ከሌሊት ከእኛ የሚጠበቀውን ማድረግ እና የድርሻችንን ማንሳት ይኖርብናል።

         ረ. የዋለልኝ ፍሬዎች /Self-hate Amharas/፡-

”ስም ይወጣል ከቤት፥ይቀበላል ጎረቤት” የሚል በሳል ብሂል አለን። ”የኢትዮጵያ አብዮት ” እየተባለ በሚጠራው የስልሳዎቹ ትውልድ ውስጥ ዋለልኝ መኮንን የተባለው ራስ-ጠል አማራ በኢትዮጵያ ውስጥ የብሄር ጭቆናና የአማራ የበላይነት እንዳለ በማስመሰል ያሰራጨው መርዛማ ጽሑፍ ዛሬ ድረስ ለዘለቀው አማራንና አማራዊን ለማጠልሸት መሠረት የጣለ ነበር።መጽሐፍ የዋለልኝ አይነቱን ወገኑን የሚጠላውን ”አባቱን የገደለ፤እናቱን ያገባ፤ጌታውን የሸጠ የጥፋት ልጅ ” ይለዋል።

ዛሬም የዋለልኝ ፍሬዎች በማህበረሰባችን ውስጥ ተሰግስገው ጠላት ከሚወጋን በላይ ትልቅ ጥፋት በህዝባችን ላይ እየፈጸሙ ይገኛል።

ትናንት ሶማሌው አማራዊውን እንዲገድለው ሲቀሰቅስ የነበረው የትናንቱ ጠቅላይ ሚንስቴር የዛሬው ፓስተር ነኝ ባይ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

ትናንት የገዛ ወገኑ ተገፎ እና ተዘርፎ ሲባረር ሳያሳስበው ”እንዳይባረር የትምክህት ለሀጩን መጥረግ አለበት” ፣” አማራ በባዶ እግሩ እየሄደ…..” እያለ በቁስላችን ላይ እንጨት የሰደደው አለምነው መኮንንም የበጣም ቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

ከሰሞኑ ደግሞ በኖርዌይ እሱና ቤተሰቦቹ በመንግስት ዌልፌር እየተጦረ የሚኖር ዶክተር ነኝ ባይ በአማራ ሀገር ምስረታ ዙሪያ የሚሰሩትን ”የአማራ ኦነጎች” እያለ የጭቃ ጅራፉን ሲያጮህ ሰምተናል።እርግጥ ነው ቀበቶውን አላልቶ ቀፈቱ እስኪሞላ የዌልፌር ምግብ ሲበላ የኖረን ሰው የወገኑን ጥቃት ለማስቆም እጅጌህን ሰብስብ፥ቀበቶህንም አጥብቅ መባልን አይሻም። ”ውሃን ምን ያስጮኸዋል? ቢሉ፥በውስጡ ያለው ድንጋይ” ይባል የለ!

አማራዊ ሆይ! በሥነ-ቃልህ ውስጥ፡-
”ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው፤
አስቀድሞ ማለት አሾክሿኪውን ነው።” የሚል አባባል አለህ። ስለሆነም ከአብራክህ ወጥቶ፥ማዕድህን በልቶ ካደገ በኋላ ከጠላቶችህ ጋር የሚጠላህን፣መንገድ መሪ ሆኖ ጥፋትህን የሚያፋጥነውን እሱን አስቀድመህ አጥፋው።ከማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ህይወት ሁሉ አግልለው።በሀዘኑም በደስታውም አትካፈል፤በሀዘንህ እና በደስታህም እንዲካፈል አትፍቀድለት።

እንግዲህ የውስጥ ተግዳሮቶችን ያየንበትን የዛሬውን ፅሑፍ በዚህ እንቋጭ።በቀጣይ ውጫዊ ተግዳሮቶችን እና መደምደሚያውን እናያለን።

እግዚአብሔር ግዮናዊውን የአማራ ሀገር ይባርክ!!!አሜን።

ዴቭ ዳዊት።(Dave Dawit)

የኃያላኑ ቀስት እንደምን ተሰበረ?


/ክፍል ሁለት/

/የአማራ ህዝብ ለባህርይውም ይሁን ለማንነቱ ፈፅሞ እንግዳ የሆነ ጥቃትን የመሸከም ስብዕናን እንዲለማመድ ያደረጉትን ውስጣዊ ተግዳሮቶች በክፍል አንድ ማየታችን ይታወሳል። ይሁን እንጂ ወደ ውጫዊ ተግዳሮቶች ከመሸጋገራችን በፊት ሳይጠቀስ መታለፍ የሌለበት ቁልፍ ውስጣዊ ተግዳሮት በመኖሩ ክፍል ሁለትን በዚህ ዙሪያ በማተኮር እንጀምራለን።መልካም ንባብ።/

       ሰ. የሰመርናሃ ሰፋሪዎች /The Amhara Elites/:- 

እንዲህም ሆነ። እስራኤል በባቢሎን ለሰባ ዓመታት በባርነት ከሚኖርበት ግዞት ሊወጣ ሲቃረብ ነብዩ ኤርምያስ እስራኤላውያን ጣዖትን ከሚያመልኩ ባቢሎናውያን ጋር ጋብቻን እንዳይፈፅሙ፤ የፈፀሙትም እንዲያፈርሱ ያስተምር ነበር። ጣዖት አምላኪዎች ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዳይገቡ የተከለከለ ነበርና። ጊዜው ደርሶ እስራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለስ ኤርምያስና የጎበዝ አለቆቹ በኢየሩሳሌም በር ቆመው ከባቢሎናውያን ጋር የተጋቡትን እንዳይገቡ ከለከሏቸው። ከባቢሎንም ከኢየሩሳሌምም የተባረሩት እነዚህ ሀገር አልባ ሰዎች እግራቸው ወደመራቸው ሲጓዙ አንድ ስፍራ አገኙ። በዚያም ሰፈሩ። የቦታውንም ስም ”ሰመርናሃ” ብለው ጠሩት፥ በኋላም ያ ስፍራ ሰማርያ ተባለ። የሰማርያ ሰዎች በወገኖቻቸው ላይ ክህደትን ፈጽመዋልና፤በባርነት ካስገበሯቸው ባቢሎናውያን ጋር ተዛምደዋልና ከጣኦት አምላኪዎች ጋርም ተጋብተዋልና በአይሁድ ዘንድ እጅግ የተናቁ ነበሩ።

ዛሬም እንዲሁ ለቁጥር አታካች የሆነው የአማራ ልሂቅ ”አንድነት” ከምትባል ወገኖቻችንን በግፍ እንዲጨፈጨፉ ምክንያት ከሆነች ጋለሞታ ጋር በቀላሉ የማይፋቱት ጋብቻ ፈፅመው የእነሱ አቻ የሆኑቱ የሌሎች ብሄሮች ልሂቃን ጊዜያቸውን፣ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን ለወገኖቻቸው ከማዋል አልፈው በመሰሪ ተግባራቸው አማራዊ ወገኖቻችንን ለማጥፋት ሲጠቀሙበት የእኛዎቹ ግን ለራሳቸው ሀገር አልባ፥ ለወገናቸው ዕዳ፥ለትውልዱም ማፈሪያ ሆነዋል። በዚህም ምክንያት አማራዊ ወገናችን እንዳልወለደ፣እንዳላስተማረ፣”እደጉ፥ተመንደጉልን” ብሎ እንዳልደገፈ ሁሉ የወላድ መካን ሆኖ ሲሳደድ እና ሲገደል፣በግፍ ከነነብሱ በቀበሮዎች ጉድጓድ ሲቀበር፣ማረፊያ አጥቶ ሲቅበዘበዝና የሰው ልጅ ይሸከመዋል ተብሎ የማይታሰብ ግፍ እና መከራ ሲደርስበት የአማራ ልሂቃኑ ግን ወያኔ ከዘመናት በፊት የገደላትን ኢትዮጵያ የሙት መንፈሷን ጣዖት በማምለክ፥እንዲሁም የአመንዝራይቱ ኤልዛቤል ምሳሌ ከሆነችው ከ”አንድነት” ጭን ውስጥ መውጣት ባለመቻላቸው ህዝባችን ለባህርይው የማይስማማውን ጥቃት እና በደልን እንዲሸከም ትልቅ አስተዋፆ አበርክተዋል።

ዶክተር መረራ ጉዲና ”የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምስቅልቅል ጉዞና የህይወቴ ትዝታዎች (ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ እስከ ኢህአዴግ)” በተሰኘ መፅሀፉ የሌሎች ብሄር ልሂቃን በአማራ ልሂቃን ላይ ሁለት ጊዜ ክህደት እንደፈፀሙበት ይጠቅሳል። በ66ቱ አብዮት ማግስት እና በደርግ ውድቀት ማግስት ማለት ነው። በነዚህ ሁለት ወሳኝ ወቅቶች የሌሎች ብሄር ልሂቃን ”አጥብቀህ ጎርሰህ፥ወደ ወገንህ ሩጥ” የሚለውን ብሂል ተግባራዊ ሲያደርጉ የአማራ ልሂቅ ግን ከባቢሎንም ከኢየሩሳሌምም ሳይሆን እንደውሃ ላይ ኩበት ሲዋልል መሠረቱ የሆነውን የገዛ ወገኑን ለፈፅሞ ጥፋት እንዲጋለጥ አድርጓል።

በእኔ እይታ በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የአማራ ልሂቅ በአራት መጥፎ እና አደገኛ ምድብ ውስጥ ተከፍሎ ይገኛል።

       1ኛ. ክህደት ምሱ /The Ignorant Elites/፡- 

          ''ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፍጣል?''

በእንግሊዝኛ አንድ አባባል አለ ”Fool me once, shame on you; fool me twice, shame on me!” እውነት ነው! ማንነትህን አስቀድሜ ላውቀው ባለመቻሌ ለመጀመሪያ ጊዜ ብታታልለኝ ቅሌታሙ አንተ ነህ! ለሁለተኛ ጊዜ እንድታታልለኝ ከፈቀድኩልህ ግን በእርግጥም ቂሉ እኔ ነኝ።

አማራዊ ልሂቅ ሆይ! ከአንዴም ሁለት ጊዜ አንተ ”አንድነት”፣”ኢትዮጵያ” እያልክ አብዝተህ ስትጣራ ለጊዜው ካንተ ጋር የቆሙ የመሰሉህ፥በመጨረሻው ግን አጥብቀው ከፊትህ ሸሽተው አንተን እና የወጣህበትን አማራዊ ወገንህን በጠላትነት በመፈረጅ ክህደት ፈፅመውብሃል፤ ወገንህን ካላጠፉ ዕረፍት ላያገኙ ተማምለውም ዳግም ክደውሃል።

ከሃዲዎች በመጀመሪያው ክህደት አንተን እና አማራዊ ወገንህን በጠላትነት ፈረጁ። በሁለተኛው ክህደት የህዝብህን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ መሠረቱን ንደው የቻሉትን ገድለው ያልቻሉትን አሳደው ካሉት በታች፥ከሞቱት በላይ ሆኖ እንዲቅበዘበዝ አደረጉት። ዛሬ ራስህን ለሦስተኛ ክህደት ካመቻቸህላቸው አንተንም ሆነ የወጣህበትን ህዝብህን እንደ ነጣቂ መብረቅ፥እንደ ተራበም ተኩላ ሊናጠቁህ ፈፅሞም ሊያጠፉህ አሰፍስፈዋል።

ታዲያ ከሃዲዎቹ እንደ ጴጥሮስ ከሶስት ጊዜ ክህደት በኋላ በንሰሐ ይመለሳሉ ከሚል የቂል ምኞት ማማ ላይ ራስህን ሰቅለህ እስከመቼ ትኖራለህ? ያንተ ስህተት እኮ ዕንቁዎችህን በእሪያዎች መካከል ማኖርህ ነው። ያንተ ስህተት ውሾቹ ቅዱሱን በእግራቸው እንዲረግጡት፥ተመልሰውም እንዲነክሱህ የተቀደሰውን ነገር ለውሾች መስጠትህ ነው። ዛሬ ግን በቃ ልትል ግድ ይላል።

አንተ እኮ በተፈጥሮህ አልጫውን የምታጣፍጥ ጨው ነበርክ። ከሃዲዎች ድንጋይ ነው ብለው ወደ ውጪ የጣሉህ የወጣህበትን አማራዊ ወገንህን ትተህ፥ያለተፈጥሮህ አልጫ ሆነህ ስለተገኘህ ብቻ ነው። አንተ እኮ በተፈጥሮህ ጨለማን የምትገላልጥ ብርሃን ነበርክ።በአማራነት መቅረዝ ላይ ከፍ ብለህ ልታበራ የተፈጠርክ ብርሃን እንጂ ከሃዲዎች እንቅብ የሚደፉብህ የጋን ውስጥ መብራት አልነበርክም። ከማንነትህ ጋር የምትታረቅበት፣ ወደ አባትህ ቤት የምትመለስበት፣ ለአማራዊው ወገንህም ጋሻ ሆነህ የምትቆምበት ጊዜ ዛሬ ነው።

አንተ የተኛህ አማራዊ ልሂቅ ንቃ!!! እንደ አቻዎችህ አንተም ዕውቀትህን፣ ጊዜህን እና ገንዘብህን ለአማራዊ ወገንህ አውል!!! ወትሮም ኮትኩቶ ዛሬ ለደረስክበት ዕልቅና ያደረሰህ አማራዊ ወገንህ ነው፤ ደግሞም መደበቂያ የሚሆንህ ከጥፋትም የምትድንበት የመሸሸጊያ ምድርህ ይኸው የአባትህ ርስት ግዮናዊው የአማራ ሀገርህ እንጂ ከሃዲዎቹ ያፈረሷት እና ከአዕምሮህ አልጠፋ ያለችው የምናብህ ኢትዮጵያ አይደለችም።

            2ኛ. የይሁዳ ፍየሎች /The Judas goat/

የይሁዳ ፍየል ማለት በተለይ በምዕራቡ ዓለም ከብት አርቢው ከመንጋው መካከል አንዱን ፍየል ነጥሎ ይወስደውና ሌሎቹን ፍየሎች ወይም በጎች ሳይበታተኑ ከፊት ከፊት እየመራ ባለቤቱ ወደሚፈልግበት ቦታ እንዲወስዳቸው ያሰለጥነዋል። አብዛኛውን ጊዜ የይሁዳ ፍየል መንጋውን እየነዳ የሚወስደው የበጎቹ ፀጉር ወደሚሸለትበት ቦታ አልያም በጎቹ ወደሚታረዱበት ስፍራ ሲሆን የይሁዳው ፍየል ራሱን ከመንጋው ጋር በማመሳሰል ተራ በተራ መንጋውን ወደመታረድ እየመራ የደም ምንዳ ይሰፈርለታል።

እንዲሁ ዛሬ ከአማራ ልሂቃኑ መካከል ጥቂት የማይባሉት አፋቸው ከእኛ፥ልባቸው ግን ከእነኛ ሆኖ አንድ የሆነውን የአማራን ህዝብ አራጆቻችን በሚፈልጉት መልክ በመንጋ በመንጋ እየከፋፈሉ እና ከፊት ሆነው እየመሩ ለሸላቶች እና አራጆች ቢላ እያመቻቹን ይገኛሉ።

መለስ ዜናዊ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 2010 ዓ.ም. በፓርላማ ተገኝቶ ከደቡብ ክልል በግፍ ስለተፈናቀሉት አማራውያን ቃል በቃል እንዲህ ነበር ያለው ”አማራ ተፈናቀለ እየተባለ የሚባለው መሠረት የሌለው ነው። እነዚህ ሰዎች የምስራቅ ጎጃም ሰዎች ናቸው። በሞፈር ዘመት ሄደው የሰፈሩ የምስራቅ ጎጃም ሰዎች ናቸው…………………………………….።” መለስ የሚናገረውን የማያውቅ ሰው ሆኖ አይደለም ”አማራ ሳይሆኑ ሞፈር ዘመት የምስራቅ ጎጃም ሰዎች ናቸው” ያለው በወቅቱ ቢሳካለት ሌላው አማራ የተሰደዱትን ሰዎች የምስራቅ ጎጃም ሰዎች እንጂ የእኔ አካባቢ ሰዎች አይደሉም ብሎ እንዲያስብለት ከመመኘት ነው። በተመሳሳይ ዛሬ አማራዊው የአማራ ተወላጅ በመሆኑ ብቻ የግፍ ዶፍ እየወረደበት ሳለ የይሁዳ ፍየሎች ግን ከአሳዳሪዎቻቸው በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት ”የጎንደር ህብረት”፣ ”የጎጃም ህብረት” እያሉ አማራዊው በአንድ ጥላ ሥር እንዳይሰባሰብ እና የተጋረጠበትን የፈፅሞ መጥፋት አደጋ አንድ ሆኖ እንዳይከላከል ትልቅ ዕንቅፋት ሆነዋል።

አማራዊ ሆይ! ጎጃም፣ጎንደር፣ወሎ እና ሸዋ የአንተ ወይም የወላጆችህ የትውልድ ስፍራ እንጂ የአንተ ማንነት አይደለም።አንተ ደምህ አማራ ነው!!! ጥቃት የተከፈተብህ ደምህ አማራዊ ስለሆነ ብቻ ነው!!! ጎጃምም ተወለድ ጎንደር፤ ወሎም ተወለድ ሸዋ ጠላት አንተን የሚያውቅህም ሆነ የሚጠራህ አማራ ብሎ ነው!!! አንተን አማራነትህን አስክዶ በትውልድ ቦታ ሊከፋፍልህ እየሞከረ ያለው የይሁዳ ፍየል አንተን መስሎና አንተን አህሎ በመሳም ለአሳዳጆችህ አሳልፎ ሊሰጥህ የደም ምንዳ ተከፍሎታል። በቁምህ ሸጦህ የደም መሬት አኬልዳማ ገዝቶበታል።

አማራዊ ሆይ! አንተ እኮ ትልቅ ህዝብ ነህ። አንተ እኮ በህግ የተወለድክ የእመቤቲቱ የሳራ /የጣይቱ/ ልጅ ነህ። ያለህግ የተወለደው የገረዲቱ አጋር ልጅ ፥ ያ ከሃዲ በትውልድ ስፍራ ሊከፋፍልህ ሲነሳ፤ ከጠላትህ ጋር በምስጢር ወግኖ ሊያጠፋህ ሲያደባ አንተም በምላሹ ”በቃ! ገና ከበለስ በታች ሳለህ የይሁዳ ፍየል መሆንህን አወቅሁ” ልትለው ይገባል።

እናንት የአማራ ልጆች! ጠላት አንድ የሆነውን የአማራን ህዝብ በትውልድ ስፍራ ከፋፍሎ ለማጥፋት ያመቸው ዘንድ በይሁዳ ፍየሎች ፊታውራሪነት ያዘጋጃቸውን ”የጎንደር ህብረት”፣ ”የጎጃም ህብረት” የሚባሉ የጠላት የመውጊያ ዘንጎችን ሰባብሩ!!! ንሑሩሽታን /ሰባብሩት/!!!

        3ኛ. የሌሊት ወፎች /The Tepid-Water Effect/

”በራድ ወይም ትኩስ እንዳልሆንክ ስራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንክ ከአፌ ልተፋህ ነው።”

የሌሊት ወፍ ከበራሪ እንስሳ ወገን እንዳትባል አጥቢ ናት፤ ሙሉ በሙሉ ከአጥቢ እንስሳ ወገን እንዳትባልም ሌላው ተፈጥሮዋ ሁሉ እንደ በራሪ እንስሳ ነው። ብቻ የሁለት ዓለም ፍጡር!

ዛሬም እንዲሁ በቁጥር ቀላል የማይባል የአማራ ልሂቅ ቀን ቀን ”አማራ የተደቀነበት አደጋ የፈጽሞ መጥፋት አደጋ ነው” ሲል ይውል እና ሌሊት ላይ ”አንድነት” የምትባለዋን የሌሊት ልብሱን ደርቦ ያውም ገና ፍትህ ያላገኘውና ዛሬም ወደ ራማ እየጮኸ ያለው የአማራ ህዝብ ደም በእጃቸው ላይ ካለ ሰዎች ጋር ፖለቲካዊ መዳራትን ይፈጽማል። ይባስ ብሎም ቀን ላይ የነገረህን ትቶ ”ሁሉም ብሄር በወያኔ ተጨቁኗል፤ የአማራም ችግር ቢሆን በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ውስጥ ይፈታል” ይልሃል።

እንዲያው ”እናቱ ገበያ የሄደችበትና፥ እናቱ የሞተችበት እኩል ያለቅሳል” ካልሆነ በስተቀር ከአማራ ውጪ የትኛው የኢትዮጵያ ብሔር ነው በ ሃያ ስድስት ዓመታት ብቻ ከሃያ ጊዜ በላይ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎቹ ያፈሩትን ንብረት እንኳ እንዳይሰበስቡ በመንፈግ የተፈናቀለው? ከአማራ ውጪ የትኛው ብሔር ነው ዘሩን እንዳይተካ በመድሃኒት የመከነው? ከአማራ ውጪ የትኛው ብሔር ነው በጅምላ የተጨፈጨፈው? ከአማራ ውጪ የትኛው ብሔር ነው ህፃን፣ ሴት፣ ሽማግሌ ሳይል በገደል ከነነብሱ የተወረወረው? ከአማራ ውጪ የትኛው ብሔር ነው ‘የህዝብ ቁጥርህ በደዌ ተመናምኗል’ ተብሎ እያለ እንደሌለ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎቹ ያለበጀት በድህነት ሰንሰለት እንዲገረፉ የተደረገው? ከአማራ ውጪ የትኛው ብሔር ነው ቢ.ፒ.አር በሚል ሽፋን በጅምላ ከስራ ገበታው የተፈናቀለው? ከአማራ ውጪ የትኛው ብሔር ነው የመንግስት ሚዲያ በሚባሉት ሳይቀር የጥላቻ እና የስም ማጥፋት እንዲሁም የስነ ልቦና ጦርነት ሰለባ የሆነው? ከአማራ ውጪ የትኛው ብሔር ነው ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወር ባልተፃፈ ህግ የተከለከለው? ከአማራ ውጪ የትኛው ብሔር ነው ለም መሬቱን እየተነጠቀ ከአባቶቹ ምድር የተሳደደው? ብቻ በጣም ብዙ ነው።

አማራዊ ሆይ! የሌሊት ወፎቹ የሚነግሩህን ”የአማራ ችግር በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ ይፈታል” የሚል ማደናገሪያ እና ማደንዘዣ ከንቱ ቅዠት ለመሆኑ እነዚህን በምድር ላይ ያሉ እውነቶች አስተውል።

ሲጀመር ነገሮች እንዲሁ በአርምሞ ከቀጠሉ ወያኔ እንደ ሀገር እየገነባት ያለውን ትግራይን በሁለት እግሯ ካቆማት በኋላ በተግባር የሞተችውን ኢትዮጵያ በአዋጅ መሞቷን ነግሮህ አንተን ምንም ባልተዘጋጀህበት በትኖህ ይሄዳል።

ሲቀጥል ሁኔታዎች ከቁጥጥሩ ውጪ እየወጡ ከሄዱ በአንድ ሌሊት ውስጥ ከሩቅ ይህን ቀን እየተጠባበቁ ያሉትን ኦነግንና ኦብነግን ሰብስቦ ሀገሪቱን እንደየድርሻቸው ተቃርጠዋት እብስ ሲሉ አንተ ምንም ባልተዘጋጀህበት አውላላ ሜዳ ላይ ቀሪ ነህ። በዚህም ሳያበቃ ለቀጣይ ጥቃትም የተመቻቸህ ትሆናለህ። ያለው ነባራዊ ሃቅም ሆነ ሊመጣ ያለው ነገር ይህ ከሆነ ዘንዳ በሁለት ሃሳብ የሚያነክሱት የሌሊት ወፎች የሚሏት ድህረ-ወያኔ ኢትዮጵያ የት ነው ያለችው? ወትሮውንም አይናቸውን አንድም ባለማወቅ አልያም በረብ ስላሳወሩት እንጂ አይደለም ነገ ዛሬስ ኢትዮጵያ መቼ ኖረችና?

አማራዊ ሆይ! ከዚህ በኋላ የአማራ ህዝብ ሰቆቃ የሚቆመው በውክልና ሳይሆን በአንተ በአማራዊው ተጋድሎ ብቻ ነው!!! ፍፁም ዕረፍት የምታገኘውም በቄዳር ድንኳኖች ሳይሆን አባት ሀገር ግዮናዊውን የአማራ ሀገር ስትመሰርት ብቻ ነው። ስለሆነም አንድ እጃቸውን በ”አንድነት” መንደር አድርገው በሌላ እጃቸው አማራዊ ወጪትህ ውስጥ ገብተን ካልፈተፈትን የሚሉትን አትፍቀድላቸው!!!

እንዲሁ ባለማወቅ በሁለት ሃሳብ የምታነክሱ የአማራ ልሂቃን የአጥንታችን ፍላጭ፥የስጋችንም ቁራጭ እንደሆናችሁ ከማንም በላይ እናውቃለን። የእኛ ተቃውሞ እና ፀብ የህዝባችንን ሰቆቃ እንዲራዘም እያደረገ ካለው በሁለት ሃሳብ ከሚያነክሰው አስተሳሰባችሁ ጋር ብቻ ነው።

የሰው ልጅ ልክ እናንተ የደነቀራችሁብንን አይነት ተግዳሮት ሲገጥመው አይደለም የሰውን ልጅ የእግዚአብሔርን መልዓክ እንኳ ”ከእኛ ወገን ነህ? ወይስ ከጠላቶቻችን?” ብሎ እንደሚጠይቅ ከእግዚአብሔር ነብይ ከኢያሱ አይተናል። እኛም እንጠይቃለን ወይ ከእኛ ጋር አልያም ከጠላቶቻችን ጋር ወግኑ።

          4ኛ. ስዬዎች /The Egocentric/

የዛሬ ሰባት ዓመት አካባቢ ቀንደኛ ወያኔ የነበረው እና አሁንም የሆነው ስዬ አብርሃ ከእስር ሲፈታ የቆሰለ አውሬ ሆኖ ነበር። ራሱ በዋናነት የመሰረተውን ሥርዓት በግል ጋዜጦች ከማብጠልጠል ጀምሮ ፖለቲካ ፓርቲ እስከመመስረት ደረሰ። ይባስ ብሎም እስከ ዛሬ እንደዚህ እጅ እጅ የሚል መጽሐፍ አንብቤ የማላውቀውን ”ፍትሕ እና ዳኝነት በኢትዮጵያ” የሚል መጽሐፍ ፃፈ፤ ኧረ ይባስ ብሎም የአሜሪካው ዲያስፖራ መድረክ አዘጋጅቶ ጋበዘው። ታድያ ይሄን ሁሉ ”በተቃውሞ” ጎራ ከተጓዘ በኋላ በድንገት መለስ የመሞቱ ነገር ተሰማ። በቃ መለስ ሲሞት የስዬም ተቃዋሚነት አብሮ ሞተ እና ወደ ዘመዶቹ ተቀላቀለ። ወትሮውንም የግል ፀብ እንጂ የአመለካከት ልዩነት አልነበረውም። እንዲያው የግል ፀቡን የአመለካከት ልዩነት ያለ በማስመሰል ደጋፊን ከኋላ ለማሰለፍ የተደረገ ስልት ነበር።

ዛሬ ይሄንን መሰሪ ሰው ለምሳሌነት የተጠቀምኩት በቁጥር ብዙ ባይባሉም ሊያሳድሩ ከሚችሉት ተፅዕኖ አንፃር ”እኔ፣የእኔ፣ለእኔ” በሚል ግለኛ አመለካከት ታጥረው በግል ”አንድነት” ከምትባለው ጎራ ጋር ስለተጣሉ ብቻ የግል ተቃርኗቸውን የአማራነት ካባ ደርበውላት ተከታዮችን ለማፍራት እንደሚጥሩ ከአንዳንድ የአማራ ልሂቃን እያየን ነው። ነገ የግል ቁርሿቸው በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት ሲያሽር ዛሬ አንቅረን ተፍተነዋል ያሉትን ነገ ተመልሰው እንደሚልሱት እርግጥ ነው።

ስለሆነም አማራዊ የሆንክ ሁሉ ማንም ሄደም መጣም ያንተ ተጋድሎ ግለሰቦችን ማዕከል ያደረገ ሊሆን አይገባም። ያንተ ተጋድሎ ግዮናዊ አባት ሀገርህን እስክትመሰርት እና ነፃነትህን እስክታረጋግጥ እንጂ ግለኞች እስከሚወርዱበት የግማሽ መንገድ ፌርማታ ሊሆን አይገባም።

ለዛሬ ይቆየን።በቀጣዩ ክፍል እስክንገናኝ ቸር እንሰንብት።

ዴቭ ዳዊት።

ተግባር ይቅደም፤ ትኩረት ለኢኮኖሚው፤ ትኩረት ለወጣቱ!


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢሕአዴግ ሊቀመንበርና የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ በርካታ ቁጥር ያለው የአገራችን ሕዝብ በተስፋ ስሜት ላይ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ከምንጊዜውም በላይ በጣም አሳሳቢ ነው፡፡ በተለይ ካለፉት አራት ዓመታት ጀምሮ የሚታየው ነገር ከባድ ከመሆኑም በላይ መሠረታዊ ለውጥን የሚጋብዝ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች መሠረታዊ ጥያቄዎችን አንግበው ሲታገሉና ሲሞቱ ቆይተዋል፤ የሚጠብቁትን ለውጥ ግን አላገኙም፡፡ ኢኮኖሚው በእጅጉ ተቀዛቅዟል፤ ሥራ አጥነት ጣሪያ ነክቷል፡፡

በሀገራችን በግንባር ቀደምነት የለውጥ ጥያቄ የሚያነሳው የትኛው የኅብረተሰብ ክፍል ነው? የሚለውን ነጥብ መለየቱ ተገቢ ነው፡፡ የለውጡ እንቅስቃሴ ሞተር ወጣቱ ነው፡፡ ይኽ ወጣት የኅብረተሰብ ክፍል መቶ ሚሊዮን እንደሚሆን ከሚገመተው የአገራችን ሕዝብ ውስጥ 70 መቶ የሚሆን ድርሻ አለው፡፡ ይኽ በገጠርም በከተማም የሚኖረው ወጣት ነገሮች ቢመቻቹለት በአጭር ጊዜ ወደ መካከለኛ መደብ ሊደርስ የሚችል ነው፡፡ አፍሪካ ውስጥ እንደሚታወቀው የመካከለኛ መደቡ ቁጥር አነስተኛ ነው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ደግሞ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ነገሮች ቢመቻቹለት፣ ትክክለኛ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ቢቀየስለት፣ ትክክለኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ቢዘረጋለት በአጭር ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ሊኖረው የሚችል የኅብረተሰብ ክፍል ነው፤ ወጣቱ፡፡ የሚጠይቀውም ትክክለኛ ጥያቄ ነው፡፡ በገጠር ያለው አብዛኛው መሬት ይፈልጋል፡፡ በከተማ የሚኖረውም ካፒታል እንዲፈጥርና ራሱን እንዲችል ሁኔታዎች ሊመቻቹለት ይገባል፡፡

ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ጥራት ያለው ትምህርትም ባይሆን “ተምሯል”፤ በተለያየ የዕውቀት ደረጃና ችሎታ የሰለጠነ ነው፡፡ የመረጃ ግብዓትም ያገኛል፤ ለቴክኖሎጂ ቅርብ ነው፡፡ ወጣቶች አካባቢያቸውን መረዳትና መመልከት ችለዋል፡፡ ስለሆነም ማን እየተጠቀመና ማን እየተጎዳ እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ የሚገባቸው እና አገራቸው ልታቀርብላቸው የምትችለው ምን እንደሆነም በሚገባ ይረዳሉ፡፡

እንደሚታወቀው ባለፉት 27 ዓመታት ጥቂት የኅብረተሰብ ክፍሎች በከፍተኛ ደረጃ የበለጸጉበት እና አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የበይ-ተመልካች የሆነበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ባለበት የለውጥ ጥያቄ መነሳቱ የማይቀር ነው፡፡ ጥቂት ከሥርዓቱ ጋር የተጠጋጉ ሰዎች ካፒታል የሚያገኙበትና የሚፈጥሩበት ምቹ ሁኔታ ይመቻችላቸዋል፤ በቀላሉ የባንክ ብድር ያገኛሉ፣ ሌላም ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ለነዚህ ዜጎች (ለጥቂቶች) የተመቻቸው ሀብትና ዕድል ለእኔም ይመቻችልኝ እያለ ነው ያለው፡፡ ምንጊዜም ቢሆን አንድን አገር አስተዳድራለሁ ያለ መንግሥት (ድህነትን እታገላለሁ፤ ብልጽግናን አመጣለሁ ካለ) ካፒታልን ለኅብረተሰቡ ማመቻቸትና መፍጠር አለበት፡፡ ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ሥራ ፈጣሪ ነው፡፡ ሥራ ለመፍጠር ደግሞ ካፒታል ያስፈልጋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ይፈጠርልኝ ነው የወጣቱ ጥያቄ፡፡ ይኼ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ተሞክሮ ተሞክሮ ሰሚ ስላጣ ወደ እምቢተኝነት፣ ከዚያም አልፎ ወደ አመጽ ተሸጋግሯል፤ በዚህ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ (ለሦስተኛ ጊዜ) ላይ እንገኛለን፡፡ ወጣቶች በፈጠሩት ተጽዕኖ ምክንያት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ ካቢኔ እንዲያዋቅሩና በመጨረሻም ራሳቸው ሥልጣን እንዲለቁ ተገድደዋል፡፡ በምትካቸው አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሸመው፣ እሳቸውም አዲስ ካቢኔ እንደሚያዋቅሩ ይጠበቃል፡፡

ጥያቄው ግን አንድ ጠቅላይ ሚኒስትርን በሌላ የመተካት ጥያቄ አይደለም፡፡ የዴሞክራሲ፣ የፍትሕና የነጻነት ጥያቄ ነው፡፡ ጥያቄው መልስ ካላገኘ ግን ሁላችንም ወደማንወጣው አደጋ ውስጥ ልንገባ እንችላለን፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ መሠረታዊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ባፋጣኝ መልስ ካላገኙ ወይም ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የሚያስችል የመፍትሔ አቅጣጫ ካልተቀየሰ እና ምላሹ ጥያቄ ያነሱትን አካላት ካላሳመነ ወደ ከፋ ሁኔታ እንሄዳለን፤ መንግሥትም ሊቆጣጠረው ወደማይችለው ችግር ያስገባናል፡፡ ጥያቄው እየቀረበ ያለው በሰላማዊ መንገድ ነው፡፡

በሚያሳዝን ሁኔታ ለፖለቲካዊ ጥያቄ ፖለቲካዊ መልስ መስጠት ሲገባ አሁን የሚታየው ግን እሱ አይደለም፡፡ በመንግሥት በኩል የሚወሰኑት ውሳኔዎችና የሚቀርቡት የመፍትሔ ሐሳቦች እርስ በርሳቸው የሚጋጩና የችግሩን ሥረ-መሠረት ከግንዛቤ ውስጥ ያላስገቡ ናቸው፡፡ ሕዝብ የሚጠይቀው ጥያቄ ሌላ መንግሥት የሚያቀርበው የመፍትሔ ሐሳብ ሌላ እየሆነ ነገሮች ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እየሄዱ ነው፡፡ ከታሪክ መማር ትልቅ ቁም ነገር ነው፡፡ ከቅርቡ የአገራችን ታሪክ እንኳ በጣም በርካታ ቁም-ነገሮችን መማር ይቻላል፡፡ እንደሚባለው ጥሩ ፖለቲከኛ ከሀገሩና ዓለም ታሪክ የተማረ ፖለቲከኛ ነው፡፡

ከታሪክ ያልተማረ የፖለቲካ ሰው የፖለቲካ ሰው ሊባል አይችልም፡፡ ኢሕአዴጎች ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ መማር አለባቸው፡፡ ከቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴና ከደርግ አወዳደቅ የተማሩ አይመስለኝም፡፡ ከሌሎችም የአፍሪካ አገሮች ለምሳሌ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከሩዋንዳና ከመሳሰሉት አገሮች የተማሩ አልመሰለኝም፡፡ ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ የወደቁበት ምክንያት መንግሥታቸውን ሪፎርም ባለማድረጋቸው ነው፡፡ በወቅቱ መሠረታዊ የሆኑ የፖለቲካ ማሻሻያዎች ባለመደረጋቸውና የኅብረተሰብ ጥያቄ ሊፈታ ባለመቻሉ ሥርዓቱ በሕዝባዊ አመጽ ተወግዷል፡፡ ደርግም ተለምኗል፤ ምሁራን መክረዋል፡፡ ነገር ግን ሰሚ የለም፡፡ መጨረሻቸው በእስር ቤት መማቀቅ፣ ሀገር ጥሎ መሰደድና ሞት ሆነ፡፡ ሀገራችን ብዙ ዋጋ ከፍላለች፡፡ ኢሕአዴግ ካለፉት ሁለት አገዛዞች የመጨረሻ እጣ-ፈንታ የሚማረው ብዙ ነገር አለ፡፡ መሠረታዊ የፖለቲካ ለውጥ ካላደረገ የእሱም አወዳደቅ ካለፉት ሥርዓቶች የተለየ ሊሆን አይችልም፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ በኢሕአዴግ ውስጥ የሚደረግ የሥልጣን ሽግሽግ አይደለም፡፡ የሚያስፈልገን መሠረታዊ የፖሊሲና የአስተሳሰብ ለውጥ ነው፡፡ የሚያስፈልገን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በነጻነትና በእኩልነት የሚኖርበት ሥርዓት ነው፡፡

ኢትዮጵያ ከሁሉም (በሀገር ውስጥም በውጭም) ከሚኖሩ ልጆቿ ተጠቃሚ የምትሆንበት ሥርዓት ነው የሚያስፈልገን፡፡ ብዙ ኢትዮጵያዊያን በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር መምጣት ደስ የተሰኙትና ተስፋ ያደረጉት እንደዚህ ያለ የዜጎችን ነጻነትና እኩልነት የሚያከብር የፖለቲካ ሥርዓት የሚገነባበት ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል በሚል መንፈስ ነው፡፡ ጋዜጠኞች በነጻነት የሚጽፉበት፣ ተቀናቃኝ ፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት ተንቀሳቅሰው ሕዝብ የሚያደራጁበት፣ ዜጎች በዘውጋዊና ሃይማኖታዊ ማንነታቸው መድልዎ ሳይደረግባቸው በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ተዘዋውረው መኖርና መሥራት የሚችሉበት፣ በፖለቲካ ኀይሎች መካከል እርቅና መግባባት የሚፈጠርበት ወዘተ. ሁኔታ ይፈጠራል በሚል ተስፋ ነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መምጣት ብዙዎች የተደሰቱት፡፡

በመንግሥት በኩል የተገባው የለውጥ ቃል የይስሙላ ቃል እንዳይሆንና ተመለሰን ወደ አመጽ አዙሪት እንዳንገባ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡ የአመጽ አዙሪት ሊሰበር የሚችለው ደግሞ መሠረታዊ ለውጥ ሲመጣ ብቻ ነው፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በኢኮኖሚ ረገድ ያለው አቋም እጅግ ደካማና አሳሳቢ ነው፡፡ አሁን በተያዘው ሁኔታ ኢኮኖሚውን አነቃቅቶ መረን የለቀቀውን የሥራ አጥነት አደጋ መቅረፍ አይቻልም፡፡ ወገብን ጠበቅ አድርጎ፣ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ቁም ነገሮች ቅድሚያ ሰጥቶ ከምር መሥራት ይገባል፡፡ ከቃል ይልቅ ተግባር ይቅደም፤ ኢኮኖሚው ትልቅ ትኩረት ይሻል!

አገው ዐማራ ነው ዐማራም አገው ነዉ! (ልጅ ተድላ መላኩ)


(ሳይንሳዊና ታሪክ ተኮር ethnological ሐተታ፣ ከምሁራዊ ምንጮች ጋር)

ዋና ዋና ነጥቦች፦

 • ሴማውያን (ነገደ ዮቅጣን/አግዓዝያን) ከጥንተ ኩሻይት ጋር ተዋህደው ጥንተ አገውን ወለዱ።
 • ቀደምት/ጥንታዊ አገው ከጥንት ኩሻይት እና ከአግዕዝያን የሚወለድ የአምሓራ የኩሻዊ የዘር ግንድ ነው። አገውንም ኩሽ ነው የሚሉት ከዚህ የተነሳ ነው።
 • ግዕዝ የአግዓዝያን ልሳን ነው።
 • አገውኛ ከአግዓዝያን ቋንቋ (ግዕዝ) እና ከጥንት ኩሻይት ቋንቋ (?) ጋር ተዋህዶ የተፈጠረ ቋንቋ ነው።
 • በኋላም ግዕዝኛ ከተዋሃደው አገውኛ (ጥንተ ኩሻይት ቋንቋ እና ግዕዝ) ጋር እየተሳሳበ/ እየተዋሃደ አማርኛን ፈጠረ።
 • የአምሓራ ዘር የደቡብ አግዓዝያን (southern Himyarites ) ሲሆን ከትግሬ የሚለየው የአገው ማንነት ያለበት በመሆኑ ነው። አምሓራ የአገውን ማንነት የያዘው የአግዓዝያን ዘር ነው።
 • የአክሱም መንግስት የአግዓዝያን (የአምሓራ/የአገው) ስልጣኔ ነው።
  የአክሱም መንግሥት ከመመስረቱ ከብዙ ሺህ ዘመናት በፊት በኢትዮጵያ ምድር ቀደምት አገው የሚባል ጥንታዊ ዘር ነበር። በዚያን ዘመን አግዓዚያን የሚባል፣ ቋንቋው ግዕዝ የሆነ ጥንታዊ ብሔር የቀደምት አገው ዘር እና ሥልጣኔ በሚገኝባት በኢትዮጵያ ምድር የግዕዝ ሥልጣኔውን ሲያስፋፋ በዘመናት ሂደት የጥንት አገዎችና አግዓዚያን በዘር፣ በባሕል፣ በእምነት እየተዋሃዱ አደጉ። አግዓዚያን “ትግሬ” ማለት ሳይሆን ከ modern ትግሬ ማንነት በፊት የነበረ እና ከግዕዝ ቋንቋ የመጡን ቋንቋዎች የሚናገሩ ብሔሮች ሁሉ አባት ነው።
  የአክሱም መንግሥት አገውን መሰረት አድርጎና ከአገው ዘር፣ ቋንቋና ባህል ጋር በመዋሃድ ያደገ የግዕዝ ተናጋሪ የአግዓዚያን ሥልጣኔ ነበር። ይህ ጥንታዊ የማንነት መዋሃድ “አክሱም” የሚለው ሥም ውስጥም ይታያል። የታሪክ ሊቃውንት አክሱም ማለት ከአገውኛ እና ከግዕዝ ቃላት መዋሃድ የተገኘ ቃል እንደሆነ ይተነትናሉ። የቃላቱም ውህደት፣ “አኵ” (ውሀ) ከሚለው ከአገውኛ ቃል እና “ሥዩም” (ሹም) ከሚለው ከግዕዝ ወይም አማርኛ ቃላት የተገኘ የቃላት ውህደት ነው። “የውሃ ሹም” — የቀይ ባህር ጌታ ተብሎ ሊፈታም ይችላል። ይህ በሳይንሳዊ የታሪክ አጠናን ዘዴ (Historical Method) ያለ፣ በመጻህፍት የተጻፈ ዳሰሳ ነው።
  በባህላዊ ታሪካዊ ትንተና ደግሞ፣ አማራ እና አገው ከብዙ ሺህ ዘመናት በፊት ከአንድ ቤት የወጡና አብረው የፈለሱ ወንድማማች የጥንት እስራኤላዊያን ዘር ናቸው (ይህን የጻፉት አለቃ ታዬ ናቸው)። ወደ ኋላ ርቀን ስንሄድ ከንግሥተ ሳባ ዘመን (ሦስት ሺህ ዘመን) በፊት የነበሩት የጥንት የኢትዮጵያ ነገሥታት early Cushites/ የጥንት ኩሻዊያን ናቸው። በኋላ ነገደ ዮቃጤን (Joktan) ሴማዊያኑ ጥንት ኩሻዊያን ጋር ተዋሕደው ከአክሱም በፊት (pre-Axumite) ሳባዊ ሥልጣኔና በኋላ አክሱማዊያን ተፈጠሩ (ሴማዊያን የተባሉትም አግዓዚያን [ሴማዊ ተናጋሪ ንዑስ ብሔሮችን የወለዱ ግዕዝ ተናጋሪዎች] ናቸው) ። ቀደምት አገው የሚባለው ከearly Cushites የሚገኝ የአምሓራ ኩሻዊ የዘር ግንድ ነው። ይህን ለመደገፍም አማርኛም፣ ግዕዝም፣ ትግርኛም አገውኛ “substrate” (የቋንቋ መሰረት) አላቸው። ግዕዝ የሚናገሩ ደቡብ አግዓዚያንም ብላቴን ጌታ ኅሩይ ነገደ ዮቃጤን ሴማዊ ሳባዊያን ይሏቸዋል) የአማራ አባቶች ናቸው።አማርኛ ቋንቋ ውስጥ የጥንት አገው ልሳን lingual particles አሉ።
  ከቀዳማዊ ምኒልክ ጀምሮ ያሉትም ነገሥታት ስማቸው ኩሻዊ ሆኖ ይቀጥልና ቆይቶ የሁለቱን (የአገው-አግዓዚያንን) መጋባት ሲያሳይ ሴማዊ ወይንም ግዕዝ ስሞችን መያዝ ይጀምራል — የዚህ ታሪካዊ እይታ ድጋፍ ሊሆን የሚችለው የነገሥታቱ ስም አሌክትሮን፣ ፒያንኪያ፣ ንያትሞሙን፣ አይተት፣ አርካሚን፣ ቶኒኪ፣ ኪንዳኪ፣ ወዘተ ነበር። ይህ ግዕዝ ሳይሆን ኩሻዊ ነው። ወይንም ቀደምት-አገው (proto-Agaw) ነው። ሲቀጥል ደግሞ ስማቸው አብራሐ፣ አጽብሐ፣ አድሐና፣ ሳሕል፣ እለ ሳሕለ፣ ኢዮአብ ኢያለ ይመጣል። ይህ ደግሞ ሴማዊ ወይንም ግዕዝ ሲሆን ከአማርኛና ከትግርኛ ጋር የተያያዘ ነው (የአግዓዚያን ልሳን ነው)። አማርኛ ቋንቋ አገውኛን እየሳበ ሳያድግ በፊት ቀደምት ግዕዝ (early Ge’ez) ነበር። ከጥንታዊ አማርኛ ግጥም ላይ ማነጻጸር እንደሚቻለው፣ ከሰባት መቶ አመት በፊት እንኳን የሚነገር አማርኛ ለግዕዝ ልሳን በድምጸትም በጣም ይቀርብ ነበር። ለምሳሌ፣ “ሽንኩርት ይላጥ” ሊል “ሽንጕርት ይልሐጽ” ይላል። “አርበኛ” በጥንታዊ አማርኛ “ሓርበኛ” ነው። “አማራ” የሚለውም ቃል በጥንታዊ አማርኛ “አምሓራ” ነው። በጥንታዊ አማርኛ “አንገት” የሚለውን ቃል “ሐንገት” ይለዋል። “ፈጠፈጠ” የሚለውን “ፈጸፈጸ” ይለዋል። “ጦር” የሚለውን “ጾር” ይለዋል። የአማርኛ ከጥንታዊ የቋንቋ ቅላጼው እየለሰለሰ የሄደው በቅድሚያነት አገውኛ ጋር ባለው መተሳሰሩ ምክኒያት ነው።
  ግዕዝ ቋንቋ የሚናገሩ አግዓዚያን ቀደምት አገውኛ ከሚናገሩ አገዎች ጋር በዘር፣ በቋንቋና በባህል ተዋህደው አማርኛ ቋንቋና የአማራ ዘር ከሁለቱ በጣም ጥንታዊ (primitive) እድገቶች (developments) ተገኘ። አማርኛ ቋንቋ በጥንታዊ ግዕዝ እና በቀደምት አገውኛ ቋንቋ ውሕደት ያደገ ቋንቋ ነው። የአማራ ዘር /Hamra/ ሐምራ (ኸምራ) የሚባለውን ዘር መሰረታዊ-ጥንታዊ የአገው ማንነት በውስጡ ያካተተ ልዕለ ብሔር ነው። በስድስተኛው ክፍለዘመን በአክሱም መንግሥት የአገውና አግዓዚያን መዋሃድ የአክሡምን ሥልጣኔ ከማስገኘት አልፎም አድጎ ነበር። በአንድ ጎኑ አገው ለአማራ የደም፣ የአጥንት፣ የቋንቋ፣ የሥልጣኔ አካል ነው። ኣማራ ለአገው የሆነውን ትግሬ ለአገው አይደለም። የአገውን ማንነት የሳበው የአግዓዚያን ክፍል #አምሓራ የሚባለው ነው። ኤትኖሎጂስቱ (የብሔር አጥኚ) ኦገስተስ ኪን እንደጻፈው አምሓራ የተባለው ‘ደቡብ አግዓዚያን’ (southern Himyarites) ሲሆን ከትግሬ አንድ ልዩ የሚያደርገው የአገውን ማንነት ያካተተ መሆኑ ነው : “When the [ancient] Ag’azian crossed the Takazze and extended . . . southwards, they became more and more intermingled with the #Agao/Agaw aborigines. Hence the southern Abyssinians of Amhara and Shoa are a mixed Hamito-Semitic people, whose very name is . . . the primitive Hamra inhabitants of the central provinces between the Takazze and the Abai . . . . Amhara, present name of the Southern Himyarites [ደቡብ አግዓዚያን] still remains the designation of a large section of the Hamitic (Hamra) aborignies.” (Africa, Vol I, Augustus Keane, p. 494 – 495).
  አገውኛ አማርኛ ውስጥ ከጥንት ግዕዝ ልሳን ጋር በመዋሃዱ ምክኒያት አማርኛ የጥንት አግዓዚያን (Sabaean-Himyarites) እና አገው ውህደ ልሳን ሲሆን አምሐራ ማለት አገው ማንነትን ስቦ ያካተተ የአግዓዚያን ዘር ነው።
  የዛጔ መንግሥት የአገውነትና የአማርነትን ፍጹም ኢተነጣጣይነት ያሳየ ታላቅ ሥርወ መንግሥት ነበር። በዛጔ መንግሥት አገው የአማራን አግዓዚያን ዘር፣ ባህልና ሃይማኖት የመንግሥቱን ይፋዊ ቋንቋ አማርኛ አድርጎ ፈጽሞ ተላበሰ። አማራ የጥንት አገው ጎኑ ላይ የግዕዝ ሥልጣኔን አጠናከረ። ከዛጔ ነገሥታት ለምሳሌ ቅዱስ ላሊበላ የአገው የጦር መሪው የመራ ተክለሃይማኖት ዘር ሆኖ የርሱ ሠራዊት ደግሞ አምሓራ ነበር። አማርኛ ቋንቋ መንግሥታዊ ቋንቋ መሆን የጀመረው በላሊበላ መንግሥት ዘመን መሆኑ ይታመናል። ይህም ከዛጔ በፊት ፍጹም ግዕዝኛ የአክሱም ቋንቋ ሆኖ ሳለ፣ በዛጔ መንግሥት ደግሞ የአገውኛና የግዕዝ ፍጹም ጥምረት አማርኛ እንዲሆን በዛጔ ነገሥታት ተጀመረ። ስለዚህም አገውኛ በሰፊው ግዕዝ ቋንቋ ውስጥ እየገባ በማደጉ አማርኛ ሆኗል።
  አገው-አማራ በሦስት እና በአራት ሺህ ዘመናት የማይነጣጠል አንድነትና በጥምረት ማደግ የአንድ ሳንቲም ሁለት ግልባጭ ሆነው ላይለያዩ በአምላክ ማህተም አንድ ሆነዋል። ይህም በአገው ድህረ ታሪካዊ ማንነት በአማራ ቁልጭ ብሎ የሚታይ፣ የሚዳሰስና የሚበለጽግ ነው። አገውን ከአማርነት ውስጥ መሸርሸር አማርነትን ማጥፋት፣ አማራን ከአገውነት ውስጥ ማውጣትም እንደዚሁ አገውነትን ማራቆትና ታሪኩን መንፈግ ነው።

ልጅ ተድላ መላኩ ዘብሄረ ዋግ ሹም ክንፉ

ዋቢ መጻሕፍት

 • ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፣ “ዋዜማ”
 • David L. Appleyard, “A Comparative Dictionary of the Agaw languages”.
 • Augustus Henry Keane, “Africa”, Vol I.
 • Sergew Hable Selassie, “Ancient and Medieval Ethiopian History to 1270”.
 • Willie F. Page, “Encyclopedia of African History and Culture: African kingdoms (500 to 1500)”.
 • James Stuart Olson, “The Peoples of Africa: An Ethnohistorical Dictionary.”
  ~~
  ለነገሩ ዘር እየቆጠሩ ማጥቃት ስለተለመደ እንጂ ሁሉም የአንዱ የኖህ ልጆች ዘር ነው። ይህ አይካድም። ሆኖም ይህን ከግምት ያላስገባ ፀረ ህዝብ አካሄድን ለማስቆም ይህን መሰል ሃሳቦች የግድ ያስፈልጋሉ።
  (#ፋኖሚድያ)

ግንቦት ፳ – ሪፑብሊክ ለመመስረት ጫካ የወረዱ ፋሽስቶችና ናዚዎች ኢትዮጵያን የወረሩበትና አፓርታይድን ሕጋዊ ያደረጉበት ርጉም ቀን ነው! (Achamyelh Tamiru)

ግንቦት ፳ የኢትዮጵያ ሻለቆችና የበታች መኮንኖች የመሰረቱት የጭካኔ አገዛዝ ተወግዶ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ጫካ የወረዱት ፋሽስት ወያኔዎችና ናዚ ኦነጎች የመሰረቱት የአፓርታይድ አገዛዝ የተተካበት ቀን እንጂ የኢትዮጵያ «የድል ቀን» አይደለም! ሆኖም ግን አብይ አሕመድን ጨምሮ የአገዛዙ ነጂዎች ግንቦት ፳ን ልክ እንደ የካቲት ፳፫ የዓድዋ ድል በዓል «የድል በዓል» አድርገው እንኳን አደረሳችሁ እያሉ በማክበር ላይ ይገኛሉ።

ግንቦት ፳ ለኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ውስጥ የአገዛዝ ለውጥ [Regime Change] የመጣበት ቀን እንጂ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነ የውጭ ወራሪ የተሸነፈበት የድል ቀን ወይንም [Victory Day] አይደለም። ግንቦት ፳ «ብሶት» ወለደኝ ለሚሉት ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግም ቢሆን ኢትዮጵያን እየገዘገዙ እስካሉ ድረስ ደርግ የሚባል የኢትዮጵያ ሻለቆችና የበታች መኮንኖችን አገዛዝ ተክተው ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ የመሰረቱት አረመኔያዊ የአፓርታድይ አገዛዝ የተከለበት ቀን እንጂ እንደ ፋሽስት ጥሊያን አይነት ባዕዳና የጋራ ጠላታችንን ያሸነፈበት ዕለት አይደለም።

ስለዚህ በመንግሥትነት ለተሰየመውም ለዐቢይ አሕመድና ለጄሌዎቹ ለብአዴኖችም ሆነ ለኢትዮጵያውያን የድል በዓላት የሚሆኑት እንደ የካቲት ፳፫ [ጀግኖች አያቶቻችን ጥሊያንን ዓድዋ ላይ ድባቅ የመቱበት ዕለት] እና ሚያዚያ ፳፯ [ኢትዮጵያውያን አርበኞች የፋሽሰቱን የሙሶሎኒ ወራሪ ኃይል አቧራ አስገስተው ካገራችን ጠራርገው ያስወጡበት ዕለት] ወዘተ… አይነት ልዩ ቀናት ናቸው እንጂ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው ደርግ ሄዶ ከነትንሽነቱ የደርግ የጭካኔ ታናሽ ወንድም የሆነ ወያኔ የሚባል ጨካኝ የትግራይ ማፍያ ቡድን የኢትዮጵያን መንበረ መንግሥት የተቆናጠጠበት ቀን አይደለም።

የወያኔ ዲቃላው ዐቢይ አሕመድም ግንቦት ፳ን የድል በዓል አድርጎ የመቁጠሩ አባዜ የመጣው ወያኔ የመንፈስ አባቱና ሱሪ ያስታጠቀው ሻዕብያ የሚያደርገውን ሁሉ እንደወረደ ሲኮርጅ የኖረውን መኮረጁ ነው። ሻዕብያ አስመራን የተቆጣጠረበትን ቀን የድል በዓል ብሎ ሲያከብር ስላየ ዐቢይም ወያኔ አዲስ አበባ የገባበትን ግንቦት ፳ን የድል በዓል አድርጎ እንደ ወረደ ከሻዕብያ ኮረጀ። ወያኔ ከሻብያ አላንስም በሚል የመንፈስ ጥገኝነቱ ምክንያት ሻዕብያ ያደረገውን ሁሉ እየኮረጀ ሻዕብያ ከኢትዮጵያ አንጻር የፈጸማቸውን ሁሉ በመቅዳት ኢትዮጵያን የኢትዮጵያ ቅኝ ገዢ በማድረግ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ እያዋረደ ነው።

ሻዕብያ ኢትዮጵያን ወራሪና ቅኝ ገዢ ብሎ ነፍጥ አንስቶ ስለታገለና የታገለለትንም ዓላማ ስላሳካ፤ በተግባርም አሁን ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ኃይል ስላልሆነ፤ ግንቦት ፳ን የድል በዓል አድርጎ ሊያከብር የተገባ ነው። ዐቢይና ወያኔ ግን እንደ ሻዕብያ ሁሉ ከኢትዮጵያ ተለይተው የኦሮሚያ ሪፑብሊክና የትግራይ ሪፑብሊክን እስካልመሰረቱና ኢትዮጵያን እስኪያንገሸግሻት እየገዙ እስካለ ድረስ ግንቦት ፳ን በኛ ገንዘብ የድል በዓል አድርገው ሊያውጁና ሊያከብሩ አይችልም።

ለተቀረነው ኢትዮጵያውያን ግንቦት ፳ ማለት፡ የድልም የስርዓት ለውጥም የመጣበት ዕለት ሳይሆን ደርግ የሚባል ሻለቆችና የበታች መኮንኖች የተሰየሙበት የጭካኔ አገዛዝ ተወግዶ በጭካኔያቸው ክብረወሰን የተቀዳጁት ፋሽስት ወያኔዎችና ሁሉ ብርቁ የሆኑ ናዚ ኦነጎች የተተከሉበት የመከራ ቀን ነው።

”የአማራን ችግር የዜግነት ብሔርተኝነት አይፈታውም፤ በዜግነትና በማንነት ብሔርተኝነት የተከፋፈለው አማራው ብቻ ነው፤ የዜግነት ብሔርተኝነትን ለማራመድ ቅድመ ሁኔታዎቹ የሉም” ( ባዬ ተሻገር)


የአማራ ፖለቲካ ትግል በማንነት ብሔርተኝነት እና በዜግነት ብሔርተኝነት አቀንቃኞች መካከል እየሆነ መጥቷል። በሁለቱ የአስተሳሰብ ጎራዎች ተከፋፍሎ የእርስበርስ ትግል የሚያካሂደው ግን አማራው ብቻ ነው። ምናልባትም ከሁለትና ከዚያ በላይ ከሚሆኑ ብሔሮች ከተገኙ የድብልቅ ብሔር ተወላጆች በስተቀር አማራ ያልሆነ የዜግነት ብሔርተኝነት አቀንቃኝ ማግኘት ይከብዳል። በእርግጥ የሁለቱ ጎራዎች ትግል አማራ እንደማንኛውም ሰው እኩል የሚከበርባት አገር እንዲኖረው ማስቻል መሆኑ ባያጠራጥርም እርስበርስ የሚደረገው ጤነኛ ያልሆነ ፍትጊያ ግን ወደዚያ መንገድ የሚያመራ አይመስልም። ይልቁን በሃሳብ ልዩነት ምክኒያት ወንድም በወንድሙ ላይ ጣት መቀሳሰር ሆኗል።

የዜግነት ብሔርተኝነት የሚያቀነቅኑና ራሳቸውን ኢትዮጵያዊ ብለው መግለጽ የሚወዱ አማራዎች በጥቅሉ አንድ ብሔር/ቡድን/ መጠቃት ወይንም ማጥቃት የለበትም የሚለውን የሚቀበሉ ቢሆንም የትግላቸው አውታር የሚያዘነብለው አማራዊ ማንነታቸውን አጥብቀው የያዙትንና አማራዊ ሥነ-ልቦናን እና ባህልን የተላበሱ ወገኖቻቸውን በመቃወምና በማጥቃት ላይ ነው። ከአምሥት ዓመት በፊት ጀምሮ በአዲስ መልክ በተቀሰቀሰው የአማራ ብሔርተኝነት አቀንቃኞች እና አንቀሳቃሾች ላይ መጠነ-ሰፊ የማጥቃት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቢቆዩም በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ላይ የሚደረገው ከፍተኛ ዘመቻ ጥሩ ማሳያ ይሆናል።

በእርግጥ ኢትዮጵያዊ ነን የሚሉ አማራ የዜግነት ብሔርተኝነት አራማጆች እራሳቸውን ችለው የፖለቲካ ምህዳሩ ላይ የሚሳተፉ አይደሉም ይልቁን አንዳንድ “ህብረ-ብሔራዊ” ነን በሚሉ ነገር ግን አማራ-ጠል መሆናቸው በመረጃና በማስረጃ የተረጋገጠ በህዳጣን ብሔሮች ስብስቦች በተመሰረቱ እና ኢትዮጵያን የመግዛት ተራው የእኛ ነው ብለው በሚያምኑ ከገዥና ተገዥ ትርክት ባልወጡ ድርጅቶች ጀርባ የተደበቁ ናቸው። በአማራነታቸው የማያምኑት ኢትዮጵያዊ ነን ባይ አማራዎች አይነተኛ መገለጫዎች በአማራው እና በሌላው የሚደርሰውን ጥቃትም ሆነ ራስን የመከላከል እርምጃ እኩል አለመመዘናቸው፤ ማንኛውም የአማራ ድርጅት ወይንም አማራ ነኝ የሚል ግለሰብ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ጎልቶ የሚታያቸውና ትክክል አለመሆኑን ለመግለጽ ጊዜ የማይወስድባቸው መሆናቸው እና ከአማራው ወገናቸው ይልቅ ለሌላው ብሔር ልዩ ፍቅር እንዳለቸው ማሳየታቸውና ጥብቅና መቆማቸው ናቸው። በኢትዮጵያዊ(አማሮች) አጠራር ዜጎች (በአማራ ብሔርተኞች አጠራር አማሮች) ለዘመናት ከኖሩባቸው እና ንብረት ካፈሩባቸው ቀዬዎች ሲፈናቀሉ ድምጻቸውን አልሰማነውም፣ የተፈናቀሉትን ሲጎበኙም ሆነ መልሶ ማቋቋሙ ላይ እገዛ ሲያደርጉ አላዬንም፤ እገዛ ቢያደርጉም ምናልባት መጀመሪያ ሌላውን ኢትዮጵያዊ አዳርሰው ትችት ሲበዛባቸው ለይምሰል ነው። እነዚህ ዜጎች ሲፈናቀሉ እና ሰብዓዊ መብታቸው ሲጣስ ዝምታን የሚመርጡ የዜግነት ብሔርተኝነት አራማጆች ፍላጎታቸው ምን እንደሆነ ያጠራጥራል። ሁለተኛው ማሳያ ኢትዮጵያዊ ነን የሚሉ አማራ የዜግነት ብሔርተኝነት አራማጆች ህዝቡን የማነቃነቃ አቅም ያልነበራቸውና የሌላቸው እንዲያውም አብዛኞቹ ግለሰቦች አገር ውስጥ ያልነበሩ ህዝቡ (በተለይ አማራውና ኦሮሞው) ብሔሩን መሠረት አድርጎ ታግሎ የህወሓትን የበላይነት ሲበጣጥስ አንዳች ድንጋይ ያልወረወሩ እና በተለያዩ አገራት ሆነው ትግሉን ወደኋላ የሚጎትት ፕሮፓጋንዳ ሲነዙ የነበሩ ናቸው።

አማራ የሆኑ የዜግነት ብሔርተኝነት አራማጆች የማንነት ብሔርተኞች ዘረኞች ናቸው የሚል ልብወለዳዊ ትርክት አዝለው የሚዞሩ ናቸው፤ መሽከርከሪያ ዛቢያቸውም ይህ ብቻ ነው። በእኔ እምነት ኢትዮጵያ ውስጥ ዘረኝነት አለ የሚለው አስተሳሰብ የተዛባ ብቻ ሳይሆን የተሳሳተ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ዘረኝነት ሳይሆን የማንነት ብሔርተኝነት ወይንም የብሔር ትግል ነው። ብሔር የማህበረሰብ አካል ሲሆን የማንነት ብሔርተኝነት እና ዘረኝነት በፍፁም የተለያዩ የማይመሳሰሉ ነገሮች ናቸው። ዘረኝነት የሰውን ልጅ ተፈጥሯዊ በሆነው የሰውነት አካሉ ምክኒያት ልዩነትን በመፍጠር ጥላቻን መዝራት ነው፤ በቆዳ ቀለሙ ጥቁር ወይንም ነጭ፣ በአፍንጫው ቅርጽ ደፍጣጣ ወይም ቀጥ ያለ (straight)፣ በፀጉሩ አይነት ለስላስ ወይንም ከርዳዳ፣ በቁመቱ አጫር ወይንም ረጅም ብሎ መክፈልና በእነዚህም ልዩነቶች ምክኒያት አንዱን ከሌላው በአስተሳሰቡ ያነሰ አድርጎ ማሰብ ማለት ነው። በአስተሳሰቡ የሚያንሰው ዘር (ጥቁሩ ወይንም ነጩ) በቁጥር ቢበዛ በህዝባችን ላይ አሉታዊ ውጤት ሊኖረው ይችላል ብሎ በማሰብ ይጥፋ ማለት ወይንም ለማጥፋት መንቀሳቀስ ነው ዘረኝነት። እንዲህ ዓይነት ዘረኝነት የነበረው አሁንም አልፎ አልፎ የሚስተዋለው በምዕራቡ ዓለም በአሜሪካና በአውሮጳ ነው። ለምሣሌ አሜሪካን አገር ውስጥ ሰው በዘሩ ይመደባል (White, Black, Hispanic or Other)፤ ጥቁር በአስተሳሰቡ ዘገምተኛ ተደርጎ ይታመናል፤ ከብዙ ትግልና ደም መፋሰስ በኋላ የተሻሻለ ነገር ቢኖርም አሁንም ቢሆን እንደዛ ዓይነት መድሎ ይታያል። ጥቁር ወይንም ነጭ መሆን ዘር ሲሆን አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ ወይም ሌላ መሆን ደግሞ ማንነት ወይንም ብሔር ነው። በኢትዮጵያ ሁኔታም ህወሓትም ሆነ ሌላው ጽንፈኛ ድርጅት የትግራይ ህዝብ ከአማራው ወይንም ከኦሮሞው ወይንም ከሌላው በቆዳ ቀለሙ ወይንም በተቀረው ተፈጥሯዊ አካሉ ይለያል የሚል አጀንዳ ነበራቸው የሚል እምነት የለኝም እንደዛ ዓይነት መረጃም አላየሁም። ዘረኝነት በሃይማኖትም እጅጉን የተጠላና የተወገዘ ነው፤ አማራ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብ በአጠቃላይ ሃይማኖተኛ (religious) በመሆኑ ዘረኝነትን የሚቀበልበት ሥነ-ልቦና የለውም። በመሆኑም በሌለ ነገር ላይ ፍረጃ አድርጎ መንቀሳቀስ እንዲያውም ዘረኝነት እንዲፈጠር መሥራት ነው። ይልቁን የትግራይም ሆነ የኦሮሞ ብሔርተኞች የማይወዱት በተለይ ህወሓት በጠላት ፈርጆ ሲያጠቃውና ሲያስጠቃው የኖረው አማራ የሚባለውን በእምነት፣ በባህል፣ በቋንቋ፣ በሥነ-ልቦና እና መልክዓ-ምድራዊ ማንነት ነው፤ ለዚህም የህወሓትን ማንፌስቶ ጨምሮ በርካታ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የብሔር ትግል ነው። ብሔር ማለት የጋራ ቋንቋ፣ ሃይማኖት (እምነት አይደለም)፣ ባህል፣ መልክዓ-ምድርና ሥነ-ልቦና ያለው ህዝብ ማንነቱን መሰረት አድርጎ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅሙ እንዲከበርለት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ነው። ስለዚህም ኢትዮጵያዊ ነን የሚሉ አማራዎች የማንነት ብሔርተኝነትን እና ዘረኝነትን አጥርተው ሊያዩ ይገባል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔርን መሠረት አድርገው የተደራጁ ድርጅቶች ግን ችግር የለባቸውም ማለት አይደለም። እጅግ የከፋ ችግር ያለባቸው የማንነት ብሔርተኝነትን የሚያራምዱ ድርጅቶች አለ። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ብሔርተኛ ድርጅቶች ያለው ችግር የማንነት ብሔርተኝነትን በበላይነት ብሔርተኝነት (superiority nationalism)አድርጎ ማየትና መተርጎም ነው። የህወሓትና የኦነግ ችግር የትግሬ ብሔር ወይንም የኦሮሞ ብሔር የበላይ ሆኖ በብቸኝነት በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚውና በማህበራዊው ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆን መፈለጋቸው ነው። መነሻቸውም ከአሁን በፊት አማራ የበላይ ነበር፣ ልዩ ተጠቃሚ ነበር፣ ገዥ ነበር፣ ጨቋኝ ነበር ወዘተ የሚል እና አሁን እኛ ከሌላው ብሔር የበለጠ ልንጠቀም ይገባል የሚል የልዩ ተጠቃሚነት ጽንሰ-ሃሳብ እና የሃሰት ትርክት ነው። በመሆኑም ከላይ የገለጽኩት ጽንሰ-ሃሳብና ትርጉም ህወሓትን፣ ኦነግን ወይንም ሌላ ጽንፈኛ ድርጅቶችን ለመደገፍና እነርሱ በንጹሃን ላይ ያደረሱትን ግፍ ለመደበቅ አይደለም። ህወሓት በተለይ በአማራው ላይ ያደረሰው ግፍና ሰብዓዊ መብት ጥሰት መነሻው አማራው የጥቅም ተጋሪዬ ነው እሱን አጥፍቸ ብቻዬን መጠቀም አለብኝ ከሚል የመጣ ነው። ይህ ደግሞ እንደ ሮማን ፕሮቼዝካ ዓይነት የውጭ ዜጎች ሳይቀሩ በጥናት ያረጋገጡት እና ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ይዞ ሪሶርሷን ለመሟጠጥ አማራንና ኦርቶዶክስን መምታት ይጠቅመናል ብለው ያስቀመጡት መንገድ ነው። ህወሓት የወልቃይትን እና የራያን ለም መሬቶች ወደ ትግራይ የከለለው አሁንም ለባለቤቶቹ አልመልስም ያለው በእነዚህ መሬቶች ተጠቃሚ መሆን ስለፈለገ ነው፤ የትግራይ ብሔርተኞች “ወልቃይትን መሬቱን እንጅ ሰውን አንፈልገውም” ያሉት ተልዕኳቸው የትግሬ ብሔር የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ መሆኑን የሚያሳይ ነው፤ ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ የህወሓት ሰዎች የአገሪቱን ንብረት በሙሉ የመዘበሩት እና በተቻላቸው መጠን ወደ ትግራይ ያጋዙት ከሌላው የበለጠ ተጠቃሚ የመሆን ህልማቸውን ለማሳካት መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ኦነግና ተስፋፊ የኦሮሞ ብሔርተኞች የአማራን ርስቶች የሚሻሙበትና አማራን የሚያጠፉበት ምክኒያት የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን ካላቸው ፍላጎት የመነጨ ነው። ከዚህ ውጭ ህወሓትም ሆነ ኦነግ አማራን የሚያጠፉት የፀጉሩን ዓይነት፣ የቆዳውን ቀለም፣ የአፍንጫውን ቅርጽ ወይንም የቁመቱን መጠን ስላልወደዱት ነው የሚል እምነት የለኝም፤ እንዲህ ዓይነት እምነት ያለው ግለሰብም ሆነ ድርጅት ማስረጃ ማቅረብ የሚችልም አይመስለኝም። የኦሮሞ ህዝብ በአካባቢው ያለውን ሌላ ህዝብ በሞጋሳ ኦሮሞነትን ተቀብሎ አብሮ ኦሮሞ ሆኖ እንዲቀጥል የሚያደርገው በዘሩ ስለሚጠላው አይደለም፤ በዘሩ ቢጠላውና የቆዳው ቀለም፣ የፀጉሮ ዓይነት፣ ቁመቱ እና የአፍንጫ ቅርጽ ወዘተ ዘሬን ይበክላል ብሎ ቢያስብ ኖሮ ጨርሶ ያጠፋው ነበር እንጅ አይጋባም አይዋለድም። የኦሮሞ ተስፋፊዎች ከ16ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ አማራውን ሲያጠፉት የኖሩት አማራው የርስቱን ባለቤትነት የሚጠይቃቸውንና በርስቴ ተጠቃሚ እሆናለሁ የሚላቸው ስለሆነ ነው፤ የባለቤትነት ጉዳይ ነው። አሁን በተለያዬ ጊዜ አማሮችን የሚያፈናቅሏቸው መሬታቸውን ቀምተው በኢኮኖሚ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን ነው። ሌላው ቀርቶ በአዲስ አበባ የኦሮሞ “ልዩ ተጠቃሚነት” ሊረጋገጥ ይገባል እያሉ አንዳንዴ ብቅ የሚያደርጓት አጀንዳ የችግሮች ሁሉ ምንጭ ምን እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው። አብይ አህመድ ስልጣን ከያዘ በኋላ የኦሮሞ ብሔርተኞች አገራዊ አንድነት ፈላጊዎች መስለው መታዬት የጀመሩት አሁን ያለው ሥርዓት በኦሮሞዎች የበላይነት የተያዘ ነው በመሆኑም ኦሮሞ የበለጠ ተጠቃሚ ይሆናል ብለው በማመናቸው ነው። የህወሓት የበላይነት በነበረበት ጊዜ በትግሬዎች ላይ ይነበብ የነበረው አገራዊ አንድነትን ፈላጊ የመምሰልና “ህገ-መንግሥቱ”ን ለማከበር ሲደረግ የነበረው ጥረት ህገ-መንግሥት የተባለው ሰነድ የትግሬ ብሔር ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ እና ህጋዊ ሽፋን ሰጥቶች የነበረ በመሆኑ ነው። በአጭሩ የትግራይም ሆነ የኦሮሞ ብሔርተኞች ማጥቃት የፈለጉት የአማራን ማንነት ነው፥ ይህ የሆነበት ቁልፍ ምክኒያት ደግሞ የአማራ ማንነት በአማራ ሁለንተናዊ ጥቅሞች እና እሴቶች ላይ የማይደራደር በመሆኑ ነው።

የአማራን ችግር የዜግነት ብሔርተኝነት ሊፈታው እንደማይችል የሚከተሉትን ሁለት ጥያቄዎች አንስቶ ማጥራት ይቻላል። የመጀመሪያው ጥያቄ የዜግነት ብሔርተኝነት (civic nationalism) ምንድነው የሚለውን መመርመር ሲሆን ሁለተኛው ኢትዮጵያ ውስጥ የዜግነት ብሔርተኝነትን ለማራመድ አመች ሁኔታ አሉ ወይ የሚለውን ማጤን ነው። እነዚህን ቁልፍ ጥያቄዎች መመለስ ስንችል አማራ በሁለት ጎራ ተከፍሎ እርስበርሱ የሚያደርገውን ውል የለሽ ትግል ማቆም ይቻላል የሚል እምነት አለኝ።

የዜግነት ብሔርተኝነት ማለት አንድ ህዝብ የጋራ እሴቶቹ (shared values) እና ሜሪቶቹ (merits)ን መነሻ አድርጎ የፖለቲካ ተሳትፎን እና የአገር ባለቤትነትን የሚወስንበት አካሄድ ነው። በመሆኑም አማራ የሆኑ የዚህ ብሔርተኝነት አቀንቃኞች ሊመለከቱት የሚገባው ነገር ኢትዮጵያዊያን የጋራ እሴቶች እና ሜሪቶች አሉን ወይ የሚለውን ነው፤ የዜግነት ብሔርተኝነት የሚዘራበት ዋናው ማሳም የጋራ እሴቶችና ሜሪቶች ናቸው። መሬት ላይ ያለው ሃቅ የሌሉን መሆኑን ያሳያል። ይኸውም የአንዱ ብሔር ታሪክ ለሌላው ልብወለድ (fiction) ነው፣ የአንዱ ብሔር መልካም እሴት ለሌላው ጎጅ ነው፤ አማራና ኦሮሞ በጋራ የሚስማሙበት ታሪክ ማግኘት ከባድ ነው እንዲያውም የታሪክ ገጾች በአግባቡ ይፈተሹ ካልን አብረን ለመኖር እንቸገራለን እስከዛሬም አብረን የኖርነው ከመቶ ዓመት ወዲህ ያለው አማራ ለታሪኩ ቸልተኝነት በማሳየቱ ነው። የአንዱ ብሔር ባህል ለሌላው ኋላቀር ነው፣ የአንዱ ብሔር አስተዳደር ለአንዱ ዴሞክራሲያዊ ለሌላው ጨቋኝና ኋላ ቀር ነው። በየትኛውም መልኩ በጋራ የምንስማማባቸውና የምንቀበላቸው እሴቶችና ሜሪቶች የሉንም፤ በዘመናት አብሮነት የገነባናቸው ጥቂት የጋራ እሴቶችም በክራሪና የበላይነት ስሜት በተጠናወታቸው የትግራይና የኦሮሞ ብሔርተኞች ተንዷል። በመሆኑም ኢትዮጵያ የዜግነት ብሔርተኝነትን ለማራመድ ምቹ ሁኔታ ያለባት አገር አይደለችም። ማድረግ የምንችለው እያንዳንዱ ብሔር ያለውን እሴት ጠብቆ እንደ ወርዱና ቁመቱ ተወክሉ ማንነትን መሠረት ያደረገ ፌደሬሽን መሥርቶ መኖር ወይንም የየራሱን ነጻ መንግሥት መሥርቶ እንደ አውሮጳ ዓይነት የጋራ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት መደላድል ፈጥሮ መኖር ነው። የዜግነት ብሔርተኝነት የኢትዮጵያን ችግር ያባብሳል እንጅ አይፈታም ምክኒያቱን የዜግነት ብሔርተኝነት የብሔሮችን ማንነት የሚክድና የሚንድ ነውና።

ኢትዮጵያዊ ነን የሚሉ አማራ የዜግነት ብሔርተኝነት አራማጆች የሚሰብኩት “territorial federalism” እውን ሊሆን የማይችል ነው። ምክኒያቱም የማንነት ትግል በባህሪው አንዴ ከተጀመረ የማይቆም በመሆኑና በማንነቱ ምክኒያት መነሳሳት ያሳዬ ህዝብ ከማይመስለው ህዝብ ጋር በአንድ አካባቢያዊ ጥላ ስር ለመተዳደር የማይችል መሆኑ ነው። ለምሳሌ ያህል ኢትዮጵያን ወደ አምስት አካባቢያዊ ግዛቶች ከፋፍለን ለማስተዳደር ብናስብ (የሌሎቹን ህዝቦች ይሁንታ ማግኘት አስፈላጊ መሆኑ ሳይዘነጋ) ሰሜናዊውን ግዛት የትግራይንና የጎንደር አማራን አካባቢ አንድ ላይ ማስተዳደርን ይጠይቃል ብለን እናስብ። ይህ ዕቅድ ይዞ ወደ መሬት ሲወረድ ዱሮውንም የትግራይ ብሔርተኞች በድለውኛል አጥፍተውኛል የሚል ብሶት ያለበት
የጎንደር አማራ ሰማይ ከፍ ምድር ዝቅ ብትል በአንድ አስተዳደር ሥር መሆንን የሚቀበለው አይሆንም። እንዲያውም ከአሁኑ የበለጠ ቀውስ
ይፈጥራል። ከዚህም በተጨማሪም የማንነት ልዩነት ያለ በመሆኑ ከላይ የተጠቀሰውን ዓይነት አስተዳደር ለመፍጠር አይመችም። ስለዚህ ዞሮ ዞሮ አማራውን በአንድ፣ ኦሮሞውን በአንድ፣ ትግሬውን በአንድ አድርጎ አስተዳደራዊ ግዛት መፈጠሩ አይቀርም ይህ ደግሞ ነገሩን አልሸሹም ዞር አሉ ያደርገዋል። አጭሩ መፍትሔው የህወሓት ብሔርተኞች
የተጫዎቱበትን የማንነት ብሔርተኝነት በትክክለኛ አቋሙ ሁሉም ህዝብ እንደ ወርዱና እንደ ቁመቱ ታሪካዊ መሠረቱንና ህዝባዊ ፍላጎቱን ጠይቆ ማስተዳደር ነው።

በነገራችን ላይ የህወሓት ወያኔ መንግሥት እንደ ኢትዮጵያዊ ነን ብለው ራሳቸውን እንደሚገልፁት የአማራ ምሁራን ጢባጢቤ የተጫዎተበት አካል የለም። ህወሓት አናሳ ቡድን መሆኑንና በሥልጣን ለመቆየት አብዛኛውን የሕብረተሰብ ክፍል ዘወትር በተቃዋሚነት እንዲሰለፍና የሥልጣን ድርሻ እንዳይኖረው ማድረግ እንዳለበት ገና ቀድሞ የተረዳ ቡድን ነው። በመሆኑም የማንነት ብሔርተኝነትን ለሰለጠነ ህዝብ አይመጥንም የሚል ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ተማርኩ አወኩ የሚለው ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው የአማራ ክፍል የማንነት ብሔርተኝነትን ሳያውቅ እንዲሸሸው ፕሮፓጋንዳ ሰርቷል። ፕሮፓጋንዳውን እጅግ ውጤታማ ያደረገው ደግሞ የማንነት ብሔርተኝነት ጽንሰ-ሃሳብ አዲስና በተለይ በሥርወ-መንግሥት ይተዳደር የነበረ ህዝብ ሊቃወመው እንደሚችል በአግባቡ የተረዳ መሆኑ ነው። በአንድ ነገር ላይ የበላይነት ለማግኘት አጭሩ መንገድ ነገርዬውን በጭፍን የሚቃወመው ቡድን መፍጠር መቻል ነው፤ ጭፍን ተቃውሞ ዘወትር ተሸናፊ ነው ምክኒያቱም ራሱን ለውይይት የማይጋብዝና ሞግቶ ለመርታት የማይሞክር ግትር አቋም ያለው አካል መቼም አያሸንፍም። ከዚህም በተጨማሪ
ኢትዮጵያዊ ነን በሚሉ የአማራ ምሁራን ጭንቅላት ውስጥ ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን በመጫን በግለሰብ ደረጃ ራሱ ከራሳቸው ጋር እንዳይስማሙ
አድርጓል። ይኸውም በአንድ በኩል በማንነት ብሔርተኝነት ምክኒያት የዓለም የፖለቲካ ቁንጮ የሆኑትን ምዕራባዊያንን በተለይ አውሮጳዊያንን እንዲያደንቁ በሌላ በኩል “የሥርወ-መንግሥት” አድናቂና ጠበቃ እንዲሆኑ አድርጎ በራሳቸው ፓስወርድ ጭንቅላታቸውን የቆለፈባቸው መሆኑ ነው።

የገሃዱ ዓለም እውነታ ይህ ነው። በዓለም ላይ ካሉ አገሮች መካከል ከስድስት ማለትም ከግብፅ፣ ሰሜን ኮርያ፣ ደቡብ ኮርያ፣ ሌሴቶ፣ አልጀርያ እና ሞሮኮ በስተቀር በአንድ ብሔር ብቻ የተገነባ አገር የለም። በሌላ አባባል ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑት የዓለም አገራት የብሔር መድብሎች (multi-ethnic nations) ናቸው ማለት ነው። በአንዲት አገር ውስጥ በርካታ ብሔሮች መገኘታቸው አስደናቂም፣ አስገራሚም፣ መጥፎም ጥሩም አይደለም፤ በአጭር ቋንቋ የተፈጥሮ ሃቅ ነው። ይሁን እንጅ በኢትዮጵያ ከ40 ዓመት ገደማ ወዲህ ጀምሮ መደበኛ የፖለቲካ አጀንዳ ሆኗል ይህም እንደ እስካሁን እንደ ብርቅ እየታየ ይገኛል። ነገር ግን ይህ በሌላው ዓለም በተመሣሣይ ሁኔታ የተከሰተ ነው፤ የማንነት ብሔርተኝነት መስፋፋትም እንዲሁ አስደናቂም አስገራሚ ነገር አይደለም።

ኢትዮጵያ ውስጥ የማንነት ብሔርተኝነት ብቅ ብቅ ማለት የጀመረው ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያ ትተዳደርበት የነበረው የሰለሞናዊ ሥርወ-መንግሥት ዘመናዊነትን መላበስ ሲጀምር ነው። በተለይም አውሮጳዊያን አፍሪቃን ለመቀራመት ጎራ ማለታቸው ኢትዮጵያ ሳትወድ በግድ የምዕራቡ ዓለም ሥልጣኔ እንዲያሳስባት አድርጓታል። የኢትዮ-ጣሊያንን ጦርነት በጀግንነት የመሩትና ለድል ያበቁት ታላቁ ጥቁር ሰው እምዬ ምኒልክ ንጉሠ-ነገሥት ዘ-ኢትዮጵያ ጣልያን በዘመናዊ መሣሪያ መታጠቁን ሲያዩና በአጠቃላይ አውሮጳዊያንን ወደ አፍሪቃ የመጡት ስለሰለጠኑ መሆኑን ሲረዱት ስልጣኔን አብዝተው መሻት ጀምረዋል። ከውጭ አገር መንግሥታት ጋር በመቀራረብ እንደ ባንክ፣ የፖስታ አገልግሎት፣ መኪና፣ ሆቴል፣ ስልክ ወዘተ የመሳሰሉትን ነግሮች ወደ ኢትዮጵያ አስገብተዋል። በዚህም ምክኒያት ዘመናዊ ትምህርት አገርን ሊለውጥ እንደሚችል እና ብልጥግናን ለማምጣት እንደሚያስችል ቀስ በቀስ በህዝቡ ውስጥ ግንዛቤ እንዲፈጠር አድርገዋል። የህዝቡ ግንዛቤ ማደግ ያልታሰበ ነገር ግን ተያያዥ የሆነ ችግር ይዞ መጥቷል ይኸውም ንጉሡና ንጉሣዊ ቤተሰቡ የበለጠ ተጠቅሟል የሚሉና ጭሰኛው ተጠቃሚ አይደለም፤ ከበርቴው አላግባብ በልጽጓል ወዘተ ዓይነት የማህበራዊ ፍትህ በህዝቡ ውስጥ ብቅ ብቅ እንዲሉ አስችሏል። እንግዲህ በዚህ መነሻ ነው እነ ወያኔ መጠንሰስ የጀመሩት።

በአውሮጳ የታየው የማንነት ብሔርተኝነት አጀማመርም ተመሳሳይነት ያለው ነው። አውሮጳና እስያ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ በኢምፓዬር ሲገዛ የኖረ ህዝብ ነው። የከተሞች መስፋፋት፣ የትምህርት መስፋፋት፣ የፖለቲካ ንቃት መጨርና፣ የሥነ-ተዋልዶ እና የምጣኔ ሃብት ዕድገት ልዩነት የአውሮጳን ብሔርተኘት እንደወለዱት ይታመናል። የአውሮጳ አህጉር በማንነት ብሔርተኝነት
(ethnonationalism) እጅግ ብዙ ትግል የተደረገበት ምድር ነው። እንደ ጄሪ ሙለር ያሉ የታሪክ ምሁራን የማንነት ብሔርተኝነት አውሮጳን አሁን ወደምትገኝነብት መረጋጋት የመራ ውጤታማ እንቅስቃሴ ነው በማለት ይሞግታሉ።

ከ19ኛው ክፍለ-ዘመን ቀደም ብሎ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ፖርቹጋል፣ ስፔን እና ስዊድን የመሣሰሉት አገሮች ብሔረ- መንግሥታት (nation-states) የነበሩ ቢሆንም በባህልና ማህበረሰባዊ መስተጋብር ጥንካሬ ምክኒያት በብሔሮች መካከል ልቱነቶች አይስተዋሉም ነበር። የመካከለኛው አውሮጳ ከመቶ በላይ በሚሆኑ አነስተኛ አካባቢዎች የተከፋፈለና ጣሊያንኛና ጀርመንኛ ተናጋሪዎች የሚበዙበት ነበር። እ.ኤ.አ በ1860ዎቹ እና ’70ዎቹ በእነ ጁሴፔ ማዚኒ በመሳሰሉት አመካኝነት ጣሊያን አገር ሆነው ሲቆሙ ብጥስጣሾቹ መልክ ያዙ።

ወደ 1914ዎቹ አካባቢ የመካከለኛው፣ ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ አውሮጳ በኤምፓዬሮች የሚተዳደር ነበር። ኦስትሪያ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ሃንጋሪ ስሎቫኪያ እና አሁን ቦስኒያ፣ ክሮሽያ፣ ሮማንያ፣ ፖላንድ፣ ዩክሬን ወዘተ በሀፕስበርግ ኢምፓዬስ ስር ነበሩ። የኦቶማን ኢምፓዬር ደግሞ የአሁኗን ቱርክ፣ ግሪክ፣ ቡልጋሪያ፣ ሰሪቢያንና እስከ ታች ዘልቆ የሰሜን አፍሪቃ አገራትን ያጠቃልል ነበር። የሮማኖቭ ኢምፓዬር ደግሞ እስከ እስያ ጫፍ የተዘረጋ ሲሆን ያሁናን ሩሲያን እና የተወሰነውን የዩክሬንና ፖላንድ ግዛት ያካልል ነበር። የአገራቱ ስብስብ እንደሚያሳየው እንደ ኢትዮጵያ ዘውዳዊ አገዛዝ ሁሉ የአውሮጳ ኢምፓዬሮችም በውስጣቸው የብሔር መድብል (multiethnic) የነበራቸው ናቸው። ነገር ግን ብሔርን መሠረት ያደረገ የሥልጣን ክፍፍል ወይንም ውክልና አልነበረም። እስከ 19ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ ደግሞ አብዛኛው የኢምፓዬሩ ነዋሪ በግብርና ሥራ የሚተዳደር እና በትምህርት እጅግም ያልገፋ ነበር። ብሔርን መሠረት ያደረገ ምንም ችግር አልነበረም ለምሳሌ አይሁዶች በየትኛውም ቦታ ይኖሩ ነበር እምነታቸውን መሠረት በማድረግ መንግሥትም ሆነ አገር አልመሰረቱም ነበር። በተመሣሣይ ጀርመኖችና ግሪኮች ከኢምፓዬራቸው ውጭ በተለያዬ ቦታ ይኖሩ ነበር። ብሔርተኝነት በዘመናዊ መልክ መቀንቀን ሲጀምር ይህ ሁኔታ ተለዋውጧል።

ዘመናዊነት በአውሮጳ ማበብ ሲጀምር ነገሮች ተለዋውጠዋል። በመንግሥታት (states) መካከል የነበረው የወታደራዊ ኃይል ውድድር ተጨማሪ ሪሶርስ ፍለጋ ግዛታቸውን እንዲያሰፉና የኢኮኖሚ አቅማቸውን እንዲያጠናክሩ ግድ ብሏቸዋል። የኢኮኖሚ ዕድገቱ በበኩሉ በብዛት የተማረ ህዝብና ቀላል የመገናኛ ዘዴ (easy communication) እንዲኖር በማስገደዱ ምክኒያት የጋራ ቋንቋ አለመኖሩና የትምህርት አቀርቦት ያለበት ርቀት ወይንም ተደራሽነት ብሔር ተኮር ግጭቶችን ሊፈጥር ችሏል። በከተሞች የሚኖረው የተማረው የሰው ኃይል የተመቻቸ ወይንም ከገጠሬው የተሻለ ኑሮ የነበረውና የበለጠ ተጠቃሚ የነበረው ነው። በዚህም ምክኒያት በ19ኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻና በ20ኛው ክፍለ-ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በስፋት ገበሬ ማህበረሰብ የነበራቸው እነ ቼክ፣ ፖላንድ፣ ስሎቫኪያና ዩክሬን ወደ ከተሞች በመፍለስ መማር ጀመሩ። ይሁን እንጅ ቁልፍ የሥራ ቦታዎች በግሪኮች፣ በአርመናዊያን፣ ጀርመኖችና አይሁዶች ተይዘው ነበር። ይህ ሁኔታ ተመሳሳይ ቋንቋ ይናገሩ የነበሩትና ሥራ ያጡት በተጠቂነት ስሜት የጋራ ሥነ-ልቦና ፈጥረው እነርሱ የሚያዙበት፣ የሚመሩትና የሚያስተዳድሩት ሊኖረን ይገባል የሚል ትግል እንዲጀምሩ ምክኒያት ሆኗል። በመሆኑም የ20ኛው ክፍለ-ዘመን የአውሮጳ ታሪክ አሁን እኛ አገር እንደሚታዬው አይነት ገጽታ የነበረው ነው። ዜጎች በራቸው ፈቃድ እነርሱን ወደሚመስል ብሔር ተሰደዋል፣ መንግሥታት የህዝብ ቅይይር (population trandfer) አድርገዋል፣ ሰዎች በግድ አንድን አካባቢ እንዲለቁ ሆኗል አልፎም ተርፎም አርመናዊያ የዘር ማጥፋት (ethnic cleansing) ሰለባዎች ሆነዋል ተያይዞም ኢምፓዬሮች ፈርሰው የማንነት ብሔርተኝነት (ethnonationalism) ጦፈዋል። የአንደኛው እና የሁለተኛው ዓለም ጦርነት አንዱ ህዝብ ሌላውን የማፈናቀል፣ የእኔ ብሔር የበላይ ነው የማለት ወዘተ ነበር።

በሁለተኛው ዓለም ጦርነት መገባደጃ ላይ የዘመኑ ኃያላን መሪዎች ዌንስተን ቸርችል፣ ፍራክሊን ሩዝቤት እና ጆሴፍ ስታሊን ወዘተ መፍትሔ አበጅተው የተረጋጋ የአውሮጳ አካባቢን ለመፍጠር እስከቻሉበት ጊዜ ድረስ ብሔርን መሠረት ያደረገ ትግል ለዘመናት ተካሄዷል። የብሔር ትግል ማሳረጊያ የተገኘለት ጀርመኖች ከያሉበት ሁሉ ተፈናቅለው ወደ ጀርመን ሊመለሱ ይገባል የሚል መደምደሚያ ከላይ በተጠቀሱት ሶስት መሪዎች ከመጣ በኋላ ነው (the expulsion of ethnic Germans from non-German countries was a prerequisite to a stable postwar order) ።

እ.ኤ.አ በ1944 ዓ.ም ዊንስተን ቸርችል ለብሪቲሽ ፓርሊያመንት የሚከተለውን ንግግር በዴሴምበር 1944 አድርገው ነበር።

“Expulsion is the method which, so far as we have been able to see, will be the most satisfactory and lasting.There will be no mixture of populations to cause endless trouble. . . . A clean sweep will be made. I am not alarmed at the prospect of the
disentanglement of population, nor am I alarmed by these large transferences.”

ከዚህ በኋላ እ.ኤ.አ በ1947 ዓ.ም አካባቢ ወደ 12 ሚሊዬን የሚሆኑ ጀርመናዊያን መፈናቀል ደርሶባቸዋል። “Anti-Seminism” በመስፋፋቱ ምክኒያት ወደ 220,000 የሚሆኑ አይሁዳዊያን ከአውሮጳ ተሰደው አሜሪካ ቀሪዎቹ ደግሞ እስራኤልን መሥርተዋል። ወደ 1.5 የሚሆኑ ፖላንዳዊያን ከሶብየት ህብረት ተፈናቅለዋል በምትኩ ወደ 500,000 የሚሆኑ ዩክሬናዊያን ከፖላንድ ተፈናቅለው ወደ ሶቭየት ዩክሬን ተሰደዋል። ተመሳሳይ መፈናቀሎች ተደርገው በአንድ አካባቢ የሚኖረው ህብዝ ከሞላ ጎደል ከአንድ ብሔር የተወጣጣ ሲሆን ራሳቸውን የቻሉ ብሔረ-መንግሥታት (nation-states)
ተፈጥረው አውሮጳ የተረጋጋ አህጉር ሊሆን ችሏል።

ኢትዮጵያዊ ብለው ራሳቸውን የሚገልፁ አማሮች ኢትዮጵያ ውስጥ እየታዬ ያለው ሁኔታ ከዚህ የተለየ አለመሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል። ከ3 ሚሊዮን የሚልቁ አማሮች ከተለያዩ ክልሎች ተፈናቅለዋል፤ ወደ 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ኦሮሞዎች ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለዋል። አገሪቱ ውስጥ የሚታየው የብሔር ፍጥጫ አሁን ባለበት ሁናቴ የሚቀጥል ከሆነ ምናልባት በቀጣይ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ትግሬዎች ልክ እንደ ጀርመኖች ከአሉበት ወደ ትግራይ ክልል እንዲመለሱ የሚደረግበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። ምናልባትም ልክ እንደ አውሮጳዊያኑ ከብዙ ምስቅልቅና ውጣ ውረድ በኋላ የተረጋጋችና በብሔረ-መንግሥታት ትብብር የምትመራ ጠንካራ አገር ወይንም አካባቢ ልትፈጠር ትችላለች የሚል መላምት ማስቀመጥ ይቻላል። በመጨረሻ ዎልከር ኮነር በተባለ ብሔርተኛ ንግግር ሃሳቤን ልቋጭ፤

“It is not what is, but what people believe is that has lasting consequences.”

በተጨባጭ ሁኔታ ህዝቡ ሊቀበለው ከማይችለውና ለመተግበር በማይቻል የዜግነት ብሔርተኝነት ይልቅ በህዝብ ልብ ውስጥ ያለውን የማንነት ብሔርተኝነት በአግባቡ መርቶ ደም መፋሰስን በጊዜ አስቀርቶ የተረጋጋ አካባቢን በመፍጠር አማራውን ከጨርሶ መጥፋት መታደግ ለነገ የማይባል ሥራ ነው።

የአፄ ቴዎድሮስ እውነተኛው ማንነትና ራዕየ ምግባር (Tedla Melaku)

አፄ ቴዎድሮስ እንኳን ኦሮሞ ሊሆኑ ቀርቶ የዘመነ መሳፍንቱን የኦሮሞ መስፋፋት ያከሰሙት እርሳቸው ናቸው። ብዙ ሰው የማያውቀው ወይንም ያላስተዋለው ሐቅ አለ። የመቶ ዓመቱ ዘመነ መሳፍንት ይመጣው በኦሮሞ መስፋፋት ምክኒያት ነው። ኦሮሞዎች ጎንደር ድረስ ከደረሱ በኋላ መንግሥቱ ተዳክሞ ከነበረው አምሓራ ጋር ተቀናቃኝ መሆን ጀመሩ።

በነርሱ ዘመን የአምሓራና የትግሬ መሳፍንት ከኦሮሞው ኃይሎች ጋር እየተዋጉ የጎንደር አማራ ነገሥት ኃይል እየቀነሰ ኃይል በክፍለ ሀገር ገዥ ልዑላን ላይ መወሰን ጀመረ። እነርሱም የየራሳቸውን ፍላጎት የሚከተሉን ሰሎሞናዊ አማራ ልዑላን በፈቃዳቸው ማንገሥ ጀመሩ። በኦሮሞው በኩል የሐበሻውን ባሕል ተከትለው ደጃዝማችና ራስ እየተባሉ ፖለቲካው ላይ ተጽኖዋቸው እየጨመረ ሄደ።

በዚህ ዘመን የመጨረሻው ባለ በላይ ሥልጣን አማራ ንጉሠ ነገሥት ወጣቱ የአፄ አድያም ሰገድ ኢያሱ የልጅ ልጅ ዳግማዊ አፄ ተክለ ሃይማኖት ነበር ማለት ይቻላል። እርሱም ግን በራስ ሚካኤል ስሑል ድጋፍ የነገሠና ከራስ ሚካኤል ጋር ያበረ ነበር። ከርሱ በኋላ የነገሠውም የርሱ ወንድም ቀዳማዊ አፄ ተክለ ጊዮርጊስ (ፍቅር ሰገድ) “ፍጻሜ መንግሥት” ይባል ነበር። እንዲህ የተባለው እርሱ የመጨረሻው ሰሎሞናዊ [አማራ] ንጉሠ ነገሥት ይሆናል ተብሎ ስለታመነና የሐበሻው መንግሥት በርሱ ዘመን ያበቃለታል ተብሎ ስለታሰበ ነበር።

ከቀዳማዊ ተክለ ጊዮርጊስ በኋላ የነገሡት የጎንደር ሰሎሞናዊ አማራ ነገሥታት አፄ ቴዎድሮስ እስከሚነሳ ድረስ አቅምና ሥልጣናቸው በጣም ውስን ነበር። ቤተ መንግሥቱ የሚውሉበት በድን ስፍራ ሆኖ ነበር። እነዚህ ነገሥታት እነ አፄ ዲሚጥሮስ፣ እነ አፄ ሕዝቄያስ፣ እነ አፄ ጊጋር፣ ሣልሳዊ አፄ ዮሓንስ፣ እነ አፄ ሳሕለ ድንግል ነበሩ። አፄ ቴዎድሮስ የተነሳው በአፄ ሣልሳዊ ዮሓንስና በአፄ ሣሕለ ድንግል ዘመን ነበር። በታሪክ መጻሕፍት እንደ ተጻፈው የቴዎድሮስ ዋንኛ ዓላማ ኦሮሞዎችን ከሐበሻው መንግሥት ማስወጣትና የክፍለ ሀገራቱን መሳፍንት ከንጉሥ ስር ዳግም ማስተዳደር፣ እንዲሁም የጠፋውን መንግሥት መመለስ ነበር። ሥልጣን እንደያዘ ዙፋኑን ወደ መቅደላ አዙሮ የኦሮሞ ኃይሎችን መውጋት ጀመረ። ድል እያደረገ ከጎንደርና ከአማራው ምድር ተጽእኖ ከነበራቸው ቦታዎች ሁሉ አስወጣቸው።

የኦሮሞውን ኃይል ድል ካደረገ በኋላ ነው የሸዋን፣ የትግሬን፣ የጎጃምን ነገሥታት ከስሩ አድርጎ በመካከላቸው አንድነት እንዲኖር ያደረገው። እንድያውም ቴዎድሮስ እንደ መሲሕ የታየው የዘመነ መሳፍንት መምጣት ምክኒያት የነበረውን የኦሮሞ ኃይል ድል በማድረጉ፣ ከዚያም በክፍለ ሀገር የየራሱን ነጻ መንግሥት የመሰረተውን ከርሱ ስር ወደ አንድ በማምጣቱ ነበር።

አፄ ቴዎድሮስ ለንግሥት ቪክቶሪያ የጻፈው ደብዳቤ (ከታች አያይዤ በቀይ እንዳሰመርኩት) እንዲህ ይላል።

“አባቶቼ አምላካቸውን ስለረሱ እግዚአብሔር መንግሥታቸውን ለኦሮሞ አሳልፎ ሰጠባቸው:: ነገር ግን እግዚአብሔር እኔን ፈጥሮኝ መንግሥቱን ከነርሱ እጅ በእኔ አስመለሰ። እርሱ በሰጠኝ ኃይል ኦሮሞዎችን አሸንፌ አስወጣኋቸው።”

ይህን የጻፈው አምሓራው አፄ ቴዎድሮስ ነው። እናም ታሪክ የምታጠፉ ሰዎች ብዙ ዘንዶ እንዲወጣ እያደረጋችሁ ነው።

ምንጭ
“Ancient Cities and Temples: Ethiopia”, by Jean Doresse (Archaeologist and Historian, Authority on Ethiopian Studies)
“The Royal Chronicle of Abyssinia: 1769-1840”, (translated from Classical Ge’ez by Weld-Blundel)
“King of Kings: Tewodros of Ethiopia”, Sven Rubenson, p. 75.
“A History of Africa: Vol. I: African Societies and the Establishment of Colonial Rule 1800-1915”, p. 279.

NaMA and the Amhara Question.. (በመልካሙ ሹምዬ ኮከብ)

The Roots of Our Plight:

The Ethiopian Student Movement ignited in the 1960s hijacked by the extremist ethno nationalists who were inspired by the aborted Fascist Italy colonial policy and strategy of alienating the Amhara from other nationalities to conquer and rule Ethiopia, brought ‘the Question of Nationalities’ that argued Ethiopia was not yet a nation but Amhara – dominated and ruled collection of dozens of nationalities with their own languages, ways of dressing, history, social organization and territorial entity. They claimed the Amhara denied the recognition and dignity of these nationalities, subjugating and suppressing them. The Eritrean and Oromo nationalists took further the narration to the extreme, made their intention clear of liberating their people from ’Abyssinian colonial rule.’ The Tigrian elites followed suit.

The Dergue, devoid of an ideology of its own, run by and dominated by ethno nationalist elites mainly the Oromo, was also essentially anti Amhara. Under the guise of socialism, it liquidated the Amhara elite, confiscated hard earned properties of our people. The Dergue regime assisted by the Oromo dominated All Ethiopia Socialist Movement (Ma’ison), the Ethiopian Oppressed Peoples’ Revolutionary Struggle( Ich’at) was the first that posed existential threat of the Amhara by annihilating the economic and elite base of the Amhara people and paved the way for subsequent persecutions conducted on our people.

The systemic assault carried out on our elites left the people of Amhara defenseless and following the fall of the Dergue regime, the trident Eritrean Peoples’ Liberation Forces (EPLF), Tigray Peoles’ Liberation Front (TPLF) and Oromo Liberation Front (OLF) got the opportunity to deconstruct the country without a single hindrance. EPLF ‘liberated’ Eritrea from Ethiopia and established an independent state. TPLF with its surrogates under the name of Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF) and OLF established an ethnic based federal system which severely dismembered the integrity, unity and safety of the Amhara people. The very fertile, historical and strategically important territories of the Amhara people were incorporated to Tigray (Wolqayt,Tsegede, Tselemet and Raya), Oromiya (Shewa), and Beni Shangul(Metekel), as well effectively gerrymandering the people to suppress their votes and forcing them to abandon their identity in an unprecedented manner. TPLF and its surrogates drafted and enacted the current so called ‘Federal Democratic Republic of Ethiopia (EFDRE) constitution’. Genuine representatives of the Amhara people such as Amhara People Organization (AAPO) and its leader Professor Asrat Woldeyes were deliberately persecuted and excluded from the process. The interests, aspirations, voices and consent of the Amhara people were willfully excluded and ignored. The federal government also introduced different policies and laws in the name of reform and proportionality that undermined and hurt the Amhara people in every aspect of life.

Empowered by the direction set by the federal constitution, regional states wrote their own constitutions excluding and denying even the very existence of millions of Amhara people living within their new ‘constituency.’ This gave states and their officials wide and undeterred power to do whatever they wanted to do on the Amhara people, which resulted in gross and widespread human rights violations such as mass killings, mass displacement, property damage, institutional discrimination and insecurity to name a few. This absolute lawlessness has caused so much horror and ethnic cleansing on the Amhara people in a large scale unheard in the recent history of Ethiopia. The regime in power implemented different racist policies against the Amhara people such as population control, forced mass sterilization and numerical genocide to make it insignificant minority and downsize its political representation and power. The Amhara people who lived outside the ‘Amhara Region’ become literally stateless and even the people who lived in ‘The Region’ have been deliberately neglected, impoverished and underdeveloped denying all development programs and basic infrastructures.

Adding insult to injury, the very hateful and demonizing propaganda being propagated relentlessly against the Amhara people by TPLF and its surrogates has exacerbated the misery. Hating, demonizing, degrading and labeling the Amhara people (as Nefetegnas and chauvinists) who subjugated ‘’ the Nations, Nationalities and Peoples’’ of the country was and is the order of the day. The ruling elites reward political cadres who belittle and degrade the Amhara and accorded them the name ‘progressive.’ The hateful propaganda has worsened the Amhara misery by feeding a continued anger and false reason to attack them. The Amhara were and are the scapegoats whatever goes wrong in our country and hence bear the costs.
The threats were/are; policy oriented, very systematic and highly institutionalized, critically compromising our very survival. All the anti Amhara constitution, the system built upon it and the institutions installed are still intact bleeding us day and night.

The Amhara Question: What is in its Name?

The cumulative effects of the above atrocities and threats are: political under/unrepresentation; economic, social and cultural marginalization; property dispossession, abject poverty, and mass displacement; and loss of life with the level of genocide and ethnic cleansing. What is worrying is that they are deepening and increasing at an alarming rate and they are expected to stay same in the near future. AND all these have caused the very survival of the Amhara as a nation at stake and they failed us miserably as a nation. The fact that the great nation of Amhara has faced a multifaceted existential threat is what I call the Amhara Question. The Amhara Question is not all about democracy and development. Of course the Amhara badly needed democracy and development probably more than any group in this country. BUT it seems luxury right now to fight for democracy and development only. The Amhara first must ensure their very survival as a nation. It has to reverse the survival threat before it is too late. Unless the true sons and daughters of the Amhara take fast, coordinated and swift response to the threat, it may unfold great human tragedy in the horn of Africa. The great nation of Amhara may fall miserably and its great civilization may be forgotten. It is understandable that the threat is posed against the Amhara as a group; hence it is to be neutralized by disciplined and organized Amhara.

Amhara Nationalism: A panacea to the Amhara Question?

Amhara nationalism is nothing but a national political movement which is initiated and got momentum by Amharas annihilation and marginalization in every walk of life of the country and above all by the survival threat the nation of Amhara has faced under the TPLF/ODP/OLF led regime. It is an awakening movement which critically observes and acts every course of action and intention in a way that can protect the rights, vital interests and dignity of the Amhara people. It is very much clear that the Amhara have faced survival threat as a nation. And it is imperative to awake and defend it as an Amhara nation. The fact that the existential threat of Amhara people was/is/will not be a political agenda for the so called ‘Pan Ethiopianists’ tells us loudly, it is to be owned and answered only by Amhara nationalists. Time and again these false unionists overlooked the Amhara plight and some even embrace Amhara’s sworn enemies intentions and actions, putting stumbling blocks on the ways of Amhara Resistance. Hence, Amhara nationalism is the only panacea to the Amhara Question. Amhara Nationalism emanates from the real threats of our people, it is based on BOLD FACTS, it does not have any intention of domination, and does not label any people as enemy like those ethno nationalists who did it on the Amhara. Above all, it believes and struggles to a negotiated new constitution and constitutional order in which all Ethiopians will participate and most Ethiopians will approve it; A federal system that respects the indivisibility of our people’s unity and our historical territorial integrity.

National Movement of Amhara (NaMA): Built on Amhara Nationalism and fighting to answer the Amhara Question.

Against all adversities, the Amhara people have not got a genuine political party which is a product of Amhara nationalism and which in turn help blossom Amhara nationalism except the AAAPO which was vibrant for a couple of years before it was curtailed by the ruling regime in the 1990s. The Amhara National Democratic Movement (ANDM) has proved itself in its establishment, composition, narration and action anti Amhara in leaps and bounds. It has failed the Amhara people miserably. Saving its change of name to Amhara Democratic Party (ADP) last year, it has not changed its trend and failed to deliver on the legitimate expectations of our people.
For the last three years, Amhara nationalism is becoming the guiding political thought of the Amhara youth and has showed great leap forward after 2008 E.C following the Amhara Resistance which broke out in the historic city of Gondar where Colonel Demeke Zewedu (Wolqayt Amhara Identity Committee Chairman) defended himself and the CAUSE from death squad officers sent mid night to kidnap and kill him. After that spectacular, historic, and an act of heroic event, everything turned upside down and as they said the rest is history.
Nevertheless, the growing Amhara nationalism was not organized and formalized especially with in Ethiopia. That has to come to an end. The true sons and daughters of the Great Nation of Amhara have joined hands together and gave birth to the National Movement of Amhara (NaMA). Within a short span of time NaMA has garnered huge support and is venerated by the Amharas everywhere. It is cruising responsibly and is articulating the Amhara Question clearly and cleverly. It is also spreading and deepening Amhara nationalism as a viable and lone alternative for the Amhara CAUSE for millions and is embraced by many every day. The very fact that NaMA has made its political movement on the foundations of equality and justice has created hope in other ’minority nationalities’ that have real threat to be swallowed by supremacist groups that want to dominate and assimilate them. NaMA is defending the interests of the Amhara people, balancing political power in Ethiopia by challenging and checking those who are trying to monopolize everything and anything. This will help Ethiopia and its people to democratize by bringing the real political actors to the negotiation table.
The fact that NaMA is welcomed and accepted by many is an assurance that it is the right party to advance Amhara nationalism, pursue the real interests of our people and answer the Amhara Question. We can say that NaMA will be the vanguard of the Amhara, that it will bring the people of Amhara together and organize our people. Under NaMA’s leadership, we will neutralize the existential threats of our people, ensure our survival, and defend the rights, interests, aspirations and dignity of the Amhara people, and secure a federal system that respects the indivisibility of our people’s unity and our historical territorial integrity.
NaMA will struggle relentlessly to bring equality and justice as the very foundations of our Ethiopia, and it will stand for a constitutional order built by the participation of all Ethiopians and accepted by the majority of Ethiopians.

ፍትህና ሚዛናዊነት የት ነሽ? (Getachew shiferaw)



ባለፈው አንድ አመት፣ ኦሮሚያ ክልል ጅማ ውስጥ ከተፈፀሙት በደሎች በጥቂቱ:_

1) ከመጋቢት 5 ቀን 2010ዓ.ም. እስከ ሚያዝያ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ፣ ከ15 በላይ ክርስቲያኖች በአሠቃቂ ኹኔታ ተገድለዋል፡፡ እየደረሰ ባለው ግድያ፣ ዝርፊያ፣ የቤት ድብደባና ዛቻ ምክንያት፣ 185 አባወራ እና 13 ቀሳውስትና ዲያቆናት በድምሩ 198 አባወራዎች ከቀዬአቸው ተፈናቅለው ተሰደዋል፡፡

2) አቶ ገበየሁ ወርቅነህ የሚባሉ፣ ታዋቂ ባለሀብትና ቀደምት የአካባቢው ነዋሪ፣ ልጆቻቸውን ኹሉ እዚያው ወልደው፣ ድረው፣ የልጅ ልጅ አይተዋል፡፡ ኾኖም አሁን፣ ንብረታቸውን ኹሉ ትተው፣ ቤታቸውን ዘግተው ወጥተው ተሰደዋል፤ እንደ እርሳቸው ኹሉ ሌሎች ብዙ ንብረት ያላቸውም ተሰደዋል፡፡

3) ጥር ወር 2010 ዓ.ም.፣ የአቶ ጉባይ አደራው ቤትን ሌሊት በመስበር ወደ ውስጥ ሲገቡ አምልጧል፡፡ እርሱን ለመምታት ሲታኮሱ እርስ በርስ ስለተመታቱ (አንዱ እጁ ላይ ተመትቷል)፣ “እርሱ ነው እንዲህ ያደረገን” በማለት ቤቱ ውስጥ ያለውን ንብረት አውድመው ቤተሰቡን አሳድደዋል፡፡ የተመታው ላይ ትኩረት ሲያደርጉም፣ ሚስቱና ልጆቹ ወጥተው ተሰውረዋል፡፡ ጥሩ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበረ ሲኾን፣ በአካባቢው ያሉ ከፍተኛ ጥቃቶች በግላጭ የተጀመሩት በእርሱ ላይ ነው፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የት እንደ ገባ አልታወቀም፡፡

4) ብዙአየሁ እንዳሰኘው የተባለ ምእመን ተገድሎ ጫካ ውስጥ ተጥሎ ተገኝቷል፤ ችግሩ የተጀመረው የካቲት 13 ቀን 2010 ዓ.ም ነው፡፡

5) መጋቢት 3 ቀን 2010 ዓ.ም ደግሞ፣ አካባቢውን ለቅቀው ዕቃቸውን በተሸከርካሪ ላይ ጭነው ሲወጡ፣ ግርማ ጋሹ እና ፋንታ ታሪኩ የተባሉ 2 ሰዎችን ከተሸከርካሪው አስወርደው የኋሊት አስረው ገደሏቸው፤ ሹፌሩ ያየውን በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ቀርቦ አመልክቷል።

6) ግንቦት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. አካባቢ አቶ ጋሻው ታመነ የሚባለውን ምሽት 2፡00 ላይ በገደሞ(ገጀራ መሰል ብረት) አንገቱን በመቁረጥ ገደሞውንም ጥለው ሒደዋል፤ የጣር ጩኸት ሲያሰማ ሰው ቢደርስም፣ ወዲያው ነፍሱ ከሥጋው ተለይታለች፡፡ ጋሻው ትዳር ያልያዘ ወጣት ሲኾን፣ ቤተሰቦቹ (ወላጆቹና ወንድም እኅቶቹ) እዚያው ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ቀብረውት፣ “እዚኽ አንኖርም” በማለት አካባቢውን ለቅቀው ሒደዋል፡፡

7) ሐምሌ 16 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ የአቶ ጌታ እንዳለ ቆርቆሮ ቤት ከነጎተራው(3 ቤቶች) እና የሌሎች 4 ገበሬዎችን ቤቶች አቃጥለውባቸው ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው ተሰደዋል፡፡

8/ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ ቡርቃ ጉዲና ቀበሌ፣ በጌ የተባለች ሥፍራ ላይ፣ በ81 ቆርቆሮ የተሠራ የአቶ ጌታ እንዳለ ቤት ተቃጠለ፤ በቃጠሎውም አንድ ጎተራ በርበሬ ወደመ፤ እርሱም ከነሙሉ ቤተሰቡ ተሰደደ፡፡

9) ጉርሙ መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ አገልጋይ የነበረ፣ ስሙ ማርሸት የሚባል፣ በሚሠራበት ሊሙ ኮሳ ገባ ብሎ በሚገኘው እርሻ ልማት አካባቢ በሽጉጥ ተመትቶ ጅማ ሆስፒታል በሕክምና ላይ ይገኛል፡፡

10) ጥቅምት 2011 ዓ.ም.፣ አቶ ጥላሁን በዜ የሚባል በወርኃ ጽጌ በቤተ ክርስቲያን ሲዘክር ቆይቶ ወደ ቤቱ ሲመለስ ተደብድቦ ላይሞት ተርፏል፤ ለወረዳው የመንግሥት ሓላፊዎች አመልክቶ ምላሽ ሲያጣ ለሕይወቱ ሰግቶ አካባቢውን ለቅቆ ሒዷል፡፡

11) ኅዳር 8 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ ወንድሙን አሳድደነው፤ እርሱ ቀርቷል ብለው የአቶ ጥላሁን በዜ ወንድም የኾነውን አቶ ዘሪሁን በዜንም፣ በገጀራ አንገቱን ሊቆርጡ ሲሰነዝሩ በእጁ ሲመክት፣ የእጅ ጣቶቹ ተቆርጠው ስለ ተጎዳ እርሱም አካባቢውን ጥሎ ወጥቷል፡፡

12) በኅዳር ወር 2011 ዓ.ም.፣ የአቶ አሳዬ ዋሌ እና የታናሽ ወንድሙ ሦስት ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ጥለውም ወጥተዋል፡፡

13) በዚሁ ኅዳር ወር 2011 ዓ.ም. ውስጥ፣ የአቶ ሲሳይ ዓለሙ ልጅ ዋለልኝ ሲሳይን፣ ሜዳ ላይ ብቻውን አግኝተው ሊገድሉት ሲሉ፣ “አትግደሉኝ ተዉኝ፤ እቤት ያለውን መሣሪያ አውጥቼ እሰጣችኋለኹ፤” በማለት ሲማፀን ትተውት እቤት ድረስ ተከታትለው በመሔድ መሣሪያውን አውጥቶ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁት፣ “ጫካ ውስጥ እንዳትገድሉኝ ፈርቼ እንጂ መሣሪያ የለንም” በማለቱ እስከነአባቱ ከፍተኛ ድብደባ አድርሰውበታል፤ የቤታቸውንም በርና መስኮት ገነጣጥለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከአካባቢው ወጥተው ተሰደዋል፡፡

14) የአቶ ተሸመ እንየውም ቤት ተቃጠለ፤ ከነቤተሰቡ ጥሎ ጠፍቷል፡፡

15) ታኅሣሥ 5 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ ወ/ሮ ጥሩ ካሴ የምትባለውንና አቶ አስቻለው የሥጋት የተባሉትን ክርስቲያኖች፣ ቤቶቻቸውን ደብድበው ንብረቶቻቸውን በመሰባበር አሳደዋቸዋል፤ ልጆቻቸውም ጠፍተዋል፡፡

16) ታኅሣሥ 9 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ አዲሱ ይታየው የተባለው ክርስቲያን ወደ አጎራባቹ የኢሉ አባቦር ክልል፣ ለእርሻ ሒዶ ሲመለስ፣ አንገቱን በስለት ቆርጠው ገደሉት፤ አስከሬኑም ወደ አማራ ክልል ተወስዶ ተቀብሯል፡፡

17) ሚያዝያ 4 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ ለሚዘክረው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጽዋ ቀጤማ ሊያጭድ በሔደበት ሚጡ ወንዝ ዳር፣ አቶ ልየው ጌትነትን፣ አንገቱን ቀልተው በመጸዳጃ ቤት ጉድጓድ ውስጥ ጥለው በላዩ ላይ የከብት ፍግ ጨምረውበታል፡፡ የመጸዳጃ ጉድጓዱ የአቶ መሐመድ ሃምዛ ሲኾን፣ ቤተሰቡና በእርሻው ሥራ ላይ ያሉ የሚጠቀሙበት ነው፡፡ ወዳጅ ዘመዶቹም፣ ቀጤማ ሊቆርጥ ወጥቶ የጠፋውን አቶ ልየው ጌትነትን ፍለጋ ቢወጡም ሊያገኙት አልቻሉም፤ያገኙትን የደም ነጠብጣብ ተከትለው ሲፈልጉ ግን ለማመን የሚከብድና ለሰው ቀርቶ ለአስከሬን እንኳን የሚሰጠውን ኢትዮጵያዊ ክብር በሚንድ መልኩ ከአጨደው ቀጤማ ጋራ በመጸዳጃ ቤት ጉድጓድ ውስጥ ቀብረውት ተገኝቷል።

18) ሚያዝያ 5፣ 2011 ዓ.ም.፣ በጋሌ ሠርጤ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚኖር አንድ ወጣት፣ ከሌሊቱ 6፡00 ላይ ከቤቱ ጠርተው በማስወጣት በአሠቃቂ ኹኔታ በጥይት ገድለውታል፡፡

19) በአዲስ ልማት ቀበሌም እንዲሁ፣ የክርስቲያኖች ቤቶች ተደብድበዋል፤ ክርስቲያኖቹም ተሰደዋል፡፡

20) በቡርቃ ጉዲና እና በአዲስ ልማት ቀበሌዎች፣ ከ200 በላይ አባወራ ይኖር ነበር፡፡ ኾኖም መጋቢት ወር 2011 ዓ.ም. በተደረገ የክርስቲያኖች ቆጠራ፣ 185 አባወራ ይኖር የነበረ ሲኾን፣ የክርስቲያኖች ግድያና ስደት ስለተባባሰና ሃይ ባይ ስለሌለ፣ ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ላይ 15 አባወራዎች ብቻ በጋሌ ሠርጤ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከቤተ ክርስቲያኗ ቄሰ ገበዝ (አስተዳዳሪ) ጋራ በድንኳን ተጠልለው ቀርተው ነበር፡፡

21) በመጨረሻም ሚያዝያ 24 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ የጋሌ ሠርጤ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ቄሰ ገበዝ የኾኑት ቄስ ቢተው ገረመው፣ ለብዙ ዓመታት ሲታገሉ ቢቆዩም ሰሚ አካል ስላጡ፣ የቤተ ክርስቲያኗን ቁልፍ ለጅማ ሀገረ ስብከት በማስረከብ ጥለው ወጡ፡፡

22) ቄስ ቢተው ገረመው፣ እንደ ሌሎቹ ክርስቲያኖች፣ ቤታቸው ሌሊት ሌሊት ሲደበደብ ስለሚያድር፣ ዐይነ ስውር ባለቤታቸውንና 6 ልጆቻቸውን(ሕፃናትን ጨምሮ)፣ ከአንድ ዓመት በፊት፣ ታኅሣሥ ወር 2010 ዓ.ም. ውስጥ ወደ ትውልድ ቀዬአቸው መልሰው ልከው እርሳቸው ግን፣ የእግዚአብሔር ማደሪያ የኾነችውን ታቦተ ኪዳነ ምሕረት ጥሎ ላለመውጣት በጸሎትና በልቅሶ ተግተው ከአንድ ዓመት በላይ ከቅጽር ግቢዋ ሳይወጡ ቆይተዋል።

23) 13 ካህናት(1 መሪጌታ፣ 8 ካህናት እና 4 ዲያቆናት) በመከራው ብዛት በመጋቢት ወር 2010 ዓ.ም. ውስጥ ጥለው ሲሰደዱ፣ የቤተሰባቸውም ውትወታ አላስቀምጥ ቢላቸው፣ ምእመናን ሳይኖሩም ታቦትና ካህን ህልውና የላቸውምና፣ ሚያዝያ 24 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ የቤተ ክርስቲያኗን ቁልፍ ለሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳሰ ሊያስረክቡ ከከተቱበት ደብር ወጥተው ወደ ጅማ ሔደዋል።

24) ሚያዝያ 5 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ በዚሁ ቤተ ክርስቲያን፣ በሰበካ ጉባኤ ሊቀ መንበርነት እያገለገለ የነበረን ቅንና ታታሪ፣ የቤተ ክርስቲያኒቷ የቁርጥ ቀን ልጅ የኾነን አንድ ወጣት፣ ተኩሰው ደረቱ ላይ መትተው ክፉኝ ተገድቶ ነበር፤ ለሕክምና ርዳታ ወደ ጅማ ሆስፒታል ቢሔድም፣ ነፍሱ ከሥጋው ተለይታለች፡፡

25) በደዴሳ ወረዳ፣ ግንቦት ወር 2010 ዓ.ም ውስጥ፣ 3 ክርስቲያኖች ዴዴሳ ወንዙ ዳር፣ በመሮ ጢሳ ቀበሌ መሻገሪያ በኩል(አትናጎ ወረዳ ክልል ውስጥ) የተገደሉ ሲኾን፣ ሊሙ ገነት ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ተቀብረዋል፡፡ አንደኛው ሩጦ አምልጧል፤ ቤተሰቦቻቸውና ልጆቻቸውም ተሰደዋል፡፡

26) በሊሙ ወረዳ ጥቅምት ወር 2011 ዓ.ም ላይ፣ 101 አባወራ የነበረ ሲኾን፣ መጋቢት ወር መጨረሻ ላይ 65 አባወራ ቀርቷል፡፡

27) በወረዳው፣ መሮ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ፣ በግምት 200 ሺሕ ብር የሚያወጣ ባሕር ዛፍ፣ በቄሮ ስም የሙስሊሙ ወጣቶች ተከፋፍለውታል፤ 10ሺሕ ብር የሚያወጣ መጠን ያለው ብቻ ቀርቷል፡፡ ዛፎቹን ወገብ ወገቡ ላይ በመቁረጥም፣ መልሰው እንዳያቆጠቁጥ በማድረግ ተስፋ የማስቆረጥ ተግባር ፈጽመዋል፡፡

ጩንጌ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ ከ100 በላይ አባወራ የነበሩ ሲኾን፣ ብዙዎቹ ተሰደዋል፡፡

28/ አምቡዬ የምትባል ከተማ ላይ (ከሊሙ 17ኪ.ሜ ወደ ጅማ)፣ “ኦሮሞ ብሎ ኦርቶዶክስ የለም” ብለው ጫና በማሳደር፣ አንድ አባወራ፣ ባለፈው የ2011 ዓ.ም. ዐቢይ ጾም በማስገደድ እንዲሰልም ተደርጓል፤ ባለቤቱ ግን፣ “ጾም እስኪፈታ ድረስ ልቆይ” ብላ ምክንያት በመስጠት ቆይታለች።

29) ሚያዚያ 8/2011 ዓ.ም.፣ በገቺ ወረዳ ሴከቻ ገበሬ ማኅበር የሚገኘው ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተቃጠለ፡፡ በጣም የሚያሳዝነው፣ የቤተ ክርስቲያኑን መቃጠል ሰምተው ከሔዱ የጸጥታ አካላት መካከል፣ ኢንስፔክተር ግርማ የተባለው ሰው፣ በቤተ ክርስቲያኑ መቃጠል በማዘን ሰው እንዳቃጠለው ሲናገሩ ከነበሩት ውስጥ አንዱን ሰው መትቶ ጉዳት አድርሶበት ተጎጂው ሆስፒታል ገብቷል፡፡ የኢንስፔክተሩ ድርጊት ትክክል እንዳልኾነ ተጠቅሶ ለሕግ የቀረበውን የክሥ አቤቱታ አንቀበልም ብለው ጥለውታል፤ ከሳሾቹ እሰከ አሁን ድረስ ችግር ላይ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

መጽሃፍ በነጻ:- ግዮናዊነት – የአማራ መነሻና መድረሻ (በምስጋናው አንዱዓለም መልከ ሐራ) በ2010 የተጻፈ

ግዮናዊነት – የአማራ መነሻ እና መዳረሻ

ምስጋናው አንዱዓለም (መለክ ሐራ)

ጥር 2010 ዓ.ም
ሶስተኛ እትም (የታረመ)
—————
ከ416 ገጾች በላይ የያዘውንና ከዚህ በታች ያለውን መጽሃፍ ወንድማችን ምስጋናው አንዱዓለም (መልከ ሐራ) ለህዝብ በነጻ አበርክቷ፡፡
—————
መሪ አንቀጽ

ስለ ህዝብ ለመጻፍ መነሳት ከባድ ውሳኔን ይጠይቃል፡፡ በተለይ ስለ ባለ ታላቅ ታሪክ ህዝብ፤ ታሪካዊ ፈተና ውስጥ ስለ ገባ ህዝብ ለመጻፍ እና በታሪካዊው እና በአሁኑ ሁኔታ ላይ ተመስርቶ የመወጣጫ ሀሳብ ለመንደፍ ብዕርና ወረቀት ለማዋሀድ መወሰን ቀላል አይደለም፡፡ ከዚህ በፊት ይሄ ነው የተባለ ለመነሻ የሚሆን ስራ አለመኖሩ ደግሞ ችግሩን የበለጠ ያከብደዋል፡፡ ጠቅለል ባለ ሁኔታ አማራን የተመለከቱ ዋና ዋና ጉዳዮችን መዳሰስ ግዴታ ሲሆን ደግሞ የበለጠ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ብዙ መሆናቸው ስለብዙ ጉዳይ መመራመርን ይጠይቃልና፡፡ ግን ምርጫ አልነበረም፡፡ ምርጫ ከሌለ ደግሞ ለወደፊቱ ምርጫ ለመስራት መወሰን ግዴታ ይሆናል፡፡ግዮናዊነት፡ የአማራ መነሻ እና መዳረሻ የተወለደበት አኳኋን ይሄው ነው፡፡

እናም ግዮናዊነትን በዚህ ጊዜ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ምክንያት ከሶስት ዓመት በፊት፤ ማለትም በጥር 2007 ዓ.ም የአማራን እንቅስቃሴ በአዲስ አስተሳሰብና በአዲስ መንፈስ አነቃቅተን የአማራ ህዝብ ደመኛ ጠላት የሆነውን የህወሀት (ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ወይም በአማርኛ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ድርጅት) አገዛዝ በታሪኩ አይቶት የማያውቀው ፈተና እንዲገጥመው ካደረግን በኋላ አራት አዳዲስ ክስተቶች በመከሰታቸው እና እነሱም ለአማራነት እንቅስቃሴው ፈተና መሆናቸውን፤ ፈተናነታቸውን መግፈፍም ለቀጣዩ የአማራ ህዝብ ትግል መንገድ ጠራጊ መሆኑን ስለተገነዘብኩ ነው፡፡ …… (ሙሉ መጽሃፉን ከዚህ ላይ አውርደው ያንብቡ)

አንዳንድ ነገሮች! (ባየ ተሻገር)

መግቢያ፤

የቤተ-አማራዊው ትወልድ ወይንም እንደ አዲስ የተጀመረው የአማራ ብሔርተኝነት እንቅስቃሴ አጀማመር እውነትን እውነት፣ ሐሰት ሐሰት ብሎ በድፍረት እና በመረጃ በመሞገት ነው። የትኛውንም ግለሰብ ወይንም ድርጅት ስህተት ሆኖ እስከተገኘ ድረስ ለስም እና ዝና ሳይጨነቁ እውነቱን በማፍረጥ ለወገን ትክክሉን መረጃ ማድረስ ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለበት ትግል ነው። በዚህ የትግል ሂደት ውስጥ በጣም ጥቂቶች ዝናን ሲያተርፉበት በርካቶች ግን ከቀደመ ግለሰባዊ ማንነታቸው ጋር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተለያይተው ስለሕዝባቸው እንደ ሰም እየቀለጡ ይገኛሉ። እድል ለበለጠ መስዋዕትነት የጠራቻቸው ደግሞ አሁንም በይፋ ወያኔን ፊት ለፊት ገጥመው በማንቀጥቀጥ ላይ ናቸው! ይሁን እንጅ በትግላችን እንቅስቃሴ አጀማመር ላይ የነበረው ትጋትና ቁርጠኝነት አሁን አሁን እየላላ የመጣ ወይንም መልኩን የቀየረ ይመስላል።

የቤተ-አማራ ዝናና እና ስም እንደቀደመው እንደተጠበቀ ቢሆንም ድጋፍና ክትትል የሚያደርግላት ቁጥሩ እምብዛም ነው። እንዲያውም ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ እንደሚባለው ዓይነት ነው። በማንነታችን ምክኒያት ጥቃት ሲደርስብን እና ራሳችን መከላከል ሲያቅተን ሁላችንም ቤተ-አማራ ነን እንላለን፤ ነገሮች የተስተካከሉ ሲመስለን ደግሞ የቤተ አማራን ርዕይ《 አገር ማፍረስ》አድርገው የሚያዩትን ፀረ-አማሮች መነፅር እናጠልቅና እንሸሻታለን። በዚህ ዥዋዥዌ መሃል የቀደመ መነሻችን እየሳትን እውነትን እውነት ሐሰትን ሐሰት የማለት አቅማችን እየተዳከመ መጥቷል። በዚህም ምክኒያት የብሔርተኝነታችን ዋና ምሰሶዎች እነ ወልቃይት፣ መተከል፣ ራያ፣ ሸዋ ወዘተ እየተረሱ በየቀኑ በሚወረወርልን አጀንዳ ተወጥረን እንውላለን። ለዚህ ማርከሻው እውነት የሚመስሉ ሐሰቶችን እያጋለጡ ጠላትን እረፍት መንሳት ነው፤ ጠላት እረፍት ሲያጣ እኛ ውላችንን እናጠብቃለን። እነሆ ለዛሬ ሶስት እውነት የሚመስሉ ነገር የሐሰት ትርክቶችን በመረጃ በመታገዝ እናጋልጣለን።

ሀ) ሸዋ!

የሸዋ ጠቅላይ ግዛት የአማራ ሕዝብ የስልጣኔ መገለጫ ነበር። ከአሥራ ሁለተኛው ክፍለ-ዘመን አንሥቶ እስከ አስራ ስድስተኛ ክፍለ-ዘመን ኢትዮጵያ እንደ ኮከብ የምታበራ የዳበረች፣ የታፈች፣ ሕዝቧ ደስተኛ፣ ስልጣኔዋም ቀኝ ነበረ። በዚህ ጊዜ ተጓለት ድንቅ ከተማ ነበረች። ድንቅ ከተማ ብቻ ሳትሆን ወደ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ቤተ-አማራ እና ቀሪው ሸዋ ንግድ የሚጧጧፍባት መስመርም ነበረች። በረራና አካባቢዋ የነበረውን ሥልጣኔ ጨምሮ በፋራ ማውሮ ካርታ ላይ ምርምር የሚያደርገው ሳሙኤል ዋልከር ኢትዮጵያን ኢንሳይት ላይ ደህና አድርጎ ጽፎታል ( https://t.co/yGSCPQlxAc?amp=1)። አርኪዮሎጅስቱ ከተጉለትና በረራ በተጨማሪ ስለየረር፣ ዝቋላ እና መሰል ቦታዎች መጠነኛ አስተያየት ሰጥቷል። ማስፈንጠሪያውን በመከተል የበለጠውን ማንበብ ይቻላል።

ከሰላሳ ዓመት ወዲህ ደግሞ ሸዋ እንደ መስኖ መሬት ተሸንሽኖ የማንም መጫዎቻ ሆኗል! ሸዋ አሁን ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ምስራቅ፣ ደቡብ ምዕራብ እና አዲስ አበባ ተብሎ ተከፋፍሎ የአንበሳው ድርሻ ኦሮሚያ ወደሚባል የግዞት “ክልል” ተካሏል። አዲስ አበባም የፅንፈኞች የፖለቲካ ትኩሳት ማወራረጃ ሆናለች።

ለአምሥት የተከፈለውን ሸዋ እንደ ጥንቱ አንድ ላይ አድርገን ብናስበው እና የራሱን የወያኔን መረጃ ወስደን እንኳን እንሞግት ብንል በሁሉም የማንነት መለኪያ መስፈርቶች ሸዋ አሁንም የቀድሞውን የሸዋ ጠቅላይ ግዛትነቱን ባረጋገጠ መልኩ አማራ ሆኖ እናገኘዋለን። በ1999 ዓ.ም በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጅንሲ በተደረገው የሕዝብና ቤት ቆጠራ የተገኘው መረጃ የሚከተለው ነው።

አማራ (በሚሊዮን)
         ሰ/ሸዋ      1.84
        ም/ሸዋ      0.21
      ምዕ/ሸዋ      0.31
     ደ/ምዕ/ሸዋ   0.07
            አ/አ        1.81

            ድምር   4.24

ኦሮሞ (በሚሊዮን)

     ሰ/ሸዋ      1.21
     ም/ሸዋ     1.00
     ምዕ/ሸዋ  0.96
     አ/አ          0.54

      ድምር      3.70          ሆኖ እናገኘዋለን።

በዚህ መሠረት በሕዝብ ቁጥር የበላይነት ያለው አማራው ነው ማለት ነው። ከሕዝብ ቁጥር በተጨማሪ በቋንቋ እንውሰደው የተባለ እንደሆነ መላው ሸዋ አማርኛ ይናገራል፤ እንደ ናዝሬት፣ ደብረ-ዘይት፣ ሞጆ፣ ቡራዩ፣ መተሃራ ወዘተ ባሉት ከተሞች ደግሞ አማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋው የሆነው ሕዝብ የቁጥር የበላይነት አለው ። ባህሉም የአማራ ነው፤ አሁን ሰሞኑን መስቀል አደባባይ በኦሮሞ ስም ተሰልፎ የመጣው ፈረሰኛ ባህሉ አማራዊ መሆኑ ምንም ሊያጠያይቅ አይችልም።  ሥነ-ልቦናው አማራ ነው። መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጡም ከጎዣም እና ከቤተ-አማራ ጋር ተያያዥ ነው።

በዚህ ሁሉ እውነታ መሃል ነው እንግዲህ ነባሩ የአማራ ማዕከል ለኦሮሞ ተላልፎ ተሰጥቶ “በአዲስ አበባ ኦሮሞ ልዩ ጥቅም ይገባዋል” ብለው የሚከራከሩ  አማራዎች ነን የሚሉ ባለድርጅቶች ያሉን። ልብ ቢኖር እውነትን ይዞ ለሕዝብ ጥቅም መታገልን ዓላማ ቢያደርጉት በራሱ ጥይት መላው ሸዋን ወደ ጥንት ማንነቱ ለመመለስ ትክክለኛው የመታገያው ጊዜ አሁን ነበር። ነገር ግን ይህንን እውነተኛ መረጃ በሐሰተኛ ትርክት ሸፍነው በእርስታችን ላይ ዕጣ ተጣጥለውበታል።

ለ) የሌሎችን ማንነት ደፍጥጦ ተንሰራፍቶ ስላለው የኦሮሞ “ክልል”

አንድ የሚገርመኝ ሃቅ አለ! አማራ “ክልል” ተብሎ በሚጠራው ውስጥ ማንነታቸው አማራ የሆኑ ነገር ግን ከአማርኛ በተጨማሪ የራሳቸው አካባቢያዊ ቋንቋ ያላቸው ንዑስ-ብሔሮች ይገኛሉ። እነዚህ ብሔሮች ወይንም ንዑስ ብሔሮች ግን በሕዝብ ቁጥርም በብዛትም ጥቂቶች ናቸው፤ መብታቸውም በሚገባ ተከብሮላቸዋል። ነገር ግን የኦሮሞና የትግሬ ጽንፈኛ ብሔርተኞች ከልክ በላይ ፕሮፓጋንዳውን ስለስጮኹትና የዲስኩሩን የበላይነት ስለወሰዱ ከአማራ “ክልል” ውጭ ባለው ክልል ውስጥ የክልሉ ስም መጠሪያ ከሆነው ብሔር ውጭ ሌላ ምንም ዓይነት ብሔር የማይኖር አስመስለውታል። እውነታው ግን ቁጥራቸው አማራ “ክልል” ውስጥ ካለው የሚበልጥ የሕዝብ ብዛታቸውም አማራ “ክልል” ውስጥ ካሉት የሚበልጡ ብሔሮች  ከአማራ “ክልል” ውጭ ባሉት “ክልሎች” ይገኛሉ። በተለይ የኦሮሞ “ክልል” በርካታ ቁጥር እና የሕዝብ ብዛት ያላቸው ብሔሮች የሚገኙበት “ክልል” ነው። ይሁን እንጅ የኦሮሞ “ክልል” ደፍታጭና ጨቋኝ በመሆኑ አፍኖ እንዳይጩሁ አድርጓዘዋል፤ በተለይ የአማራው ብሔር ፖለቲከኞች ደግሞ ጽምፅ ሊሆኗቸው አልቻሉም!

የቅማንት እና የአገው አማራን ስም እያነሱ ሁናቴውን ስላጦዙት ብዙው አማራ አማራ የምንለው ሕዝብ የብዙ ማንነቶች ውጤት እንጅ አንድ ሕዝብ አይደለም የሚለውን የሐሰት ትርክት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሸምቶታል። በዚህ በኩል የሚከፈትብንን ፕሮፓጋንዳ ለመመከት የምንሞክረውም ብዙውን ጊዜ አማራ ባህሉ አቃፊ ነው በሚል ነው። ወያኔው ብአዴን ደግሞ መከራከሪያው አማራ “ክልል” ያሉ “ሕዝቦች” ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ ነው፤ በ”ክልልላችን” የሰፈነው ዴሞክራሲ በሌላው የለም  የሚል ነው። በቃ ይኼው ነው! ከዚህ ውጭ የራሳቸውን መረጃ እንኳን ተመልክቶ አፀፋዊ ምላሽ ለመስጠት የሞከረ ፖለቲከኛ የለም። እውነታው ግን የሚከተለው ነው። (በራሳቸው ጥይት ለመምታት ያክል የ1999 ዓ.ምቱን የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ እንደማመሳከሪያ እንውሰደውና ሃቁን እንመልከት።)

በአማራ “ክልል” ውስጥ 88 በላይ ብሔሮች ሲኖሩ በኦሮሞ “ክልል” ደግሞ 94 በላይ ብሔሮች ይገኛሉ። በግርድፉ ሲታይ እንዲያውም ኦሮሞ የሚባለው “ክልል” ከአማራ “ክልል” በ6 ብሔሮች ብዛት ይበልጣል ማለት ነው። ትክክለኛው አነጋገር ደግሞ ሁለቱም “ክልሎች” የብሔር ስብጥራቸው ተመሳሳይ ነው ማለት ነው። ዋናው ነጥብ ግን ይኼ አይደለም!

በሕዝብ ቁጥራቸው ጎላ ያሉ እንዲሁም የራሳቸው ማንነት ያላቸውን ሌሎች ብሔሮች ቁጥር መመልከቱ ወሳኝ ነገር ነው። ከአምስት ሽህ ሕዝብ በላይ ያላቸው በአማራ “ክልል” ውስጥ የሚገኙ ብሔሮች ብዛት ዘጠኝ ሲሆን እነርሱም

አገው-አዊ            575, 878
ኦሮሞ                 451, 362
አገው-ሃይምራ       238, 653
አርጎባ                    70, 012
ትግሬ                     37, 397
ጉሙዝ                   13, 105
አኝዋክ                    6, 265
ሶማሊ                     5, 724    እና
በርታ                      5, 213   ናቸው።

ከእነዚህ መካከል አገው-አዊ፣ ኦሮሞ እና አርጎባ ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ ብሔሮች ናቸው። አገው-አዊ እና አርጎባ ደግሞ ከተቀረው የአማራ ሕዝብ የሚለያቸው ከጋራ ቋንቋቸው አማርኛ በተጨማሪ  የራሳቸው ቋንቋ ያላቸው መሆኑ ነው። ሌሎቹ  የማንነታቸው መሠረቶች ተመሳሳይ ናቸው! አብሮነታቸውም ሺህ ዘመናትን የዘለቀ ነው።

በአንፃሩ ኦሮሞ በሚባለው “ክልል” ውስጥ ቁጥራቸው ከአምስት ሺህ በላይ የሆነ ሃያ ሶስት (23) ብሔሮች ይገኛሉ (ንፅፅሩ 9 ለ 23 መሆኑን ልብ ይሏል!)። እነርሱም

አማራ*             1, 943, 578
ጉራጌ                   248, 100
ጌዴዎ                   242, 529
ሶማሊ                     89, 533
የም                         84, 086
ወላይታ                    63, 021
ትግሬ                       61, 263
ሃድያ                         52,673
ሲዳማ                      52, 553
ስልጤ                      49, 268
ዳውሮ                       44, 601
ከንባታ.                      41, 618
ከፊቾ.                        35, 703
አርጎባ.                       31, 329
ኮንሶ.                          31, 111
ማኦ.                           24, 202
አላባ.                          18, 897     
ጋሞ.                            13, 339
አኙዋክ.                        12, 683
ብራይሌ                        11, 811
ቀቤና                               7,766
ንታንጋቶም                        6, 933    እና
አይዳ                                6, 216 ናቸው።

ኦሮሞ በሚባለው “ክልል” ያሉ ብሔሮች በቋንቋም ሆነ በማንነት ከኦሮሞ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የላቸውም። ሁሉም ቀደምት ሕዝብ ሲሆኑ በመጤው ኦሮሞ ማንነታችው ተጨፍልቆ፣ ርስታቸው ተነጥቆ፣ አዲስ ገዥ ተሾሙላቸው ይኖራሉ። በቋንቋቸው የመማር፣ የመዳኘት ወዘት መብት የላቸውም። ብአዴን ወያኔዎችም ሆነ ሌሎች ተቃዋሚ የሆኑ ድርጅቶች አንድም ቀን ስለዚህ ሁናቴ አውርተው አያውቁም!

ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኞች ወንዝ ተሻግረው በአማራው ዓይን ውስጥ ያለችውን ጉድፍ አይተው ቅማንት፣ አገው ወዘተ እያሉ በውስጥ ጉዳያችን እንዲገቡ እድል የፈጠረላቸው በእነሱ ዓይን ውስጥ ያለውን ምሶሶ የሚጠቁማቸው ስለጠፋ ነው።

የኦሮሞ “ክልል” የብሔሮችን መብት የማያከብር፣ አፋኝ፣ ደፍጣጭ እና ኢ-ዴሞክራሲያዊ “ክልል” ነው። ለምሳሌ ያክል በጉጁ ዞን ውስጥ ከስማንያ በመቶ የሚበልጠውን የሕዝብ ቁጥር የሚይዙት ጌዴዮዎች ናቸው። ነገር ግን ከሃያ በመቶ በታች የሆነው ኦሮሞ ተሰሚነት ባለቤት ሆኖ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ጌዴዎዎችን አፈናቅሎ ለርሃብ አደጋ ማጋለጡ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። ቢያንስ ከአሁን በኋላ የአማራ ፖለቲከኞች ይህንን ደፍረው ሊናገሩት ይገባል። የአማራው ብሔርተኛም ቢሆን እየነቀሰ እያወጣ ሊጠቀምበት ይገባል። የአማራ ሚዲያዎች ይህንን ጉዳይ ሽፋን ሰጥተው ሊዘግቡት ይገባል።

ሐ) የአማራ ሕዝብ ተበትኗል የሚለው ማስፈራሪያ!
(በክፍል 2 እመለስበታለሁ)

ይቀጥላል

———————————-
(*ኦሮሞ በሚባለው “ክልል” የሚኖረውን አማራ በተመለከተ ለብቻው ለማየት እሞክራለሁ)

የህገ መንግስት ይሻሻል ጥያቄን በአግባቡ መመለስ ህገ-መንግስቱ ህይወት ኖሮት ለረጅም ጊዜ እንዲኖር ያደርገዋል!! (lesane damote)

ህገ-መንግስት ማሻሻል ማለት በአጭር አነጋገር ለህገ-መንግስት ማስተካከያ የሚደረግበት ሂደት ማለት ሲሆን የህገ-መንግስት ማሻሻል ሂደት ክለሳ(Revision) እንጂ ሙሉ በሙሉ የማስወገድና የመቀየር አብዮት(revolution) ማለት አይደለም፡፡ ይልቁንም መሻሻል ማለት የለውጥ ሂደት (process) ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህ ሂደት በአንድ ህገ-መንግስት ሰነድ ውስጥ የለውጥ እርምጃ ወይንም እድገት የሚታይበት ሂደት መሆኑን መገንዘብ ብልህነት ነው።
አብዛኛው ጊዜ ማሻሻያ የህገ-መንግስቱን ቃላት፣ ሐረግ፣ ዓ/ነገር ወይንም አንቀጾችን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡ በነዚህ በሚሻሻሉት ምትክ በከፊል መጨመር፤ በከፊል መቀነስ ወይንም ሙሉ በሙሉ መለወጥ ሊሆን ይችላል፡፡ እኛም እንደ አማራ ህዝብ ህገ መንግስቱ በፀደቀበት ወቅት በተለያዪ አካላት እንደተነገረው ተወካይ ስላልነበረን አዋራጅ፣አሳቃቂ እና የበዳይነት ስሜትን ያዘሉ ቃላትን የያዘ፤ እንዲሁም ከህወሓት የፖለቲካ ፕሮግራም የተቀዳ በመሆኑ የአማራን ህዝብ ጨቋኝ ብሎ በመፈረጅ በብሔር ብሔረሰቦች ዘንድ በቅራኔ እንዲታይ በተንኮለኞች ሴራ ተሰርቶበታል። ይህንን ለማረጋገጥ የህገመንግስቱን መግቢያ መመልከት በቂ ነው። ስለዚህ ህገመንግስቱ ሲሻሻል ከህገ-መንግስቱ አጠቃላይ ዓላማ፣ ግብና መንፈስ ጋር በሚጣጣም መልኩ መሆን ይኖርበታል ብየ አምናለሁ፡፡ የማሻሻሉ ሂደት ህገ-መንግስቱን የማይቀበል የህብረተሰብ ክፍል እስካለ ድርስ እንዲሻሻል መስራቱ ህገ መንግስቱ ህይወት ኖሮት ለረጅም ጊዜ እንዲኖር ያደርገዋል፡፡ ምክንያቱም ጊዜ በሄደና ነገሮች በተቀየሩ ቁጥር የእድገት ደረጃም አብሮ ይቀየራል፡፡ ቅሬታዎችንም በዛው ልክ እየፈቱ መሄድ ስለሚቻል። ስለሆነም ህግም ሆነ ህገ-መንግስት አብረው ከህብረተሰብ እድገት ጋር ማደግ ካልቻሉ ፍላጎቶችና ጥያቄዎች እየጎመሩ ለስርዓት አልበኝነት ምክንያት መሆናቸው አይቀሬ ነው፡፡ በመሆኑም ህገ-መንግስት ዘላቂነት ኖሮት ገዢ ሆኖ ለመኖር መሻሻል ወይንም መለወጥ የሚያጠያይቅ አይሆንም፡፡ ህገ­መንግስት የማሻሻል ሂደት ህገ-መንግስት ሲሰራ እራሱን የቻለ ሂደት እንዳለው ሁሉ በማሻሻሉም ወቅት መከተል
የሚገባቸው ሂደቶች እንዳሉትም እገነዘባለሁ፡፡ በኢፌዲሪ ህገመንግስት አንቀፅ 104 እና 105 ላይም የተቀመጡት ድንጋጌዎች ይህንኑ ሂደት በግልፅ የሚያሳዪ ሲሆን ጥብቅ(Strict) መሆናቸው ግን የማሻሻል ሂደቱን የተንዛዛና በቀላሉ የማይሳካ መሆኑን ያመለክታል። በነዚህ አንቀፆች መሰረት ህገመንግስ ለማሻሻል የምንከተላቸውን ሂደቶች ይነግሩናል።
እነሱም ፡-

 1. የማሻሻያ ኃሳብ ማመንጨት/Initiation/
 2. መወያያት /Deliberation/
 3. መቀበል/Adoption/
 4. ማፅደቅ /Ratification/ ናቸው፡፡
  እነዚህ ሂደቶች ከህገ-መንግስት አወጣጥ ሂደት ጋር ከሞላ ጐደል ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ማለትም መሠረታዊ ልዩነት የሚታየው በመጀመሪያ ሂደት ላይ ሲሆን በህገ-መንግስት አወጣጥ ሂደት የመጀመሪያ እና አዳዲስ ኃሳቦች የሚካተቱበት ሂደት በማርቀቅ/Drafting/
  ሂደት የሚከናወን ሲሆን በማሻሻል ወቅት ግን አስቀድሞ ያለ ህገ-መንግስት የሚሻሻል ስለሆነ በዚህ ደረጃ የመጀመሪያ ደረጃ የማሻሻያ ኃሳብ ማመንጨት ደረጃ (Intiation) ይሆናል፡፡
  በዋነኝነት የአንድን ህገ-መንግስት ዓይነት ለመለየት ከሚረዱት ዋነኛ ባህሪያት ውስጥ አንዱ የማሻሻያ ሂደቱ ወይንም ሥርዓቱ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- አንድ ህገ-መንግስት ጥብቅ ወይንም ልል ነው የሚባለው የማሻሻያ ሂደቱን በማየት የሚታወቅ ሲሆን ህገ-መንግቱ በቀላሉ የሚሻሻል ከሆነ ልል(felexible) ነው ማለት የሚቻል ይሆናል፤ በቀላሉ የማይሻሻል ከሆነ ደግሞ ጥብቅ(Strict) ህገ-መንግስት ይባላል፡፡

በአንቀፅ 104 ስር በግልፅ ሰፍሮ የሚገኘው ስለህገመንግስቱ መሻሻል ሀሳብ እንዲህ ይነበባል ፡፡ አንድ ህገመንግስት የማሻሻያ ኃሳብ በፌዴሬሽን ምክር ቤት እና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሶስተኛ ድምፅ ከተደገፈ ወይንም ከፌዴሬሽኑ አባል ክልሎች ውስጥ አንድ ሶስተኛ የክልል ምክር ቤቶች በድምፅ ብልጫ የማሻሻያውን ሀሳብ የደገፉት ከሆነ ለውይይትና ለውሳኔ ለሕዝቡና ጉዳዮች ለሚመለከታቸው ክፍሎች እንደሚቀርብ ይደነግጋል፡፡
ከሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ውጭ ሌሎች የህገ-መንግስቱ ድንጋጌዎች ሊሻሻሉ የሚችሉት የተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በጋራ ስብሰባ በሁለት ሶስተኛ ድምፅ የቀረበውን ማሻሻያ ሲያፀድቁት እና ከፌዴሬሽኑ አባል ክልሎች ምክር ቤቶች ውስጥ የሁለት ሶስተኛ ክልሎች ምክር ቤቶች በድምፅ ብልጫ ሲያፀድቁት ብቻ ነው፡፡ ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች እና የህገ-መንግስቱን ማሻሻያ የሚመለከቱ ድንጋጌዎች የሚሻሻሉት ሁሉም የክልል ምክር ቤቶች ማሻሻያው በድምፅ ብልጫ ሲያፀድቁት የፌዴራሉ መንግስት
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሁለት ሶስተኛ ድምፅ ማሻሻያውን ሲያፀድቀው አና የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በሁለት ሶስተኛ ድምፅ ማሻሻያውን ሲያፀድቁት ነው ይላል፡፡ስለሆነም የኢፌድሪ ህገ-መንግስት የማሻሻል ሂደት ጥብቅ(Strict) ያልኩት ለዚህ ነው። በተለይ ሰብዓዊ መብቶችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ማሻሻሉ ደግሞ ይበልጥ ጥብቅ(Strict) እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህ ማለት ግን ህገ-መንግስት አይሻሻልም ማለት እንዳልሆነ በግልፅ መታወቅ ይኖርበታል። ህገ-መንግስቱ በኢትዮጵያ የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች የቃል ኪዳን ሰነድ ከሆነ ጥያቄ እያቀረበ የሚገኘው 50 ሚሊዮንና በለይ አማራና ሌሎች ህዝቦች በቂና አሳማኝ የሆነ ምክንያት እስካላቸው ድርስ በቀላሉ የሚቀየርበትን ወይንም የሚሻሻልበት ሁኔታ ማመቻቸት የውዴታ ግዴታ ይሆናል ማለት ነው። ከዚህ በመነሳት የኢፌድሪ መንግስት ጥብቅ የሆነውን የህገ-መንግስት ማሻሻያ ስርዓት ሊያጤነውና ህዝቡን ሊያዳምጥ ይገባል።

ዐማራ፣ የዐማራ ብሔርተኝነት እና ዘረኝነት፡-

ነጮች ጊዜው የደረሰን አሳብ ማንም ሊያቆመው ወይም ሊያስቆመው አይችልም ይላሉ፡፡ ጊዜው የደረሰ አሳብ የሚባለው ቀደም ባሉት ዘመናት ወይም ዓመታት የሚያፈልቀው ጠፍቶ ወይም ደግሞ ቢፈልቅም ኅብረተሰቡ ሊቀበለው ሳይፈቅድ ቀርቶ ነገር ግን በሌላ ዘመን ብቅ ሲል ነባራዊና ኅሊናዊ ሁኔታዎች ለተፈጻሚነቱና ተግባራዊነቱ ተሟልተው የሚገኙበት አሳብ ማለት ነው፡፡ የዐማራ ብሔርተኝነትም ብቅ ያለው ይህን በመሰለ ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡ ዛሬ ጊዜው እንዲህ የደረሰውና ብሶትና መከፋት፣ መከራና ስቃይ፡ መገፋትና መገለለል፣ መሞትና መጥፋት የወለደው ለጋውና የዐማራው ብቸኛው የመዳኛ መንገድ የዐማራ ብሔርተኝነት ገና በጥዋቱ ፍሬ ማፍራት ጀምሯል፡፡
ይሁንና በዚህ ሁኔታ በተነቃቃው የዐማራ ብሔርተኝነት አማካይነት ዐማራው እንደሕዝብ መብቱን ሲጠይቅ ወይም ደግሞ በማንነቱ ልደራጅ ሲል ደግሞ ለማሽማቀቅ ዘረኝነት፣ ጎሠኝነትና የሌሎች ፍረጃዎች ሰለባ ሲሆን ይታያል፡፡ በተለይም ደግሞ ዐማራው ለአንድ ሕዝብ ቅንጦት ስለሆኑት ነጻነት፣ እኩልነት፣ ዴሞክራሲ፣ ሉዓላዊነትና ሕዝባዊ ጥቅሞች ደልቶት የሚጠይቀው ሳይሆን ቀደም ብሎ ባለመደራጀቱ በመፈጸመው ታሪካዊ ስህተት እና ታሪካዊ ጠላቶቹ ከግራና ከቀኝ፣ ከፊትና ከኋላ ተወግቶ ቅርቀር ውስጥ (DEADEND) የገባውን ህልውናውን ለመታደግ ብሎ ተፈጥሯዊ የሆነውን ራስን የመከላከል ወይም የአልሞትባይ ተጋዳይነት (SELF DEFENCE) የሞት ሺረት ትግል በሚያደርግበት ወቅት እንበለምክንያት ሁሉም ተነስቶ ዘረኛ፣ ጎሠኛና ሌላም አፋቸው አንዳመጣላቸው ይከሱታል፡፡ እንዲያውም አሁን አሁን በአገር መሪ ደረጃ ሳይቀር “ዘርኝነት ይብቃ” የሚሉ መፈክሮችን ደረታቸው ላይ ለጥፈው በአደባባይ መውጣት ጀምረዋል። ይህ ደግሞ ነገሮችን ወዳልተፈለገ መንገድ ይወስድ ይሆናል እንጅ አይጠቅም ፡፡ ለዚህም ደግሞ ብሔተኝትና ዘረኝነት ምን አገናኛቸው፣ የዐማራው ብሔርተኝነት ጉዳዩ ምንድነው የሚለውን መመልከት ተገቢ ይመስለናል፡፡

~ዘረኝነት ሰዎችን በቆዳ ቀለማቸው፣ በፊትና በአካል ቅርጻቸው፣ በዓይናቸው ቀለም፣ በጸጉራቸው (በዘራቸው ሥጋዊ መልካቸው) በተፈጥሯዊ ነገር ምክንያት ወይም የበላይ ማድረግ፣ ማግለል፣የዘር ማጽዳት መፈጸም፣ በዘራ ምልክት፣ከራስ ዘር ጋር እንዳይዳቀሉ ማድረግ መሥራት የመሳሰሉትን የሚያጠቃልል ነው፡፡

~ብሔርተኝነት በተቃራኒው የጋራ ታሪክን፣ ቋንቋን፣ የጋራ ማንነትን፣ ብሔረሰባዊነት ዋጋዎችንና ከማንነታዊ ጋር በተያያዘ የመጠን የጋራ ሥነ ልቦና ሥነ ምግባር፣ ባሕል ወዘተ የመሳሳሉትን ይዛ እነዚህ ላይ የራሱን ህልውና የመታደግ፣ የራሱን ጉዳይ በራሱ የማስተዳደርና አደረጃጀት የመመሥረት ራእይና ንቅናቄ ነው፡፡
ዘረኝትና ብሔርተኝት አይገናኙም፣ ከአፍሪካዊነት አንጻር ምሳሌ ኢትዮጵዊነት ብሔርተኝነት ነው፤ ዳሩ ግን ዘረኝነት አይደለም፡፡ ከኢትዮጵያዊነት አንጻር ሲታይ ዐማራነት፣ ኦሮሞነት ወዘተ ብሔርተኝነትና ብሔራዊ ማንነት ነው፣
በሌላ በኩል ብሔርተኝትና ዘረኝነት በንጽጽር ሲቀመጡ የሚከተለውን ልዩነት እናገኛለን፡-

 1. የመጀመሪያው ልዩነት ዘረኝነት መቆሚያው ደመነፍሳዊ ሲሆን፣ ብሔርተኝነት ግን በማኅበራዊ አብርኆት ላይ የቆመ ነው፡፡
 2. ዘረኝነት ዝግ ነው፤ብሔርተኝት ግን ለሁም ክፍት ነው፡፡
 3. ዘረኝነት ደምና አጥንት ላይ ሲቆም ብሔርተኝነት ግን ምክንያት ላይ የቆመ ነው፡፡
 4. ዘረኝነት ሰዎችን የመምረጥ ዕድል በማይሰጣቸው የትውልድ ዝርያቸው አማካይነት የሚያደራጅ ሲሆን፣ ብሔርተኝት ግን ሰዎች መርጧቸውና ሊሰሯቸው በሚችሏቸው ማኅበራዊ እውነታዎች አማካይነት የሚያደራጅ ነው፡፡
 5. ዘረኝነት ጥንታዊ በምንላቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አደረጃጀቶች ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ ብሔርተኝነት ግን ከዘመናዊነትና ከአብረሆት ጋር ከሚመጡ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ አደረጃጀቶችና ባሕላዊ እሴቶች ወይም ዋጋዎች ጋር የተሳሰረ ነው፡፡

እናም ዐማራነት (የዐማራ ብሔርተኝነት) ዐማራ እንደሕዝብ ቆሞ መራመድ የሚችልበት የተፈጥሮና የህልውና ምርኩዝ እንጅ ዘረኝነት ወይም ጎሠኝነት አይደለም፡፡ ይህም ማለት እንድ ሕዝብ እንደሕዝ ቆሞ እንዲራመድ ወይም ህልውናው እንዲረጋገጥ፣ ከዚህ በላይ ከደላው ደግሞ ለፍትሕ፣ እኩልነት፣ሉዓላዊነት፣ ሲባል እስከሕይዎት ሊደርስ የሚችል ትግል ማድረግ ነው፡፡

ስለሆነም አሁን ስለዐማራ ብሔርተኝነት የምንነጋገረው ከዚህ በላይ በተገለጸው አግባብ ለአንድ ሕዝብ ቅንጦት ስለሆኑት ነጻነት፣ እኩልነት፣ ዴሞክራሲ፣ ሉዓላዊነትና ሕዝባዊ ጥቅሞች ደልቶት የሚጠይቀው ሳይሆን ቀደም ብሎ ባለመደራጀቱ በመፈጸመው ታሪካዊ ስህተት እና ታሪካዊ ጠላቶቹ ከግራና ከቀኝ፣ ከፊትና ከኋላ ተወግቶ ቅርቃር ውስጥ (DEADEND) የገባውን ህልውናውን ለመታደግ ብሎ ተፈጥሯዊ የሆነውን ራስን የመከላከል ወይም የአልሞትባይ ተጋዳይነት (SELF DEFENCE) የሞት ሺረት ትግል ምክንያት ባለፉት አራትና አምስት ዓመታት መነቃቀት በጀመረው የዐማራ ብሔርተኝነት ጉዳይ ነው፡፡
የዐማራ ብሔርተኝነት ሲባል ኢትዮጵያዊነትን መካድ ማለት አይደለም፣ ይልቁንም ህልውናው አደጋ ላይ ከወደቀበት የጨለማ ዘመን ወጥቶ በመነቃቃት ላይ ነውና ይህን አጠናክሮ በመጓዝ የዐማራውን ህልውናና ሁለንተናዊ ጥቅም ለማረጋገጥ ተገቢውን ትኩረት መስጠት ማለት ነው፡፡ ህልውናውን በማረጋገጥ ለከፋ ውርደት የዳረገንን ድህነትና ኋላቀርነት ታግሎ በማሸነፍ ወደቀደመው ክብር ለመመለስ፣ በራሱ የሚተማመንና የበለጸገ ማኅበረሰብ ለመገንባት፣ ከሌሎች ወንድም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር እኩል በሰላማና በደስታ ለመኖር የሚያሰችል ሁሉን አቀፍ ትግል ይፈልጋል፡፡ ትግል ደግሞ ኅብረት፣ አንድነት፣ መግባበት፣ መተባባርና መተማመን ይፈልጋል፡፡ ይህ ሁሉ ደግሞ ያለተመሳሳይ ሥነ ልቦናዊ እንደነት ከየትም ሊመጣ አይችልም፡፡ የተመሳሳይ ሥነ-ልቦናዊ አንድነት ምንጭ ደግሞ ብሔርተኝነትና ብሔርተኝነት ብቻ ነው፡፡ ዛሬ በዓለም ላይ እጅግ ተሳክቶላቸው በሀብት ላይ ሀብት አካብተው፣ በሥልጣኔ መጥቀው፣ በዓለም አደባባይ ተሰሚነታቸው ጎልቶ የሚሰማው ሁሉም ድምፃቸው የሚቀዳው ከበለጸገው ብሔርተኝነታቻው ነው፡፡ ይህም ማለት በዓለም ዙሪያ ያሉ ሕዝቦች ሁሉ እንደሕዝብ የቆሙት የብሐርተኝነት ምርኩዛቸውን ተመርኩዘው ሲሆን፣ ብልጽግናቸው፣ አንድነታቸውም ሆነ ትብብራቸው የሚቀዳው ከዚሁ ከዳበረው የብሔርተኝነት ወቅያኖሶቻቸው ነው፡፡

ስለሆነም ቀደም ሲል ከዓለም ሕዝቦች ታሪክም እንዳየነው ብሔርተኝት ኅብረት ነው ያሰባስባል፣ ያስተሳስራል፣ ያረዳዳል፡፡ ብሔርተኝነት ጉልበት ነው ያበረታል፣ የማይገፋውን ያስገፋል፡፡ ብሔርተኝነት ማንነት ነው ራስን ይወልዳል፣ ያኮራል፣ ያስከበራል፤ በአንጻሩ ከብሐርተኝነት መራቅና መሸሽ እንደጨው ያሟሟል፣ ከሞላው ሰው መሀል ብቻን ያቆመቀል፣ እንደቄጠማ ያልማል፣ ለባሰ ውርደትና የበታችነት ያጋልጣል፣ጭው ወዳለ ምድረበዳ ይውስዳል፣ አውላ ሜዳ ላይ ይጥላል፣የአውሬ ሲሳይ ያደርጋል፣ መጠጊያ ያጣው ሁሉ ጎጆ መውጫ ያደርገዋል፡፡ የዐማራ ብሔርተኝነት ስንልም በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ በእንደነት ስም ተዳፍኖ የኖረውን ዐማራነት በዐማራ ብሔርተኝነት ተክተን የዐማራውን ሁለንተናዊ ጥቅም ማረጋገጥ ነው፡፡ ዐማራው ይህን ሁለንተናዊ ጥቅም ማረጋገጥ የሚችለው የወገኑን ሁለንተናዊ ሕይወት ለማሻሻል በሚያደርገው አስተዋጽኦ ልክ መሆን አለበት፡፡ ዐማራነትን ከዐማራ በመወለድ ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱ የዐማራ ሰው ለወገኑ ሁለንተናዊ ልማትና ጥቅም ዕውን መሆን የሚያደርገውን አስተዋጽኦ እንደወሳኝ የዐማራነት መስፈርትነት ማጎልበት ይኖርበታል፡፡
ይህ ደግሞ ባለፈት አራትና አምስት ዓመታት ብሔርተኝነቱን ከተዳፈነበት ፈልጎ አውጥቶ ውጤት በማስመዝገብ ላይ ባሉት ጥቂት ግለሰቦችና ቡድኖች ብቻ የሚከወን አይደለም፤ የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል፡፡ መዚቃኛው በድምፁ የዐማራ ማንነቱን ይናገር፣ የወገኑን ብሔርተኝነት ያነቃቃ፣ ደራሲውና ፀሐፊው የዐማራ ብሔርተኝነት ጥሪውን ያቅርብ፣ ያስተጋባ፣ የየመስኩ ምሁራንና ሊቃውንት ወገኑን አፍተልብ ወደዐውቀት ጥግ ይምራ፣ የሥነ ማኅበረሰብ ባለሙያው የማኅበረሰቡን ገንቢ እሴቶች የሚያጎለብትና የማይሆኑትን ደግሞ የሚያስወግድ ሥራ ይሥራ፣ የጤና ባለሙያው ለወጉኑ ጤንነት እንቅልፍ አጥቶ ይሥራ፣ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው በዝናብ ጠብታ ከተቆራኘ ግምታዊ ሕወት እንዲወጣ ሥልቶችን ይቀይስ፣

ባጠቃላይ ሁሉም የእኔ ነው ብሎ ማሰብ ትልቅ ጉዳይ ነው፤ ሁሉም በያገባኛል ብሔራዊ ስሜት መነሳትና ለዐማራው ወገኑ የቻለውን ሁሉ ያለማመንታት ለማበርከት ቁርጠኝነትና ዘግጁነት ሊኖረው ይገባል፡፡ የዐማራ ብሔርተኝነት ለዐማራ ሕዝብ ፍላጎት ተገቢውን ቦታ የሚሰጥ፣ እያንዳንዱ የብሔሩ አባል በብሔሩ ጉዳዮች ላይ የወሳኝነት ሚና እንዳለው የሚያምን ዴሞክራሲያዊ ባሕል የሠረጸው፤ በምንም መንገድ ግለኝነት የማያማልለው፣ የአንድም የብሔሩ አባል ሰበአዊ መብት የማይደፈርበት የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ሥርዓት መገንባት፣ በግለሰብም ሆነ በቡድን ደረጃ የተያዘ አስተሳሰብ የማያሰጋው የዐማራ አስተሳሰብ መፍጠርና ማዳበር ነው፡፡ ይህ ነው የዐማራ ብሔርተኝነት ማለት እንጅ እንዳዶች እንደሚሉት ዘረኝነት፣ ጎሠኝነት ወይም ደግሞ ከፍታዬና ደሜ ናት የሚላትንና ከዛሬ 8 (ስምንት) ሺህ ዓመት በፊት የገነባትን ሀገረ ኢትዮጵያን የሚያፈርስ አይደለም፡፡

ስለሆነም የዐማራ ብሔርተኝነት ለዐማራው ሕዝብና ብሔር የሁሉም ችግሮች ፈውስ ነው፡፡ የዚህ ሁሉ መጨረሻ ደግሞ ህልውናን አረጋግጦ በደስታና በፍስሀ፣ በሰላምና በብልጽግና የሚኖር ዐማራዊ ሕዝብ ተፈጥሮ ማየት ነው፡፡
ባጠቃላይ የዐማራ ብሔርተኝነት ዓላማውን አፍ ተልብ ታጥቆ ፣ አደጋ ላይ የወደቀውን ህልውናውን አረጋግጦ ዕድሜውን ሙሉ በልቶ ለማደር ሌት ተቀን ከመኳተን ወጥቶ የተሻለ ሕይወት ለመፍጠር የሚተጋ የዐማራ ማኅበረሰብ የመገንባት ራዕይ አንግቦ ከፊት ለፊቱ ሊገጠመው የሚችለውን ማናቸውንም ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ መሰናክሎችና ተግዳሮቶች ሁሉ አምክኖ ከግብ ማድረስ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ከዚህ በኋላ የዐማራን ብሔርተኝነት ለማዳከም ወይም ጨርሶ ለማዳፈን የሚደረግ ማናቸውም ዓይነት ሙከራ የአንድን ሠው የተፈጥሮ ገላ በሌላ ሰው ሠራሽ ገላ ቀይሮ የማይቻለውን ሰው እንዲሆን እንደማድረግ የሚቆጠር ነው፡፡

ባጠቃላይ ዐማራ ከብዙ ሺህ ዓመታት በፊት ማንነቱን ገንብቶ የጨረሰና የሕዝብነት ደረጃ የተጎናጸፈ ብቸኛው የዓለማችን ብቸኛው ብሔር እንጅ ዘር አይደለም፣ጎሳም አይደለም፤ በዚህም ምክንያት የዐማራ ብሔርተኝነትና ዘረኝነት በምንም መልኩ የሚገናኙ አይደሉም፡፡

ከሁሉም ከሁሉም ዐማራነት ይቅደም!!

ጣና እንደምን ተገደለ? (Ecocide By Design!) ( ዴቭ ዳዊት )

ምናልባትም እኛ ራሳችንን እናውቀዋለን ከምንለው በላይ ጠላቶቻችን የግል ስማቸውን የማወቅ ያህል ጠንቅቀው ያውቁናል የሚል ጥርጣሬ አለኝ። በተለይ ከእኛ ጋር ውጊያን ማድረግ እንዴት እንደሆነ አሳምረው ተክነውበታል።

በዘመናት መካከል ተፈትኖ ውጤታማ የሆነ ስልት አላቸው፤ ይኸውም በባህርይው አዝጋሚ፣በለሆሳስ የተቃኘ ግን ደግሞ የማያቋርጥ ውጊያ /Gradual Warfare/ ነው። ይህ የውጊያ ስልት መጥፎ ጎኑ ጦርነት እየተደረገብህ እንደሆነ እንኳን የምትባንነው አንድም እጅግ በጣም ከረፈደ አልያም ውጤቱን ልትቀለብሰው ብትሞክር እንኳን አስቀድሞ አንተ ከመንቃትህ በፊት ሙሉ አቅምህን ገዝግዞ የጨረሰው በመሆኑ የአቀበት ላይ ውጊያ /Uphill battle/ ስለሚሆንብህ ነው።

በተለይ በወያኔ ትግሬ ከተፈፀመብን ጥፋት መካከል የአንዳንዶቹን ውጤት ማወራረድ የሚጠበቅብን ዛሬ ላይ በዚህ ትውልድ ብቻ ሳይሆን ነገና በመጪው ትውልድ ጭምርም ነው። የጣና መገደል የዚህ አንዱ ማሳያ /microcosm/ ነው።

የጣና ሐይቅ ዋነኛ ችግር እምቦጭ የሚባለው አረም ቢሆን ኖሮ “የአማራ ህዝብ ጊዜ የማይሰጥ የህልውና አደጋ ገጥሞታል” የሚለውን እምነት በጽኑ እንደሚያምን አንድ ግለሰብ “ጣና ታሟል አሉ” የሚለውን የድምፃዊያን ዳኜ ዋለንና ሰለሞን ደምሌን ዘፈን እያዳመጥኩ በጥቂት ጥረት መስተካከል የሚችል ጉዳይ ነው በሚል የማልፈው ይመስለኛል።

ነገር ግን ጣና ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት “ይሙት በቃ!” የፖለቲካ ፍርድ ተወስኖበት የተገደለ፣ ዛሬ ጉሮሮው ላይ ሲር፥ሲር የምትል እስትንፋሱን ደግሞ ቧልተኛውና ዳተኛው ብአዴን/አዴፓ እንዲጨርሳትና ግብዓተ-መሬቱን እንዲያከናውን የተተወ መሆኑ ነው።

ጉዳዩን በአማራ ህዝብ ላይ ከተቃጡ የጅምላ ፍጅቶች ጎራ እንዲመደብ የሚያደርገው ደግሞ የጣና ሞት የሶስት ሚሊየን አማራዊያንን ህይወት የቀጥታ ሰለባ ከማድረግ አልፎ ጎንደርና ጎጃም የሚባሉ ቦታዎች ለሰው ልጅ መኖሪያነት ፍፁም ከማይመቹ ስፍራዎች ተርታ እንዲመደቡ የማድረግ እምቅ አቅሙ ነው። ይህም በአማራ ህዝብ ላይ በወያኔ ትግሬና ተላላኪዎቹ ከተፈፀመው የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማጽዳት፣ የሜዲካል አፓርታይድ እና መሰል ጥፋቶች ጎን ለጎን በአማራ ህዝብ ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ የስነ-ህይወትና ከባቢ ፍጅት /Ecocide/ ተፈጽሟል ብለን በድፍረት እንድንናገር ያደርገናል።

     ለመሆኑ የስነ-ህይወትና ከባቢ ፍጅት /Ecocide/ ምንድነው?

የስነ-ህይወትና ከባቢ ፍጅት /Ecocide/ እንዲህ እና እንዲያ ነው ከማለታችን በፊት ከጣና ክስተት ጋር የሚመሳሰል አንድ አለማቀፍ ምሳሌን አንስቶ መመልከት ለአንባቢ የተሻለ ግንዛቤ ያስጨብጣል።

በ1960ዎቹ አካባቢ በዓለም ላይ በመሬት ከተከበቡ ባህሮች /Inland Seas/ መካከል በትልቅነት የአራተኛ ደረጃ ላይ የነበረው በቀድሞዋ ሶቭየት፥ በዛሬዎቹ ደቡባዊ ካዛክስታንና በሰሜናዊ ዩዝቤክስታን መካከል የሚገኘው የኤራል ባህር /Aral Sea/ ነው። በወቅቱ ይህ ባህር የጣና ሐይቅን ሰላሳ ሁለት /32/ እጥፍ ይሆናል። እሱም እንዲህ እንደ ዛሬው ጣና በክፉዎች እጅ ወደቀና የፖለቲካ ፍርድ ተላለፈበት፤ ይኸውም የሀገሪቱን የእዝ ኢኮኖሚ በበላይነት የሚመራው የኮሚዩኒስት ፓርቲው የላይኛው አመራር ወደ ባህሩ የሚገቡ “አሙ ዳሪያ” እና “ሲር ዳርያ” የተባሉ ወንዞችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ በመጥለፍ የጥጥ እርሻ በሰፊው እንዲካሄድ አደረገ። በዚህም ሳይወሰን በባህሩ መሃል ላይ ትገኝ በነበረችው “ቮዝሮዝዴንዬ” በተባለችው ደሴት ላይ ከኢትዮጵያ ሳይቀር ዝንጀሮዎችን እየወሰዱ በደሴቷ ላይ እጅግ ገዳይ የሆኑ የባዮሎጂካል የጦር መሣሪያዎችን በምስጢር የመሞከሪያ ስፍራ አደረጉት።

ለጊዜው ሶቭየት በጥጥ ምርት ራሷን ከመቻል አልፋ ለአለም ገበያ በሰፊው አቅራቢ ሀገር ብትሆንም በሂደት ግን ይህ በትልቅነቱ ከአለም አራተኛ የነበረ ባህር ለሰላሳ ዓመታት ያህል በአዝጋሚ ሞት ሲሰቃይ ኖሮ ሶቭየት ስትበታተን መጠኑ የመለስተኛ ሐይቅ ያህል ሆኖ ሲቀር በሶቭየት የመጨረሻው ዓመት ላይ ራሽያዎች ይባስ ብለው ከላይ በተጠቀሰችው ደሴት ላይ ሁለት መቶ ቶን የሚመዝን ለባዮሎጂካል ጦር መሣሪያነት የሚውል የአንትራክስ ዕጭ /Weapon Grade Anthrax Spores/ ቀብረውበት ሄዱ።

ሶቭየት ስትበታተን የባህሩ አብዛኛው ክፍል የነበረው ቦታ “ካራካልፓክስታን” የሚባለው የዩዝቤክስታን ግዛት አካል ሆነ። በ1960ዎቹ የኤራል ባህር ይባል የነበረው ዛሬ የኤራል በረሃ የሚባል ሲሆን ይህ በረሃ /የትናንቱ ባህር/ ለሰው ልጅ መኖሪያነት እጅግ አደገኛ ከሆኑ ስፍራዎች አንዱ ነው፤ በመሆኑም ከሁለት ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዩዝቤክስታናዊያን በተለያዩ ካንሰርና ተያያዥ በሽታዎች እየተጠቁ ያለዕድሜያቸው በአጭሩ እንዲቀጩ ምክንያት ሆኗል። ያደረሰውን የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውስ ማንሳት እንዲሁ በከንቱ አንባቢን ማሰልቸት ነው የሚሆነው።

በፖለቲካዊ “ይሙት በቃ!” ውሳኔ የጥጥ ማሳ ታላቁን ባህር ሲበላ፤ የባህሩም ሞት፥ በሚሊየን የሚቆጠሩ ህዝቦችን፣ በባህሩ ውስጥና በአጠቃላይ በአካባቢው የነበረውን የስነ-ህይወት ምህዳር ክፉኛ አመሳቀለው። እንግዲህ ይህ ሆን ተብሎ የሚደረግ የስነ-ህይወት ምህዳር ምስቅልናና በሰዎች ላይ የሚያስከትለው ለከት የለሽ ጥፋት ነው የስነ-ህይወትና ከባቢ ፍጅት /Ecocide/ የሚባለው።

ወደ ጣና ጉዳይ ስንመለስም ከላይ ሲታይ “የምዕተ ዓመቱን የዕድገትና የልማት ዕቅድ ለማሳካት” በሚል ሽፋን በልማት ስም “የጣና-በለስ የኃይልና የመስኖ ልማት አገልግሎት” አልያም “The Tana Diversion Program” /TDP/ በሚል የዳቦ ስም ከጣና ሐይቅ ላይ 12 ኪ.ሜ. በሚረዝም ሰው ሰራሽ ቦይ /Tunnel/ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ በመውሰድ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያመነጭ ከተደረገ በኋላ ውሃው ወደ ጣና እንዳይመለስ ተደርጎ ከበለስ ወንዝ ጋር ይገናኛል። ከዚያም እስከ 140 ሺህ ሄክታር መሬት የሚሸፍን ለስኳር ምርት የሚውል የሸንኮራ አገዳ የመስኖ እርሻን እንዲያለማ ከተደረገ በኋላ የበለስ ወንዝ በሱዳን ድንበር አካባቢ ከአባይ ወንዝ ጋር ተቀላቅሎ ድንበር ተሻግሮ ይሄዳል።

ከላይ ሲታይ በስሱም ቢሆን ጤነኛ ይመስላል። ነገር ግን ጉዳዩን ከሁለት መሠረታዊ ነገሮች አንፃር ስንመዝነው የአማራ ህዝብ የምንጊዜም ጠላት የሆነው ወያኔ ትግሬ በአንድ ድንጋይ ብዙ ወፎችን የማርገፍ አላማ ይዞ የተነሳበት፤ በተለይም በልማት ስም ኢኮኖሚያዊ ትርፉን ከማግኘት ጎን ለጎን ተፈጥሮን እንደ መውጊያ መሳሪያ / Weaponization of Nature as an Offensive Tool/ በመጠቀም ለአማራ ህዝብ ዘመን ተሻጋሪ የቤት ስራን ሰጥቶ ያለፈ ጉዳይ ነው።

ዛሬ ላይ አይናችን ህያው ምስክር በሆነበት ሁኔታ የጣና ሐይቅ በአስደንጋጭ ሁኔታ ሲደርቅ ስናይ እንዲሁም የአባይን ግድብ በመጠነኛ ወጪ በአማራ ምድር ላይ እንዳይሰራ የተደረገበትን ፖለቲካዊ ውሳኔ ስንታዘብና እንዲሁም ሌሎች የልማት እድሎች ሆን ተብሎ ሲነፈገው የኖረ ህዝብ እንደዚህ ላለው ዘመን ተሻጋሪ አካባቢያዊ ጠባሳን ለሚያስከትል እንቅስቃሴ /Stigmatized Activity/ ሲመረጥ ከጅምሩም ይህ የአማራ ህዝብ ለምን ዓላማ እንደታጨ ግልጽ ነው።

የአማራን ህዝብና የአማራን ሀገር ለበለጠ ጥፋት እያዘጋጀ ያለው የዚህ ፕሮጀክት ውጤቶች ማለትም የኃይል ማመንጫውም ይሁን የመስኖ ስራ ፕሮጀክቱ ንብረትነቱ የፌደራል መንግስቱ መሆኑ ደግሞ ፈጣሪ ለህዝባችን የሰጠው ፀጋ በኢ-ፍትሐዊ መንገድ መበዝበዙ ሳያንስ የሚያስከትለውን ከባቢያዊ እና የአጠቃላይ የስነ-ህይወት ምህዳሩ ጥፋት ብቸኛ ገፈት ቀማሽ የሆነው የአማራ ህዝብ መሆኑ ነው።

ሲጀመር ይህ የጣና-በለስ ፕሮጀክት /”The Tana Diversion Program” /TDP// በቀላል የዲዛይን ስራ መስተካከል የሚችል ሆኖ ሳለ በእኔ እምነት ሆን ተብሎ በፖለቲካ ውሳኔ እንዲያ እንዲሆን በመደረጉ በሁለት ተመጋጋቢ ምክንያቶች በሐይቁ እና በዚያ ዙሪያ ላይ የስነ-ህይወት ምህዳሩ ላይ መዛባት /Ecological Imbalance/ እንዲፈጠር ተደርጓል።

1ኛ. የሐይቁ ተፈጥሯዊ የውሃ ፍሰት ሚዛን እንዲናጋ ማድረግ /Breaking the Water Balance/:- ይህ የሆነው የፕሮጀክቱ ባህርይ በራሱ ሙሉ በሙሉ ከሐይቁ ላይ ውሃን በመውሰድ ብቻ /Irreversible Consumption/ ላይ የተንጠለጠለ በመሆኑ ወደ ሐይቁ ከሚገባው ውሃ ይልቅ ከሐይቁ የሚወሰደው ውሃ በመብለጡ የሐይቁ መጠን በጣም ሊታይ በሚችል ሁኔታ ሊጠብ ችሏል። አሁን ባለው አያያዝም ከዚህ በላይ እየጠበበ ከመክሰም የሚያድነው የለም።

2ኛ. ከላይ ባየነው መንገድ እየደረቀና እየጠበበ የመጣው ሐይቅ “ዕድሜ ለብአዴን ይሁንና¡” በሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች የብክለት ሰለባ ሆኗል።

2.ሀ. የሐይቁን መድረቅ ተከትሎ ውሃው ሲሸሽ በተፈጠረው ረግረጋማ ቦታ ላይ የሚሰራውና በከፍተኛ ሁኔታ ኖርዌይ ሰራሽ የሆነውን ግን ደግሞ በአውሮፓ እና አሜሪካ ለአገልግሎት እንዳይውል የታገደን ማዳበሪያ በሩዝ እና መሰል እርሻዎች ላይ በመጠቀም ከፍተኛ የሆነ የኬሚካል ብክለት ሲሆን /Pesticide–Intensive Farm/

2.ለ. ከመኖሪያ ቤቶችና ከሆቴሎች የሚወጡ ቆሻሻዎች ወደ ሐይቁ እንዲፈሱ መደረጋቸው /Household and Municipal Waste Disposal/ ሌላው የብክለት ምንጭ ነው።

እንግዲህ እነዚህ ሁኔታዎች ናቸው የጊዜ ቦምብ ሆነው ነገ የሶስት ሚሊየን አማራዊያንን ህይወት እና የመኖሪያ ስፍራ የቁም ሲኦል ሊያደርጉ እየተዘጋጁ ያሉት።

ሙይናክ በምትባለው የዩዝቤክስታን ከተማ ውስጥ “የሰው ልጅ እንዴት እንዲህ ሆኖ ይወለዳል?” ብለህ በድንጋጤ እስክትጠይቅ ድረስ ቀልብህን የሚገፍ ክስተት ስታይ የስነ-ህይወትና ከባቢ ፍጅት /Ecocide/ ማለት የመጨረሻ ውጤቱ በኑክሌር ከመመታት እንደማይተናነስ ትታዘባለህ። ታዝበህም አትቀር ነገር “Fools rush in where angels fear to tread.” የሚለው የአሌክዛንደር ፓፕ አባባል ኅሊናህን ሰቅዞ ይይዝሃል።

           "በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ"

ከላይ ለማየት እንደሞከርነው የጣና-በለስ ፕሮጀክት /”The Tana Diversion Program” /TDP/ በሐይቁ ላይ የስነ ህይወት ምህዳር መዛባት /Ecological Imbalance/ ከፈጠረበት ምክንያት አንዱ የሐይቁን የውሃ ፍሰት ሚዛን ማናጋት /Breaking the Water Balance/ ሲሆን የእንቦጭ አረም በሀይቁ ላይ መከሰት ደግሞ ከአረሙ ባህርይ አንፃር የተጋረጠውን አደጋ በማፋጠን በኩል ነገሩን “በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ” እንዲሆን አድርጎታል።

ከቀን አንድ ጀምሮ በእምቦጭ ዙሪያ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የትንታኔ ስራ በተለያዩ ሰዎች በመሰራቱ ያንን ዛሬ እንደአዲስ ልናነሳው አይገባም። ከዚያ ይልቅ ይህን አደገኛ አረም ለመቆጣጠር ከመትጋት ይልቅ ዳተኛውና ቧልተኛው ብአዴን/አዴፓ የሄደበትንና እየሄደበት ያለውን መንገድ መመልከት በቀጣይ ምን ቢደረግ ይሻላል? የሚለውን ለመወሰን ይረዳል።

              የብአዴን/አዴፓ ቧልቶች

ብአዴን/አዴፓ በአማራ ምድር ላይ በህግ መታገድ ያለበት ድርጅት ነው የሚል አቋም ካላቸው ሰዎች መካከል ራሴን ከማገኝበት ምክንያት አንዱ ገና ከፍጥረቱ ጀምሮ ፀረ-አማራ ተላላኪ በመሆኑ ብቻ አይደለም። ይልቁን ባለችው አቅም እንኳን መወጣት ያለበትን ህዝባዊ ኃላፊነት መሸከም የማይችል፣ ቅቡልነት ያለው አመራር እንዲኖረው ሊያደርገው የሚችለውን ዝቅተኛውን የሞራል ልዕልና /The Moral Minimum for Legitimate Rule/ የሌለው ቀትረ-ቀላል ተላላኪና በህዝብ ጥቅምና ህልውና ላይ የሚቀልድ ድርጅት በመሆኑ ነው።

የእንቦጭ አረምን በተመለከተም ብአዴን/አዴፓ የጣና ሐይቅ በጣና-በለስ ፕሮጀክት /”The Tana Diversion Program” /TDP/ እንዲገደል ከተደረገ በኋላ ቀሪ እስትንፋሱ ከማለቋ በፊት አፋጣኝና ዘላቂ ውጤት ያለው መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ አይንና ጆሯችንን እስክንጠራጠር ድረስ ዛሬም ድረስ የቧልት ስራ ሲሰራ ነው የሚታየው።

ቧልት ቁጥር 1. ሐይቁን ላልሰለጠኑ ተለማማጆች የመለማመጃ ላቦራቶሪ ማድረግ:-

በአማራ “ክልል” የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና በከተሞች የሚገኙ ብረት በያጆች ሌላ የፈጠራ ስራ የሌለ ይመስል “የእንቦጭ አረም ማስወገጃ ማሽን” ሰሩ የሚል ዜና በሳምንት አንድ ጊዜ መስማት በጣም የተለመደ ነው። እውነታው ግን ተሰሩ የተባሉት በሙሉ ውጤታማ አይደሉም!!!

እስኪ ክስተቱን ወደግል ህይወታችን መልሰን እንየው። ብንታመም የመጀመሪያ ስራችን የሚሆነው አቅማችን በፈቀደው መልኩ ጥሩ የሚባል ሐኪም ፈልገን እንታከማለን እንጂ “ቆይ ትንሽ ታገሰኝ። ለጊዜው ሀኪም አይደለሁም። አጥንቼ ሀኪም ከሆንኩ በኋላ አክምሃለው” ወደሚለን የእኔ ቢጤ ጨዋ ጋር አንሄድም።

በድጋሚ “ዕድሜ ለብአዴን ይሁንና¡” ጣና ግን ለዚህ አልታደለም። ይልቁን የጣና አዝጋሚ ሞት የብአዴን/አዴፓ የቧልት ማድመቂያ ነው የሆነው። ሲፈልግ “ለጣና ያሰባሰብኩትን ገንዘብ እስከዛሬ ጥቅም ላይ አላዋልኩትም” ብሎ እንደደህና ወሬ ያወራል፤ ሲብስም “አረሙን ለማጥፋት ተገዝተው የመጡት ጥንዚዛዎች ማደሪያቸው በነፋስና በዝናብ በመፍረሱ ተበተኑ” የሚል ዜና እያስነገረ፥ ሳንወድ በግድ “አለበለዚያውማ በዘዋል ልጅ ሊዳር!” እንድንል ያደርገናል።

    ቧልት ቁጥር 2. "ከእንቦጭ ነዳጅ /Bio-diesel/ እናመርታለን"

ይህ እ.አ.አ በ2012/2013 ዓ.ም. የተፈፀመ የብአዴን ታሪክ ነው። አንድ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረ በኋላም የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነ ከዚያው ከደቡብ አካባቢ የመጣ ሰው ከጃትሮፋ ተክል ነዳጅ ማምረት የሚችል መጠነኛ የጎጆ ኢንደስትሪ ይሰራና ከአዕምሮ ፈጠራ መስሪያ ቤት የባለቤትነት ማረጋገጫና ከሳይንስና ቴክኖሎጂ መስሪያ ቤት ደግሞ ሽልማት ይበረከትለታል።

ይህን ዳር ቆሞ ሲታዘብ የከረመው ብአዴንም በአማራ መልሶ ማቋቋም ልማት ድርጅት /አመልድ/ አማካኝነት በወሎ /ከኦሮሞ ወረራ በፊት ቤተ-አማራ/ ባቲ ወረዳ ሶስት መቶ አርሶ አደሮችን አደራጀው ይልና ይህን የጃትሮፋ ተክል እንዲያመርቱ ያደርጋል። በዚህም ሳይወሰን ከላይ የጠቀስነውን የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበረውን የፈጠራ ባለሙያ ያነጋግርና ከጃትሮፋ ተክል ነዳጅ ማምረት የሚችለውን የጎጆ ኢንደስትሪ በባቲ ያስተክላል።

በሚሊየኖች የሚቆጠር ብር አውጥቶ ሲያበቃ፥ “አደራጀሁ” ያላቸውን አርሶ አደሮች በአግባቡ መያዝ ባለመቻሉ ምክንያት የጃትሮፋ የባዮ ዲዝል ታሪክ የውሃ ሽታ ሆኖ ሲቀር ያቺ መጠነኛ የጎጆ ኢንደስትሪም ዛሬም ድረስ በባቲ እንደጅብራ ተገትራ ቀርታለች። የብአዴን ሌጋሲ እንግዲህ እንዲህ ነው።

ይህ ልምድና ታሪክ ያለው ቧልተኛው ብአዴን ነው እንግዲህ ከአንዳንድ ደፋር “ምሁር” ነን ባዮች ጋር ሆኖ በሌላ ትርክት “ከእንቦጭ ነዳጅ አወጣለሁ” የሚለን። እንቦጭ እንደጃትሮፋ ለቧልተኞች ጊዜ የሚሰጥ አለመሆኑን ብአዴን/አዴፓ ጠፍቶት አይደለም። ይልቁን ብአዴን/አዴፓ ቧልተኛ ብቻ ሳይሆን ዳተኛም ስለሆነ ጭምር ነው እንጂ!!!

በዚህ አጋጣሚ ወደ ድምዳሜያችን ከመሸጋገራችን በፊት አንድ ነገር ተናግረን እንለፍ።
በዚህ በጣና ሞት ላይ የቆመው የጣና-በለስ ፕሮጀክት /”The Tana Diversion Program” /TDP/ ላይ የመስኖ ፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑት ንብረትነቱ የፌደራሉ መንግስት የሆነው የስኳር ፕሮጀክት ብቻ ሳይሆን ካሣ ተክለብርሃን የሚባለው ትግሬ የብአዴን አባል የክልሉ የኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ በነበረበት ወቅት ለወያኔ ትግሬ ባለስልጣናት እና ልጆቻቸው በወረራ ባደላቸው የምዕራብ ጎጃም የአማራ መሬት ላይ የአግሮ ኢንደስትሪ ባለሀብት የሆኑ ትግሬዎች ጭምር ናቸው።

ከነዚህም መካከል የስብሐት ነጋ ልጅ የሆነችው ህያብ ስብሐት ነጋ አንዷ ስትሆን በምዕራብ አማራ በአዊ ዞን በጃዊ ወረዳ አንድ ሺህ ሄክታር መሬት ያለውና ሰባ አምስት ሚሊየን ብር የመነሻ ካፒታል ያለው “ህያብ የግብርና ኢንደስትሪ” በመባል የሚታወቀው ድርጅት ባለቤት ናት።

መቼም ህዝባችንን የእኔ የሚለው መሪ ባለመኖሩ ይህ በምዕራብ አማራ የተፈፀመው የመሬት ቅርምት ለከት የለሽ ከመሆን አልፎ ከራሳቸው ባሻገር ገና የሀይስኩል ትምህርታቸውን እንኳን በአግባቡ ባልጨረሱ ልጆቻቸው ስም ሳይቀር የተፈፀመ መሆኑ ነው። ለዚህም ማሳያ የሚሆነን የስብሐት ነጋ ልጅ የሆነችው ህያብ ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን መሬት በወሰደችበት ወቅት በጣልያን ሀገር ፓድዋ በሚባል ስፍራ የሀይስኩል ትምህርቷን እየተማረች ነበር። በዚሁ አጋጣሚ የስብሐት ነጋ የቅርብ ዘመድ የሆኑ ሰዎች ሆላንድ ከሚገኝ የአግሮ ኢንደስትሪ ድርጅት ጋር በማሴር በጤፍ ላይ የፈፀሙትን የስነ-ህይወት ዘረፋ /Bio-Piracy/ እንዳስፈላጊነቱ በሌላ ጊዜ እንመለከተዋለን።

ወደ ተነሳንበት ቁምነገር ስንመለስም መሬታችንን ተቀራምተው፣ የሐይቃችንን ህልውና አደጋ ላይ ጥለው እንዲሁም አጠቃላይ የስነ-ህይወትና ከባቢ ውድመት /Ecocide/ ፈጽመውብን ሲያበቁ አማራዊ ምድራችን የጭሰኛ መፍለቂያ /Peon Factory/ ሲሆን እያየን ጦርነት ውስጥ አይደለንም ልንል አንችልም።

ከዚያ ይልቅ እያስፈራኝ የመጣው ይህን መሰል እና ከዚህም በላይ የከፋ ስንት አስጨናቂ ጉዳይ ከብቦን እያለ አሁን፥አሁን የአማራ ጉዳይ ያገባናል ባዮች ጊዜና ኃይላቸውን የሚያጠፉበት ነገር እንቶ ፈንቶ በሆነ አጀንዳ እየሆነ ስናይ ያሳፍራልም፣ያሳዝናልም፣ ያሳስባልም።

እንዳስፈላጊነቱ በሌላ ጊዜ ይህንን ጉዳይ በግልጽ አውጥተን የምናነሳው ይሆናል። ይሁን እንጂ የአማራ ህዝብ ዙሪያ ገባውን የህልውና አደጋ ተጋርጦበታል ስንል ግን በእርግጥም መሬት የያዘ እውነትን መሠረት አድርገን ነው።

ቸር እንሰንብት።
የዐማራ ብሔርተኝነት ይለምልም!!!

”ሰላሌ/ሰላላ- የአማራ ጥንታዊ ርስት” (Achamyeh Tamiru)

ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ አዛዥ፣ በ1953 ዓ.ም. እነ ጀኔራል መንግሥቱ ንዋይ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ላይ የሞከሩትን ስዒረ መንግሥት በቀዳሚነት ያከሸፉትንና ደርግ ከጭሰኞቻቸው ጋር በግፍ የረሸናቸውን የጄኔራል ታደሰ ብሩን ሐውልት በትናንትናው እለት በምድረ ሸዋ በጥንታዊቷ የአማራና ርስት በሆነችው በሰላላ/ሰላሌ መርቋል።

ጀኔራል ታደሰ ብሩ አባታቸው አቶ ብሩ ኬኔ ናቸው። አቶ ብሩ ኬኔ የከረዩ ኦሮሞ ሲሆኑ የትውልድ ሀረጋቸው እንደሚከተለው ነው፤ ብሩ ኬኔ ጅሩ ኡመቶ ጉታ ሞገር ደራ አቦቴ ሲንቼል ሲቡ ኢሌ አባዶ ሊበን ከረዩ ኦቦ። በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አዋሽን ተሻግሮ ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ወደ ነበሩበት ወደ አማራ ምድር ወደ ግራርያ አውራጃ ሰላላ ወረዳ የመጣው የመጀመሪያው ትውልዳቸው አባዶ ሊበን ነው።

የጄኔራል ታደሰ አባት አቶ ብሩ ኬኔ ጸረ ፋሽስት አርበኛ የነበሩ ሲሆኑ ሕይዎታቸው ያለፈው ከራስ ካሳ ጋር በመዝመት ለአገራቸው ተሰልፈው ሲዋጉ በፋሽስት ጥሊያን የመርዝ ጭስ ነው። አባቱ ሲሞቱ የ13 ዓመት ልጅ የነበረው ታደሰ ብሩ የአባቱን ፈለግ በመከተል ፋሽስት ጥሊያንን ለመፋለም ዱር ቤቴ ባለበት ወቅት በፋሽስት ጥሊያን ተማርኮ ወደ ሞቃድሾ እስር ቤት ውስጥ ተሰቃይቷል።

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት እንደገና ሲቋቋምና ፋሽስት ጥሊያን ያሰራቸው የኢትዮጵያ አርበኞች ከሶማሊያ እስር ቤት ሲለቀቁ ወጣቱ ታደሰ ብሩም የጦር ሰራዊት አባል በመሆን አገሩን ማገልገል ጀምሯል። የኢትዮጵያ ፖሊስ እንደ ተቋም ሲመሰረት ጀኔራል ጽጌ ዲቡ ከሶስተኛው ክፍለ ጦር ወደ አዲስ አበባ ይዘዋቸው ከመጡት ወጣት የሰራዊቱ አባላት መካከል አንዱ ታደሰ ብሩ ነበሩ። በጊዜ ሂደት በሹመት ላይ ሾመት እየደረቡ በማደግ የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ አዛዥ ሆነው በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ተሹመዋል።

መግቢያ ላይ እንዳወሳሁት ጀኔራል ታደሰ ብሩ የተወለዱበት አገር ሰላሌ ኦሮሞ ወደ ቦታው ከመስፋፋቱ በፊት የአማራ አገር ነበር። በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የቱለማ የኦሮሞ ጎሳዎች ከብቶቻቸው እየነዱ ሸዋን ወረው ባለ ርስቱን ገበሮ፣ ጠለታና ገርባ በማድረግ የቦታውን ስያሜ ሰላሌ ብለው corrupt ከማድረጋቸው በፊት የቦታው ትክክለኛ መጠሪያ ሰላላ የሚል የአማርኛ ስም ነበር። ሰላላ አማርኛ ነው። ሰላላ የሚለው የአካባቢ መጠሪያ ኦሮሞ ወደ ቦታው ከመስፋፋቱ በፊት በተጻፈው የዐፄ ሱስንዮስ ዜና መዋዕል ውስጥ ተጠቅሶ ይገኛል። የዐፄ ሱንዮስ ጸሐፌ ትዕዛዝ አዛዥ ተክለ ሥላሴ ዐፄ ሱስንዮስ በአያታቸው ምድር በሸዋ ያሳለፉትን የወጣትነት ዘመን በገለጹበት የዜና መዋዕሉ ክፍል እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፤

“ወበውእቱ ምድረ ረከቦ ዓብይ ምንዳቤ ረኅብ እስከ በልኡ ሠራዊቱ አሣእነ እግሪሆሙ። እስመ ተኃጥ አእክል ለሲሳይ በእንተ ዘኮነት ይእቲ ምድር በድወ ወዓጸ። ወእምዝ ተንሥአ እምይእቲ ምድር ወአመልአ ፍኖቶ መንገለ ግንድ በረት ። ወእምዘ የሐውር በጽሐ ምድረ ሰላላ።” [Pereira, F. M. E. (1892). Chronica de Susenyos, Rei de Ethiopia: Texto ethiopico: destinado á X sessão do congresso internacional dos Orientalistas. Imprensa nacional; Page 22 ]

ትርጉም፤

ያንጊዜም ሐንገታሞ በሚባል ስፍራ ተቀመጠ። በዚያም ስፍራ ታላቅ የርሐብ ችግር ገጠመው፤ ተከታዮቹ የእግራቸውን ጫማ እስኪበሉ ድረስ። ለምግብ የሚሆን እህል ታጥቷልና፤ቦታዋ ምድረ በዳና ደረቅ ስለሆነች። ከዚህ በኋላ፣ ከዚያች ቦታ ተነስቶ ወደ ግንደ በረት ጉዞ አደረገ። ሲሄድም ሰላላ ደረሰ።

ሐንገታሞ ደብረ ብርሀን አካባቢ የሚገኝ አገር ነው። ግንደ በረትም አሁንም ድረስ ሸዋ ውስጥ የሚገኝ ቦታ ነው። ዜና መዋዕሉ እንደሚነግረን ዐፄ ሱስንዮስ ከደብረ ብርሀን አካባቢ ተነስቶ ወደ ግንደ በረት ለመሄድ ሰላላ አድሯል። ይህ ሁሉ ታሪክ የተፈጸመው ኦሮሞ ወደ ቦታው ከመምጣቱ ከአንድ ክፍለ ዘመን በፊት ነው።

ሰላላ በአማርኛ አነጋገር ውስጥ በብዛት ጥቅም ላይ ይውላል። ጎጃም ስናድግ ልጆች ሳለን የዘመን መለዋጫ በዓልን ሲከበር በወጣቶች በሚዜሙ ጥዑመ ዜማዎች ውስጥ ሰላላ ጥቅም ላይ ይውል ነበር። በበዓሉ እለት ከሚዜሙት ጥዑመ ዜማዎች መካከል ሴት ቆነጃጅት እንዲህ እያሉ ያዜሙ ነበር፤

የቅዱስ ዮሐንስ ያልዘፈነች ቆንጆ፣
ቆማ ትቀራለች እንደ ሰፈር ጎጆ፤
እቴ አደይ አበባ ነሽ፣
ዉብ ነሽ ዉብ ነሽ፤

ልጃገረዶች ይህንን ዜማ እንግጫ እየነቀሉ ሲያሰሙ፤ ጎረምሶች ወንዶች ደግሞ የሚከተለውን እያዜሙ ወደ ልጃገረዶች ይሄዳሉ፤

እንግጫችን ደነፋ፣
ጋሻዉን ደፋ፤
እንግጫዬ ነሽ ወይ፤

ኮረዶች ይህንን ሲሰሙ እንዲህ ብለው ይመልሳሉ፤

እሰይ እሰይ፣
የቅዱስ ዮሐንስ የመስቀል የመስቀል፤
የላክልኝ ድሪ ሰላላ መላላ፣
መልሰህ ዉሰደዉ ጉዳይም አይሞላ፤

በዚህ ጊዜ ጎረምሳው ለወደዳት ልጃገረድ ማተብ ያስርላታል። ጨዋታው እንዲህ እንዲያ እያለ ይደራ ነበር. . .

የሆነው ሆኖ የኦሮሞው ጀኔራል የታደሰ ብሩ መታሰቢያ ሐውልት የቆመበት አገር ስላሌ/ ሰላላ የአማርኛ ስም ያለው የአማራ ምድር ነበር። ሰላሌ ወደሚል የኦሮምኛ ድምጸት ያለው ስያሜ የተለወጠው ከኦሮሞ መስፋፋት በኋላ ነው።

ሐውልቱ የዘመኑን እውነት የሚያንጸባርቅ አይደለም። ጀኔራል ታደሰ ብሩ በደርግ ሲገደሉ ብቻቸውን አልነበሩም። ጄኔራል ታደሰ ብሩን ደርግ የገደላቸው ከጭሰኞቻቸው ጋር ነበር። ሐውልት ሲቆምላቸው ግን አብረዋቸው የተገደሉት የታደሰ ብሩ ጭሰኞች መታሰቢያ አልቆመላቸው።

ኦነጋውያን ጀግና ለመፍጠር ስለሚፈልጉ የነሱን ትርክት ፈጥረው በጄኔራሉ ታሪክ ዙሪያ የራሳቸው ትርክት ፈጥረው ብዙ ውሸት አምርተዋል። ኦነግ የጀኔራል ታደሰ ብሩን የኢትዮጵያ አርበኛነትና የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት የፈጥኖ ደራሽ አዛዥ እንደነበሩ ማውሳት አይፈልጉም። በመኢሶን ቋንቋ ጀኔራል ታደሰ ብሩና ኮለኔል ኃይሉ ረጋሳ ፊውዳሎች ነበሩ። ጀኔራል ታደሰና ኮሎኔል ኃይሉ ጫካም የገቡት ኦነጋውያኑ እነ ባሮ ቱምሳ፣ ዲማ ነገዖና ዘገዬ አስፋው ያረቀቁትን የደርግን «የመሬ ላራሹ» አዋጅ ተቃውመው ነው።

ይህ ደርግና መኢሶን ያቀረቡት ትርክት ብቻ አይደለም። ለእድገት በኅብረት ዘመቻ የመሬት ላራሹን አዋጅ ሊያስፈጽሙ ከዘመቱ ተማሪዎች መካከል ጀኔራል ታደሰ ብሩ በሚንቀሳቀሱበት አካባቢ መሬት ለጭሰኞች ለማከፋፈል ሲሞክሩ ጀኔራል ታደሰ ተማሪዎችን መሬት ለጭሰኞች ማከፋፈል አትችሉም ብለው ያባረሯቸው ተማሪዎችም አረጋግጠዋል። የኃይሌ ፊዳ ድርጅት መኢሶንም እነ ታደሰ ብሩና መለስ ተክሌ በአንድ ቀን በተረሸኑበት ወቅት በልሳኑ ባወጣው መግለጫ ተራማጆቹ እነ መለስ ተክሌ ከፊውዳሎቹ ከነ ታደሰ ብሩ ጋር መገደል የለባቸውም የሚል መግለጫ አውጥቶ ነበር።

ለማንኛውም ኢትዮጵያ እንዲህ ነች! በአማራ ጥንተ ርስት ላይ የኦሮሞ ጄነራል ሐውልት ማቆም የሚቻልባት ምድር ናት 🙂

ከታች የታተመው ፎቶ መጋቢት 5 ቀን 1967 ዓ.ም. አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጀኔራል ታደሰ ብሩ ከነ ጭስኞቻቸውና ኮሎኔል ኃይሉ ረጋሳ በሻለቃ ተስፋዬ ገብረ ኪዳን [ኋላ ጀኔራልና ከመንግሥቱ ኃይለ ማርያም በኋላ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት የበነበረው – የኦሮሞ ነገድ ተወላጅ ] በሚመራው የደርግ አሳሾች በተያዙበት ወቅት የተነሱፎቶ ነው።

ከኢትዮጵያ ትቅደም፤ ወደ ኦሮሞ ይቅደም !- (ከጥበበ ሣሙኤል ፈረንጅ)

ኢትዮጵያ ከሶስት ሺህ ዓመትታ በላይ ታሪክ ያላት ሃገር ናት ሲባል፤ አሁን ያላትን መልክአ ምድር ይዛ ቆይታለች ማለት አይደለም። እንደማንኛውም በዓለማችን እንዳሉ ሃገራት፤ ኢትዮጵያ የተገነባቸው፤ በሰዎች ከቦታ ቦታ ፍልስት፤ ግጭቶች፤ ጦርነቶች፤ ሕይወታቸውን ከዘላንነት ወደ ቋሚ አራሽነት በቀየሩ፤ በአጠቅላይ፤ ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተው በሰፈሩ ሰዎች ነው። ሌላውን “መጤ” የሚል፤ በእራሱ ስሌት እሱም “መጤ” መሆኑን መቀበል አለበት፤ ልክ እንደ ሌላው፤ የእርሱም ዘር ማንዘሮች ከሌላ ቦታ መጥተው ነው ዛሬ “መሬቴ” የሚላትን ቦታ የያዘው። ይህንን መካድ፤ የሕብረተሰብ እድገት ሳይንስን መካድ ይሆናል። እግዚአብሔር፤ ወይም የተለየ ሰማያዊ ኃይል፤ ይህች መልክአ ምድር ለኢትዮጵያ ነች ብሎ ቀርፆ የሰጠን የለም። ይህ ለኦሮሞ፤ ይህ ለአማራ፤ ይህ ለትግሬ ወዘተ ብሎም፤ ያከፋፈለ ሰማያዊ ሃይል የለም። ኢትዮጵያ እንደ ሃገር፤ እንደ ማህበረሰብ፤ በጉልበት የተገነባች ሃገር ናት። እያንዳንዱ ብሔር/ብሔረሰብ ዛሬ የኔነው የሚለውንም ቦታ የተቆጣጠረው በተመሳሳይ መልክ ነው። ድንበር፤ ሃገር፤ ክልል፤ የምንለው ሰው ሰራሽ ነው። ይህ የመላው አለም የሃገራት ግንባታዎች ታሪክ ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያን ከሌላው የተለየ አያደርጋትም። ይህን መሰረታዊ የሰዎችን የሕብረተሰብ ዕድገት አመጣጥ ማንሳት የፈለግኩት፤ ይህንን ሀ-ሁ በቅጡ ያልተረዱ “የፖለቲካና ታሪክ ምሁሮቻችን”፤ ወይም ይህን በቅጡ ተረድተው እኩይ አላማ ይዘው፤ በተዛባ ትርከት የሚያተራምሱን ኃይሎች አንዱን መጤ፤ ሌላውን ባለሃገሬ ብለው ሊኮንኑ የሚችሉብት መቆምያ እግር እንደሌላቸውም ለመጠቆም ነው። ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ከተቆረቆረችበት ጊዜ ጀምሮ፤ በሃገሪቱ የኖሩ ዜጎች፤ ከየትኛውም ዘር ይምጡ፤ ለበጎ እድገቷም፤ ለተሰራው ግፍና እኩይ ምግባር እንደ ግለሰብ፤ ወይም እንዳደራጁት ቡድን፤ በግለስብ እና በቡድናቸው ሊወቀሱ፤ ወይም ለሰሩት በጎ ሥራ ሊመሰገኑ ይገባል እንጂ፤ ግለሰብ ወይም ቡድን በሰራው፤ የአንደ “ዘር” ማህበረሰብ፤ በጅምላ ሊወቀስም ሆነ ሊሞገስ አይገባውም። በማንኛውም ዘር ውስጥ፤ መጥፎ ሰው እንዳለ ሁሉ ጥሩም ሰው አለ። መጥፎው ሰው የሚወክለው እራሱን ብቻ ነው፤ ጥሩውም ሰው እንደዛው። ምንም እንኳን፤ አንድ ሰው የኖረበት ማህበረሰብ እና አካባቢ በግለሰብ አስተሳሰብ ላይ ተጽእኖ ቢኖረውም፤ ለሚያደርጋቸው ማንኛውም ድርጊቶች ሃላፊነቱ የግለስቡ ነው። ሰውን ከእንስሳ የሚለየውም ከአካባቢው የሚያገኘውን ትምህርት እና የኑሮ ዘይቤ አመዛዝኖ ጥቅምና ጉዳቱን አይቶ የሚወሰደውን እርምጃ ሚዛናዊ ማድረግ መቻሉ ነው። ሆኖም፤ የሰው ልጅ፤ ስስታም እና ግላዊ በመሆኑ፤ ከስብእናው ይልቅ “እንስሳነቱ” ሲብልጥበት በተደጋጋሚ አይተናል። የሰው ልጅ አእምሮው እየሰፋ፤ እውቀቱ እየዳበረ ሲመጣ፤ ከቤተሰብ፤ ወደ ማህበረሰብ፤ ከዛም ወደ ህብረተሰብ እና ሃገር ግንባታም አድጓል። እነዚህ የእድገት ደረጃዎቹ በሰው ልጅ መካከል የፈጠሯቸው በጎ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ፤ መጥፎ ነገሮችም አሉ።

ሃገራችንም በዚህ ምስቅልቅል እና የተጠማዘዘ ጎዳና አልፋ እዚህ ደርሳለች። የሰው ልጅ ስልጣኔው ዝቅተኛ በነበረበት ጊዜ፤ “ታላቅነት” ያስገኝልኛል የሚለው አመለካከቱ፤ አንዱ፤ ሌላውን በጉልበት አንበርክኮ በመግዛትና ግዛቱን በማስፋት ላይ የተመረኮዘ ነበር። ከዘመናት በኋላ፤ እውቀቱ እየሰፋ ሲመጣ፤ ለሰው ልጅ የሚጠቅመው፤ ተከባብሮ መኖር እና፤ መሪዎቹን መርጦ እራሱ በሚያወጣው ሕግና ደንብ መተዳደር መሆኑን በመረዳት ባዋቀራቸው ተቋማቱ፤ የእኔ ብሎ በከለለው መልክአ ምድር፤ እነሆ ዛሬ ዓለም ላለችበት ሥልጣኔ በቅታለች። ይህ ማለት ግን የሰው ልጅ የመጨረሻ የእድገት ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት አይደለም። ዛሬም የሰው ልጅ፤ የአንድን ሃገር ብቻ ሳይሆን፤ መላው ዓለም ላይ ያሉ ዜጎችን ሕይወት የተሻለ ለማድረግ በጥናት እና ምርምር ላይ ይገኛል። ይህ ማለት ሁሉም ሃገራት ተመሳሳይ እና እኩል የእድገት ደረጃ አላቸው፤ ሁሉም ሰዎች ተመሳሳይ የማሰብ አቅም አላቸው ማለት አይደለም። ለዚህም የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። ለአሁኑ እዛ ዝርዝር ውስጥ አልገባም።

እንደ ሁሉም ሃገራት፤ ኢትዮጵያ፤ ከጋርዮሽ የህብረተሰብ እድገት፤ ዛሬ ያለችበት የእድገት ደረጃ ላይ ስትደርስ፤ ብዙ መሰናክሎችን አልፋ ነው። በዚህ ጉዞ፤ ሕዝብ ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ከትውልድ ትውልድ በተላለፈ ሰንሰለት፤ በተለያየ አካባቢ በመስፈር ማህበራዊ ኑሮውን ገንብቷል። ተጋብቶ በመዋለድ በደም ተሳስሯል፤ በማህበራዊ ኑሮ፤ በኢኮኖሚና በፖለቲካ አስተዳደር ተጣምሯል። አንዱ ገዢ እራሱን ወይም ቤተሰቡን በመወከል፤ ሌላውን አስገብሯል፤ በየትኛውም ወቅት፤ አንድ መላ ብሔር ወይም ብሔረሰብ ሌላውን የጨቆነበት ወቅት ለመኖሩ ምንም ጭብጥ መረጃ የለም። እንደውም ብዙዊቹ ነገስታት፤ ከአንድ ዘር ብቻ የመጡ ላለመሆናቸው የታሪክ ፀሃፊዎች ዘግበውታል። ብዙ ኦሮሞ ወገኖቼ በአማራነት የሚወቀሱዋቸው ዓፄ ምኒሊክ፤ የኦሮሞ፤ የወላይታ፤ እንዲሁም የአማራ ደም አለባቸው፤ በአማራነት የተፈረጁት ዓፄ ኃይለሥላሴም እንዲሁ የአማራ እና የኦሮሞ ዘር፤ እና የክርስቲያንና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ወላጆች ውጤት መሆናቸውም ታሪክ ፀሃፊዎች ዘግበውታል።

በ1960ዎቹ፤ ጽንፈኛ ኃይሎች፤ ኢትዮጵያን ለማዳከም ባቀነባበሩት ሴራ፤ በማኬቬሊያን የከፋፍለህ ግዛ አስተምህሮት፤ “የትግራይ ነፃ አውጭ”፤ “የኦሮም ነፃ አውጭ”፤ “የኦጋዴን ነፃ አውጭ” ወዘተ በሚል ስያሜ ኢትዮጵያውያንን በማደራጀት እና፤ ከሶማሌው አምባገነን መሪ የተንኮል “ገጽ” የተዋሷትን “የአማራ ገዥ” የሚለውን እኩይ የፖለቲካ መስመር በማራመድ፤ የኢትዮጵያን አንድነት ገዘገዙ። ላለፉት 27 ዓመታትም ሃገራችን በዚህ የጽንፈኞች ፖለቲካ ስታትመስ ቆየች። ሃገሪቱን የተቆጣጠረው ገዥ ፓርቲ የተከተለውን አደገኛ የፖለቲካ መስመር፤ የሚሞግተውን፤ የሰብዓዊ መብት አክብር የሚለውን፤ የሚያወግዘውን እና እኩይ ዓላማውን የሚጋፈጠውን ሁሉ፤ ፊውዳሊስት፤ ደርጊስት፤ ወዘተ በሚል ስያሜ ዝም ለማሰኘት፤ የዜጎችን መብት በማፈን በሚወስደው አሰቃቂ የአፈና እርምጃ፤ የግፍ ጽዋው በመፍሰሱ፤ ከየአቅጣጫው የብሶት ማእበል እየገሰገሰ መጣ። ይህ ብሶት፤ ለሃገር ተቆርቋሪ የሆኑ ዜጎችን፤ ከየቦታው ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ሲያደርግ፤ አጋጣሚውን ተጠቅመን፤ እኩይ ዓላማችንን ተግባራዊ እናደርጋለን የሚሉ ጽንፈኞችንም አነሳሳ። እዚህ ግባ የሚባል እውቀትም ሆነ ራዕይ የሌላቸው ሰዎች፤ በአገኙት የታሪክ አጋጣሚ ማይክሮፎን በመጨበጥ እና፤ ቴክኖሎጂ የፈጠረው የማህበራዊ ሚድያ፤ የራሳቸው “የሚድያ ባለቤት” ስላደረጋቸው፤ ፍፁም ጽንፈኛ የሆነና፤ መርዛም የሆነውን በታኝ የፖለቲካ አጀንዳቸውን በማራመድ “የአቤቱታ ፖለቲካውን ፈረስ” እንደፈለጉት መጋለብ ጀመሩ። በዚህ ግርግር መሃከል ነው፤ የኦሮሞ ሕዝብን ብሶት ተጠቅመን ኦሮምያ የሚባል ሃገር እንፈጥራለን በሚል ቅዠት፤ “I am an Oromo First” “መጀመርያ ኦሮሞ ነኝ” የሚለውን ጽንፈኛ አመለካከታቸውን መዘው ወደ መድረክ ብቅ ያሉት። ዓላማቸውም፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማኮሰስ እና፤ ኦሮሞነትን ለማግነን ነው። ይህንን ተከትሎም፤ “Oromo First” “ኦሮሞ ይቅደም” በሚል መፈክር፤ በአእምሮና በእድሜ ያልበሰለው ወጣት፤ ብሶቱን በማራገብ ሃሳባቸውን እንዲገዛ አደረጉ። ይህም የልብ ልብ ሰጥቷቸው፤ ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ አገር፤ ጓሯቸው የበቀለ አረም ይመስል፤ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ሲሉ ዛቱ። ኢትዮጵያን በጉልበት እየገዛ፤ ዜጎችን በማሰር፤ በመግደል እና በማሳደድ የተካነው መንግስትም፤ በሚሰራው ግፍ፤ ለእነዚህ አክራሪ ሃይሎች፤ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ተከታይ እንዲያፈሩ መንገድ ከፈተ። “ኦሮሞ ይቅደም” የሚለው መሪ ሃሳብ ምን ማለት እንደሆነ ያልገባው ሁሉ፤ ኦሮሞ ይቅደም የሚለውን መፈክር ማራገብ ጀመረ። ይህም ለጽንፈኞቹ አቅም የፈጠረላቸው መሰላቸው። ለ27 አመታት በተደረገ ከፍተኛ ትግል እና በተከፈለ መስዋዕትነትም ገዥው ፓርቲ ተገዝግዞ፤ የለውጥ ኃይሎች ከውስጡ ብቅ ብለው ሃገሪቱን አቅጣጫ ማስያዝ ሲጀምሩ፤ ጽንፈኞቹ የለውጡ መሪዎች እና አሸናፊዎች እኛ በማለት ማጓራት ጀመሩ። ደርግ፤ የሕዝቡን ድል እንደነጠቀ፤ ወያኔ ለ17 ዓመታት ሕዝቡ ያደረግውን ትግል እና መስዋዕትነት ገፍትሮና ክዶ፤ “ደርግን የጣልኩት እኔ ነኝ” ሥልጣንም የሚገባኝ እኔ ነኝ እያለ 27 ዓመታት እንደገዛ፤ ታሪክ እርሷን ልትደግም ቀና አለች። የኦሮሞ ይቅደም “ፈላስፎችም”፤ የታገልነውም ያሸነፍነውም እኛ ብቻ ነን፤ እኛ ሃገሪቱን መግዛት አለብን፤ እኛ ካልገዛን ኦሮምያን እንገነጥላለን፤ እያሉ ያናፉብን ጀመር። የብሔራው አጀንዳ ቀርጸው በሃሳብ መሞገት እንደማይችሉ ስለሚያውቁም፤ በታሪክ አጋጣሚ፤ በብሄራዊ መድረክ ላይ ያገኙትን “ዝናና ክብር” በመጠቀም፤ ባዶነታቸው ሳይጋለጥ፤ የጥላቻ መርዛቸውን በሚቆጣጠሩት ሚድያ በመርጨት የማተራመስ ስራቸውን ተያይዙት። ትላንት፤ በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ ከጽንፈኛ ኃይሎች ጋር ይደረግ የነበረው ትግል፤ ዛሬ መሃል መዲናችን ገብቶ፤ የንፁሃንን ሕይወት ቀጠፈ፤ ንብረትም አወደመ። ያ አልበቃ ብሏቸው፤ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር ለማጋጨት፤ ያልተገደለውን ሰው ተገደለ በማለት፤ የሃሰት ፎቶ እየለጠፉ አጥፊ ዘመቻቸውን ቀጥለዋል።

ለመሆኑ የ “Oromo First” (“ኦሮሞ ይቅደም) ጽንሰ ሃሳቡ ምንድነው? ይህ ጽንሰ ሃሳብ ከየት መጣ ጥቅሙና ጉዳቱስ ምንድነው? የሚለውን ማየት ለሁላችንም ይበጃል። ይህ እኩይ አመለካከት “America First” (አሜሪካ ትቅደም) እና “Ethiopia First” (ኢትዮጵያ ትቅደም) ከሚሉት ሃሳቦች ጋር በቅርፁ ይለያይ እንጂ በይዘቱ አንድ ነው። የኢትዮጵያ ወታደራዊ መንግሥት “ኢትዮጵያ ትቅደም” የሚለውን መርህ፤ የዜጎችን መብት ለማፈን፤ ያለሕግ ለማሰር እና ለመግደል፤ ጠላት ብሎ የፈረጃቸውን ለማሳደድ ተጠቅሞበታል። በኢትዮጵያ ትቅደም መርህ፤ 17 ዓመታት ሃገሪቱን ረግጦ የገዛው ሥርዓት፤ ኢትዮጵያን ያስቀደመ ሳይሆን፤ ለዓመታት ወደ ኋላ የጎተተ፤ ሃገሪቱን የጦርነት አውድማ ያደረገ፤ እና ሕዝቧን ለስቃይ የዳረገ፤ በሃገሪቱ ታሪክ ትልቅ ጥቁር ነጥብ የተወ ነው። ደርግ፤ “በኢትዮጵያ ትቅደም” ሰም ነግዶ፤ ሕዝብ አሰቃየ እንጂ፤ ሕዝብን ወደፊት አላራመደም። “ኦሮሞ ይቅደም” የሚለው መርህ ስር እየሰደደ ከሄደ የሃገራችን እጣ ፋንታ ከዚህ የተለየ አይሆንም።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ሥልጣን በተረከቡበት እለት፤ አሜሪካን ትቅደም የሚል መርህ እንደሚጠቀሙ ሲገልጹ፤ ይህ ከዚህ ቀደም አሜሪካኖች የሚያውቁት መርህ፤ የመርሁን አደገኛነት የሚያስታውስ ትዝታቸውን ቀሰቀሷል። በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ፤ አሜሪካ ትቅደም የሚለውን መርህ ያቀነቅኑ የነበሩት፤ በአሜሪካው የሪፓብሊካን ፓርቲ ውስጥ የነበሩ ጥቂት ጽንፈኞች እንደነበሩ እና፤ በወቅቱ፤ ይህ መርህ በብሔራዊ መድረክ ላይ ቦታ እንዳላገኘ፤ ሳራ ቸርችዌል የተባሉ የታሪክ ምሁር “Behold, America” በተሰኘው መጽሐፋቸው ይነግሩናል። ይህ ጽንፈኛ መርህ ግን አፈር ልሶ በአሜሪካ ብሔራዊ መድረክ ላይ በ1915 (እአአ) እንደተነሳ በዚሁ መጽሐፋቸው አስፍረውታል። በ1915 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዊድሮ ዊልሰን ባደረጉት ንግግር፤ የአሜሪካንን ትቅደም መርህ በመጠቀም፤ አሜሪካ አንደኛው ዓለም ጦርነት ውስጥ እንደማትገባ ገልፀው ነበር። በ1916 በተደረግው የአሜሪካን የፕሬዝዳንት ምርጫ ውድድርም “አሜሪካ ትቅደም” የዊልሰን እና የተቀናቃኛቸው መፈክር ሆኖ እንዳገለገለ ሳራ ቸርችዌል ነግረውናል። ምንም እንኳን ዊልሰን፤ አሜሪካ ትቅደም የሚለውን መርህ የተጠቀሙት፤ አሜሪካ በሌሎች ሃገራት ጉዳይ ጣልቃ እንደማትገባ ለማሳወቅ ቢሆንም። ይህ መርህ በጽንፈኞች ተጠልፎ፤ KKK ለተባለው የነጭ ዘረኞች ዳግማዊ ትንሣኤ መነሻ መፈክር ሆኗል። በዛን ወቅት አሜሪካኖች፤ “አሜሪካ ትቅደም” የሚለውን መርህ ከፋሽዝም ጋር ያመሳስሉት እንደነበርም ታሪክ ፀሃፊዋ ያስተምሩናል።

አሜሪካ ትቅደም የሚለው መርህም ይሁን ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለው መርህ ለሃገርና ለሕዝብ ያልበጀ እኩይ መርህ በመሆኑ፤ እስከ 2010 (እአአ) ተቀብሮ ቢቆይም፤ በ2010 ኦሮሞ ይቅደም በሚል ተተክቶ፤ እንዲሁም በ2017 በዶናልድ ትራምፕ፤ አሜሪካ ትቅደም የሚለው መርህ አፍር ልሶ እንደገና ተነስቷል። ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ትቅደም በሚል መርህ፤ በአሜሪካን የሃገር ውስጥ እና የውጭ ሃገር ፖሊሲ የፈጠረው ቀውስ፤ እንዲሁም ተቀብሮ የነበረውን የነጭ ዘረኞች ስሜት ምን ያክል እንዳበረታታ እና፤ እየፈጠረ ያለውን የአግላይነት አንድምታ በገሃድ እያየን ነው። በብዙ ነገር ኩረጃ የሚታሙት፤ አሜሪካን ትቅደም የሚለውንም የኮረጁት፤ የኦሮሞ ይቅደም መርህ አቀንቃኞች አላማ ከዚህ የተለየ አይደለም።

የኦሮሞ ይቅደም መርህ ከአሜሪካው ለየት የሚለው፤ የአሜሪካው መርህ፤ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በመረጣቸው የሃገሪቱ መሪ የሚቀነቀን መሆኑ ነው። ይህም ሆኖ ግን፤ ይህ አደገኛ መርህ፤ ከአብዛኛው ሕዝብ እና ከበርካታ የዓለም መንግሥታት ተቃውሞ ገጥሞታል። የኦሮሞ ይቅደም መርህ አራማጆች፤ እራሳቸውን በመሪነት የሾሙ፤ ማንም ያልመረጣቸው፤ እንኳን የኦሮሞን ሕዝብ ወክለው ይቅርና፤ የራሳቸውን ቤተስብ እንኳን ወክለው ለመናገር ሥልጣን የሌላቸው ናቸው። ሆኖም፤ የታሪክ አጋጣሚ በከፈተው “የመሪ” ክፍተት፤ የሕዝቡን ትግል፤ በጠለፋ የወሰዱ እና “በአቤቱታ ፖለቲካ” የታጀቡ፤ በሚቆጣጠሩት ሚድያ ጽንፈኝነትን እና ጥላቻን ከማራገብ በስተቀር፤ ለኦሮሞ ሕዝብ ጠብ የሚል ነገር ያልሰሩ ናቸው። እነዚህ ኃይሎች፤ የኦሮሞ ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመሆን፤ ለሃገሩ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሎ ሃገሩን ኢትዮጵያን ለመገንባት ያብረከተውን አስተዋጽኦ፤ እነሱ በፈጠሩት ልብ-ወለድ ታሪክ ተክተው፤ ታሪኩን ያጎደፉ እና፤ ጥረታቸው ሁሉ “ኦሮምያን ለመገንጠል” ነው። እነዚህ ኃይሎች፤ የገንዘብ ሃይል ከየት እንዳገኙ፤ ወይም የውጭ ሃይል ከጀርባቸው ለመኖሩ መረጃ ስለሌለኝ እዛ ውስጥ አልገባም። ግን በርግጠኝነት ለመናገር የምችለው፤ እነዚህ ሰዎች፤ ሃሳብን በሃሳብ ማሸነፍ፤ እንዲሁም ጠቃሚ ፖሊሲ በመንደፍ በብሔራዊ መድረክ ላይ ሊሟገቱበትም ሆነ የሕዝብን ልብ ሊያሸንፉ የሚችሉበት አጀንዳ መቅረጽ እንደማይችሉ ነው።

ይህንንም በተግባር እያይነ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ በሃሳብ “ተሟግታችሁ አሽንፉ” እያለ የሚማፀን መሪ ባገኘችበት ጊዜ እና፤ ሃሳብ የማፍለቅ ነፃነት፤ ከሌላው ጊዜ በተለየ በተከበረበት ጊዜ፤ የኦሮሞ ይቅደም ፈላስፎች፤ በስራ እጦት እና በሌሎች ማህበራዊ ቀውሶች ወከባ ላይ ያለውን ወጣት፤ በትምህርት የሚጎልብትበትን አቅጣጫ ከመጠቆም፤ የእጅ ሙያ እንዲማር እድል የሚያገኝበትን፤ የራሱን ንግድ ጀምሮ ኑሮውን ሊያሻሽል የሚችልበትን፤ ሥራ ሊፈጥር እና ኑሮውን ሊያሻሽል የሚችልበትን መንገድ ከመጠቆም ይልቅ፤ የተቆጣጠሩትን ሚድያ የሚጠቀሙብት፤ የሌለ ብሶት እየፈጠሩና ያለውን ብሶት እያጋነኑ፤ ያንኑ የለመዱትን የአቤቱታ ፖለቲካ በማራገብ፤ ወጣቱ የእነሱ አምላኪ እንዲሆን በየቦታው ግጭት ለመቆስቆስ ነው። ኦሮሞ ይቅደም የሚለው መርህ አግላይ፤ ጽንፈኛ እና ዘረኝነትን እና አድልዎን የሚያንሰራፋ መርህ ነው። ልክ እንደ ኢትዮጵያ ትቅደም፤ ኦሮሞ ይቅደም፤ የሃሳብ ነፃነት አይፈቅድም፤ እነሱ የሚያራግቡትን የሃሰት ታሪክ ያልተቀበለ ሁሉ “ጸረ ኦሮሞ” ተብሎ ይፈረጃል። ጉልበት እያገኙ ከመጡ ደግሞ፤ የሚሞግቷቸውን ለማስቆም አስቃቂ እርምጃ መውሰዳቸው አይቀሬ ነው። ይህን ጽንፈኛ አመለካከት የሚያራምዱ ኃይሎች፤ ማንንም የማዳመጥ ትዕግስት የላቸውም፤ ሁሉንም ነገር እነሱ ብቻ መዘወር የሚችሉ ይመስላቸዋል። የኢትዮጵያዊነት ስሜት በኦሮሞ ሕዝብ ውስጥ “እንዳይሰርጽ” የማድረግ መብት እና ችሎታ ያላቸው ይመስላቸዋል። ብዙሃኑ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊነቱ እና ኦሮሞነቱ እንደማይጋጭበት አልገባቸውም።

የኦሮሞ ሕዝብ፤ እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ፤ ጭቆና አንገሽግሾታል፤ ብሶት አለበት። ጽንፈኛ ኃይሎች ግን፤ ይህን ብሶት ተጠቅመው የኢትዮጵያዊነት ስሜቱን ለመሸርሸር ተግተው ይሰራሉ። ሕዝቡ በሃገሩ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ፤ ይቀሰቅሳሉ፤ አመጽ ያስነሳሉ፤ ያንኑ የፈረደበትን ንጉስ ምኒልክ እና የአማራ ሕዝብ እየኮነኑ፤ የአንድነት ኃይል በሚል ስም፤ መብትህን፤ ሊገፉ ነው፤ ነፃነትህን ሊነጥቁህ ነው፤ የሚል ታምቡራቸውን ይመታሉ። ለኢትዮጵያ አንድነት የሚቆሙትን ሁሉ ይኮንናሉ፤ የ18ኛ እና የ19ነኛ ክፍለ ዘመን ገዥዎች፤ “ለምን ዲሞክራት አልነበሩም? ለምን እንደ 21ኛው ክፍለ ዘመን ሰው አላሰቡም?” ብለው ያላዝናሉ። አንድ ሃገር፤ የእድገት ደረጃውን ጠብቆ እንደሚራመድ ጠንቅቆ አልገባቸውም። ክሳቸው እና ከቀደምት ነገስታቶች ጋር ያላቸው ሙግት፤ ለምን በምኒሊክ ጊዜ ተንቀሳቃሽ ስልክ አልነበረም? ለምን በዓፄ ኃይለሥላሴ ጊዜ ኢንተርኔት አልነበረም? የሚል ዓይነት ነው። አርበኛው ኦሮሞው አያቴ፤ ከጣልያን ጋር ለመዋጋት ሲዘምቱ፤ የኢትዮጵያን ክብር እና የግዛት አንድነት ለመከላከል ነበር፤ ለሰብዓዊ መብት ሲሟገት እድሜውን የገፋው ኦሮሞው አባቴ፤ የጮኽው ለመላው ኢትዮጵያዊ ነበር። ዛሬ ዓለም እየሰፋ ባለበት ጊዜ፤ የኦሮሞን ሕዝብ አግላይ ለማድረግ የሚተጉ ሰዎች፤ የሚደክሙት ለኦሮሞ ሕዝብ ነው ብለን ካሰብን በጣም ተሳስተናል። እነዚህ ሰዎች፤ በሺህ የሚቆጠር ኦሮሞ ከሶማሊያ ክልል ሲፈናቀል፤ ምንም ዓይነት እርዳታ እንዳላደረጉ በርግጠኝነት መናገር እችላለሁ። ይልቁንም፤ ቁስሉን፤ ስቃዩን፤ ለፖለቲካ ትርፍ ተጠቀሙበት እንጂ።

ኢትዮጵያ ባለችበት በዚህ የሽግግር ወቅት፤ ‘አላማችንን ለማሳካት እድል አግኝተናል’ ብለው የሚያስቡ ጽንፈኛ ኃይሎች ቆም ብለው ማሰብ አለባቸው። የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር የተባለው ድርጅት፤ ኦሮምያን ከተቀረው ኢትዮጵያ እገነጥላለሁ በሚል ቅዠት ከ40 ዓመታት በላይ ዳክሯል፤ ግን አልተሳካለትም። ኦነግ ያልተሳካለት፤ አብዛኛው የኦሮሞ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሀገሩ ተገንጠል መባሉ ስላልተዋጠለት ነው። ኦነግ ያቃተውን የመገንጠል አባዜ፤ ነጋ ጠባ የራሳቸውን ድምጽ በመስማት በሚመረቅኑና፤ በአማርኛ ስለአንድነት እያወሩ፤ በኦሮምኛ ጥላቻን በሚሰብኩ፤ እንጭጭ ፖለቲከኞች፤ የኦሮሞ ሕዝብ እነሱ እንደፈለጋቸው የሚቆጣጠሩት ይመስል፤ “ብፈልግ ኦሮምያን እገነጥል ነበር፤ ማን ይከለክለኝ ነበር” የሚል፤ አዙሮ ማየት የማይችል ጨቅላ አእምሮ ያላቸው ትዕቢተኞች፤ ያሳካሉ ብሎ ማሰብ አይቻልም። እነዚህ ጽንፈኞች ግን የጥላቻ መርዛቸውን ዘልቀው ከመትከላቸው በፊት፤ ልጓም ሊበጅላቸው እና በግልጽም ሊጋለጡና ሊሞገቱ ይገባል። እንደ ኢትዮጵያ ትቅደም፤ ኦሮሞ ይቅደምም፤ ለሃገርና ለሕዝብ የሚያተርፈው፤ ሃገራችንን የጦርነት አውድማ ማድረግ እና የሕዝቡን ስቃይ ማርዘም ብቻ ነው። እነዚህ ጽንፈኛ ሃይሎች፤ እንኳን የኦሮሞን ሕዝብ አስተባብረው ለኦሮሞ ሕዝብ ጥቅም ሊሰሩ ይቅርና፤ ለኦሮሞ ሕዝብ እንታገላለን ብለው እንደ አሸን የፈሉትን ወደ ሰባት የሚሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ማግባባት አልቻሉም። እነዚህ ኃይሎች፤ በአንድ ላይ መቆም ያልቻሉት፤ ከኦሮሞ ሕዝብ ጥቅም እና ከሃገር ጥቅም ይልቅ፤ በራሳቸው የግል ጥቅም የተቃቃሩ በመሆናቸው ነው። ስለዚህ፤ መላው ኢትዮጵያዊ፤ “ኦሮሞ ይቅደም” የሚለውን የወደቀና የከሸፈ፤ እንዲሁም አፍራሽ አስተሳሰብ፤ ሊሞግተው እና ባዶነቱንም ማጋለጥ ይኖርበታል።

​ኢትዮጲያዊነትን መገንባትና ማፍረስ: ከአፄ ሚኒሊክ እስከ መለስ! – (ስዩም ተሾመ)

የኢህአዴግ መንግስት ትላንት ነሃሴ 26/2009 ዓ.ም “የፍቅር ቀን” ብሎ አስደመመን። በቀጣይ ቀናት ደግሞ “የአገር ፍቅር ቀን”፣ “የአንድነት ቀን” እና “የኢትዮጲያ ቀን” እያለ ሊያስገርመን ተዘጋጅቷል። “የአንድነት ቀን” የሚከበርበት መሪ ቃል “ኢትዮጵያዊ ኩራቱ ህብረ-ብሄራዊነቱ” የሚል ነው። “የሀገር ፍቅር ቀን” መሪ ቃል “እጃችን እስኪሻክር እንሰራለን ምክነያቱም ኢትዮጵያን እንወዳታለን” የሚል ሲሆን “የኢትዮጲያ ቀን” ደግሞ “እኛ ኢትዮጵያውያን የጥቁር ህዝቦች ተምሳሌት ነን” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ተገልጿል። በእርግጥ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የዘመን መለወጫን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ኢትዮጲያዊነትን፣ አንድነትንና የሀገር ፍቅርን ለማስረፅ ጥረት ማድረጉ እንደ በጎ ጅምር ሊወሰድ ይችላል። በፅንሰ-ሃሳብ ደረጃ ሲታይ ግን የኢህአዴግ መንግስትን ከፋፋይነት እና ፀረ-ኢትዮጲያዊነት በግልፅ የሚያሳይ ነው።

ከለይ ለተጠቀሱት እያንዳንዱ ቀን የተሰጠው መሪ ቃል፣ እንዲሁም በመርሃ ግብሩ የተዘረዘሩት ተግባራት አንድነትን፣ የሀገር ፍቅርን እና ኢትዮጲያዊነትን አያንፀባርቁም። ለምሳሌ፣ በመርሃ ግብሩ መሰረት፣ ሀገራዊ አንድነትን ለማንፀባረቅ ከሚከናወኑ ተግባራት ውስጥ “ትምህርት ቤቶችን እና የስራ ቦታዎችን በጋራ ማጽዳትና ማደራጀት፣ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን በአብሮነት ስሜት በጋር ማከናወን፣ እንዲሁም በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ታራሚዎችን መጎብኘት” የሚሉት ተጠቅሰዋል። በተቀሩት ሁለት ቀናት የሚከናወኑት ዝርዝር ተግባራት ደግሞ ከመሪ ቃሉ የባሰ አስቂኝና የተሳሳቱ ናቸው። በአጠቃላይ፣ “የአንድነት ቀን”፣ “የሀገር ፍቅር” እና “የኢትዮጲያ ቀን” በሚል የተዘጋጀው መርሃ ግብር የኢህአዴግ መንግስት የሚከተለውን የተሳሳተ የፖለቲካ አቅጣጫ በተጨማሪ በስልጣን ላይ ያለው ቡድን ያለበትን ስር የሰደደ የዕውቀት እጥረት (knowledge deficiency) በግልፅ ያሳያል። ለምን እና እንዴት የሚለውን ከዚህ ቀጥሎ በዝርዝር እንመለከታለን።

የሰው ልጅ አስተሳሰብ በወደፊቱ ግዜ ላይ የተመሰረተ ነው። ትላንትን የሚያስተወሰው የነገ ሕይወቱን ለማስተካከል ወይም ለማሻሻል ነው። ዛሬ ላይ የሚፈፅመው ተግባር ነገን ታሳቢ ያደረገ ነው። ምክንያቱም፣ ሰው የሚኖረው በወደፊት እና ለወደፊት ነው። “የሰው ልጅ የሚኖረው በተስፋ ነው” ወይም ደግሞ “Human being lives primarily in the future and for the future” የሚለው አባባል ይህን የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ይገልፃሉ። ስለዚህ፣ ከወደፊት ሕይወቱ የተነጠለ ወይም ተያያዥነት የሌለው ነገር ለሰው ልጅ ስሜት አይሰጥም። በዚህ መሰረት፣ ሀገራዊ አንድነት፥ ፍቅርና ዜግነት ትርጉም የሚኖራቸው በዜጎች የወደፊት ሕይወት ውስጥ ፋይዳ ሲኖራቸው ነው። በወደፊት ሕይወታችን ውስጥ ፋይዳ ከሌላቸው ግን ዛሬ ላይ ዋጋ አንሰጣቸውም። በቀጣይ ቀናት የሚከበሩት የአንድነት፣ የሀገር ፍቅር እና የኢትዮጲያ ቀናት ከዚህ አንፃር መታየት አለባቸው።

ብዙዎቻችሁ እንደምትታዘቡት እገምታለሁ፣ በተለይ ባለፉት አስርና አስራ አምስት አመታት የኢህአዴግ መንግስት ስለ “አንድነት፣ የሀገር ፍቅር ወይም ኢትዮጲያዊነት” ምንም ቢናገር፥ ቢያደርግ በብዙሃኑ ዘንድ ተዓማኒነት የለውም። የኢህአዴግ መንግስት ስለ ብሔሮች መብትና እኩልነት እንጂ ስለ ሀገራዊ አንድነት፣ ፍቅርና ዜግነት ቢናገር፥ ቢከራከር ተቃዋሚዎች ቀርቶ የራሱ ደጋፊዎች እንኳን በሙሉ ልብ አምነው አይቀበሉትም። ምክንያቱም፣ የኢህአዴግ መንግስት የፖለቲካ መርህና አመለካከት ሙሉ በሙሉ በትላንትና ዛሬ እሳቤ ላይ የተመሰረተ ነው። ከሕገ-መንግስቱ ጀምሮ የሀገሪቱ ፖለቲካዊ መርሆችና ፖሊሲዎች በሙሉ ከቀድሞ ስርዓት ላይ ተነስተው የአሁኑ ስርዓት ላይ የሚቆሙ ናቸው። ከወደፊቱ ሕይወት ጋር ትስስር የላቸውም። ሃሳቡን ግልፅ ለማድረግ ከሀገር አመሰራረትና አንድነት አንፃር መመልከት ይኖርብናል።

በቀጣይ ሳምንት ከሚከበሩት አንዱ “የአንድነት ቀን” ሲሆን “ኢትዮጵያዊ ኩራቱ ህብረ-ብሄራዊነቱ” የሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ከላይ ተገልጿል። ነገር ግን፣ የኢህአዴግ መንግስት ሀገራዊ አንድነትን “ከህብረ-ብሔራዊነት ወይም ብዙሃንነት” አንፃር የሚገልፅበት ምክንያት ምንድነው? “ኢትዮጵያዊ ኩራቱ ህብረ-ብሄራዊነቱ” የሚለው መሪ ቃልስ ከአንድነት ፅንሰ-ሃሳብ ጋር አብሮ ይሄዳል? በእርግጥ የኢህአዴግ መንግስት ሀገራዊ አንድነትን ከህብረ-ብሔራዊነት ጋር አንፃር የሚገልፅበት ዋና ምክንያት ራሱን ከቀድሞ አህዳዊ ስርዓቶች ለመለየት ነው።

የኢህአዴግ መንግስት በተለይ በአፄ ሚኒሊክ ዘመን የተመሰረተችው የአሁኗ ኢትዮጲያ በአንድ ዓይነት ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህል፥ ሃይማኖት፥… እንደሆነ ይገልፃል። በዚህ መሰረት፣ በቀድሞ ስርዓት “አንድነት” ማለት አማርኛ ቋንቋ፣ የአማራ ባህልና ሃይማኖት፣ እንዲሁም የአማራ የበላይነት የተረጋገጠበት አስተዳደራዊ ስርዓት እንደነበር ይገልፃል። በሕወሃት መሪነት የተጀመረው የትጥቅ ትግልም ይህን አህዳዊ ስርዓት በማስወገድ የብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች መብትና እኩልነት የተረጋገጠበት ፖለቲካዊ ስርዓት ለመዘርጋት ዓላማ ያደረገ ነበር። የደርግን ስርዓት በማስወገድ የተዘረጋው በብሔር ላይ የተመሰረተ ፌዴራላዊ ስርዓት የዚህ ውጤት ነው። በመሆኑም፣ የኢህአዴግ መንግስት ሀገራዊ አንድነትን ከሕብረ-ብሔራዊነት ነጥሎ ማየት አይችልም። ሕብረ-ብሔራዊነትን ከቀድሞ ታሪክ፣ ከአሁኑና ከወደፊቱ ፖለቲካ አንፃር እንመልከት።

የኢትዮጲያ አመሰራረትና አንድነት

የኢህአዴግ መንግስት በተደጋጋሚ ኢትዮጲያ እንደ ሀገር መቀጠል የቻለችው በሕብረ-ብሔራዊነቷ፥ በብሔር ልዩነት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ስርዓት መዘርጋት በመቻሏ እንደሆነ ይገልፃል። እንደ ኢህአዴግ መንግስት አገላለፅ፣ በቀድሞ ስርዓት የነበረው የኢትዮጲያ አንድነት በአንድ ዓይነት ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህል፥ ሃይማኖት፣ እንዲሁም በአንድ ብሔር የበላይነት ላይ የተመሰረተ ከነበረ፣ ሀገሪቱ የኢህአዴግ መንግስት ወደ ስልጣን እስከመጣበት 1983 ዓ.ም እንደ ሀገር መቀጠል አትችልም ነበር። አፄ ሚኒሊክ የአሁኗን ኢትዮጲያ ከመመስረታቸው በፊት ሆነ በኋላ በአንድ አይነት ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ባህልና ሃይማኖት ሀገር ለመመስረት የተደረገው ሙከራ በተደጋጋሚ ውድቅ ሆኗል። በአጠቃላይ፣ በፍፁም አህዳዊ እሳቤ ሀገራዊ አንድነትን ማረጋገጥ አይቻልም።

“Jose Ortega y Gassett” የተባለው ፀኃፊ “THE REVOLT OF THE MASSES” በሚለው መፅሃፉ ስፔን በመካከለኛውና ደቡብ አሜሪካ ያጋጠማትን እንደ ማሳያ ይጠቅሳል። ከዚህ በተጨማሪ፣ እንደ እንግሊዝና ፈረንሳይ ያሉ ሀገራት በቅኝ-ግዛቶቻቸው በአንድ ዓይነት ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህልና ሃይማኖት ላይ የተመሰረተ አንድነት ለመፍጠር የሚያደርጉት ሙከራ እንደማይሳካ መፅሃፉ በወጣበት እ.አ.አ. 1929 ዓ.ም ላይ ሆኖ በግልፅ ጠቁሟል። በተለይ ስፔን በመካከለኛውና ደቡብ አሜሪካ በነበሯት ቅኝ-ግዛቶች የጋራ ታሪክ፥ የጋራ ቋንቋና ዘር እንደነበራት ይገልፃል። ሆኖም ግን ሀገራዊ አንድነት ሊኖራት እንዳልቻለ እንዲህ ሲል ገልፆታል፡-

“With the peoples of Central and South America, Spain has a past in common, common language, common race; and yet it does not form with them one nation. Why not? There is one thing lacking which, we know, is the essential: a common future.” The Revolt of the Masses, Ch. XIV: Who Rules the World?, Page 105.

ከላይ በተገለፀው መሰረት፣ ስፔን በደቡብና መካከለኛው አሜሪካ በአንድ አይነት ታሪክ፥ ቋንቋና ዘር ላይ የተመሰረተ ሀገራዊ አንድነት ለመፍጠር ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። እንደ ፈረንሳይ ያሉ ቅኝ-ገዢ ሀገራት የራሳቸውን ቋንቋ፥ ባህል፥ ስነ-ልቦና፥ የትምህርት ስርዓት እና ሌሎች ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ስርዓቶችን በአፍሪካና ኢሲያ ሀገራት ላይ በመጫን አህዳዊ አንድነት እንዲኖር ያልተሳካ ሙከራ አድርገዋል። አንዳንድ አክራሪ ብሔርተኞች የአፄ ሚኒሊክን መስፋፋት ከቅኝ-ግዛት ጋር ያያይዙታል። ሕወሃት/ኢህአዴግ ደግሞ የኢምፔሪያሊዝም መስፋፋት እንደሆነ ይገልፃል። ሁለቱም ወገኖች ግን ከአፄ ሚኒሊክ ጀምሮ እስከ ኢህአዴግ መንግስት ድረስ በአንድ ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህልና ሃይማኖት ላይ የተመሰረተ አንድነት እንደነበረ ይገልፃሉ። የስፔንና ፈረንሳይ ተሞክሮ የሚያሳየው ግን በዚህ ላይ የተመሰረተ አንድነት ቀጣይነት እንደሌለው ነው።

የአሁኗ ኢትዮጲያ ግን መመስረት ከተመሰረተችበት ግዜ አንስቶ የኢህአዴግ መንግስት እስከ መጣበት ድረስ አንድ መቶ አመት ያህል አንድነቷን አስጠብቃ ቆይታለች። ከዚህ በተጨማሪ፣ ገና በምስረታ ሂደት ላይ እያለች የኢጣሊያን የተቃጣባትን የቅኝ-ግዛት ወረራ መመከት ችላለች። በወቅቱ የኢትዮጲያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች የወደፊት አብሮነት “common future” ካልነበራቸው የኢጣሊያን ወራሪ ጦር በጋራ ተረባርበው አይመክቱም ነበር። እንደ ሀገር አብሮ ለመቀጠል፥ የጋራ ዓላማና ግብ ከሌላቸው የተለያዩ ብሔር ተወላጆች አደዋ ላይ ከኢጣሊያን ጋር የሚዋጉበት ምክንያት የለም።

የኢትዮጲያ ብሔሮች አድዋ ላይ የተዋደቁት የጋራ ዓላማ፣ የወደፊት አብሮነት ስላላቸው እንጂ በቋንቋ፣ ታሪክ፣ ባህል ወይም ሃይማኖት አንድ አልነበረሩም። በተቃራኒው፣ ኢጣሊያ ኢትዮጲያን የወረረችበት ዓላማ በአንድ አይነት ቋንቋ፣ ታሪክ፣ ሃይማኖት እና ግዛት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ስርዓት ለመዘርጋት ነበር። ይህን “Raymond Jonas” የተባለው የታሪክ ምሁር እንደሚከተለው ገልፆታል፡-

“If any quality typifies Italian colonial efforts it would not be jingoism but apathy. The Italian statesman Marquis d’Azeglio, after Italian unification, commented that “We have made Italy. Now we must make Italians.” Italy was divided along religious, political, and regional lines. It was hoped by some, such as Prime Minister Crispi, that imperialism would improve the standing of the Italian government within the nation and across Europe.” When Ethiopia Stunned the World: Cambridge, Massachusetts: Belknap Press, 2011

ኢትዮጲያ ከአደዋ ጦርነት በኋላም አንድነቷን የሚፈታተኑ ታሪካዊ ክስተቶች አጋጥመዋታል። ከእነዚህ ውስጥ የአምስት አመቱ የፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ እና የደርግ ወታደራዊ ፋሽስት አስተዳደር በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። በአጠቃላይ፣ ከኢህአዴግ መንግስት መምጣት በፊት አንድነቷን ሊያፈርሱ የሚችሉ ብዙ አስቸጋሪ ወቅቶችን አልፋለች። አፄ ሚኒሊክ የአሁኗን ኢትዮጲያ ለመመስረት ወደ ደቡብ፥ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫዎች ካደረጉት መስፋፋት ጋር ተያይዞ ብዙ ችግሮች ሊነሱ ይችላል። ሆኖም ግን፣ እንደ ስፔን፥ ፈረንሳይና ኢጣሊያ ካሉ የቅኝ-ግዛት ኃይሎች በተለየ፣ የአፄ ሚኒሊክ መስፋፋትና የዘረጉት የፖለቲካ አስተዳደራዊ ስርዓት ሕብረ-ብሔራዊ ነበረ።

ኢትዮጲያ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ አንድነቷን አስጠብቃ መቀጠል የቻለችበት ዋና ምክንያት ይሄ ነው። የአፄ ሚኒሊክ መስፋፋት ዋና ዓላማ እንደ አውሮፓዊያኑ የነባር ጎሳዎችን፥ ብሔሮችን ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህልና ሃይማኖት በአህዳዊ አንድነት ለማጥፋት ሳይሆን ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት ለመመስረት እንደነበረ በወቅቱ ዓይን እማኝ የነበረው ሩሲያዊው ፀኃፊ “Alexander Bulatovich” እንደሚከተለው ገልፆታል፡-

“These are the motives which led Menelik to aggressive acts; and we Russians cannot help sympathizing with his intentions, not only because of political considerations, but also for purely human reasons. It is well known to what consequences conquests of wild tribes by Europeans lead. Too great a difference in the degree of culture between the conquered people and their conquerors has always led to the enslavement, corruption, and degeneration of the weaker race. The natives of America degenerated and have almost ceased to exist. The natives of India were corrupted and deprived of individuality. The black tribes of Africa became the slaves of the whites.” With the Armies of Menelik II, trans. Richard Seltzer, Journal of an expedition from Ethiopia to Lake Rudolf, an eye-witness account of the end of an era.

ከላይ እንደተመለከትነው፣ ኢትዮጲያ ከአመሰራረቷ ጀምሮ ሕብረ-ብሔራዊ እንደነበረች ተመልክተናል። ለዚህ ደግሞ ሀገሪቷ አንድነቷን ጠብቃ ለአንድ ክፍለ ዘመን መቀጠል መቻሏ፣ አህዳዊ ስርዓት ለመዘርጋት በሚሞክሩ ቅኝ-ገዢዎች የተቃጣባትን ወረራ በጋራ መመከቷ መቻሏ፣ እንዲሁም እንደ “Alexander Bulatovich” አገላለፅ፣ የኢትዮጲያ ነባር ጎሳዎች፥ ብሔሮች ወይም ሕዝቦች ልክ እንደ አሜሪካ ነባር ሕዝቦች (ቀይ ሕንዶች) የመኖር ሕልውናቸውን አለማጣታቸው፣ ቋንቋ፥ ባህልና እምነታቸውን እስካሁን ይዘው መቀጠላቸው በማሳያነት መጥቀስ ይቻላል።

የኢትዮጲያ አንድነት እና የኢህአዴግ አመለካከት

የኢህአዴግ መንግስት የዘረጋው ፖለቲካዊ ስርዓት “የቀድሞ ስርዓት አህዳዊ ነበር” በሚል አመለካከት ላይ የተመሰረተ ነው። በዚህ መሰረት፣ የሀገሪቱ አንድነት በአንድ ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህልና ሃይማኖት ላይ የተመሰረተ፣ ወይም የአማራ የበላይነት የተረጋገጠበት ነበረ። የኢትዮጱያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች መብትና እኩልነት ስላልተረጋገጠ ሕብረ-ብሔራዊነት አልነበረም። የኢትዮጲያ አንድነት እና ሕብረ-ብሔራዊነት የተረጋገጠው በኢህአዴግ መንግስት አማካኝነት ነው። ስለዚህ፣ የአንድነት ቀን “ኢትዮጲያዊ ኩራቱ ህብረ-ብሔራዊነቱ” በሚል መሪ ቃል የሚከበርበት ዋና ምክንያት፤ ከአፄ ሚኒሊክ ዘመን ጀምሮ የነበረው ፖለቲካዊ ስርዓት አህዳዊ እንደነበርና ይህም ስርዓት በ1987 ዓ.ም በፀደቀው ሕገ-መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ እንደተወገደ ለማሳየት ነው።

በቀድሞ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ መሪነት የተዘረጋው መንግስታዊ ስርዓት ከአፄ ሚኒሊክ ዘመን ጀምሮ የነበረውን በመሻር ሀገሪቷን በአዲስ መሰረት ላይ እንዳቆማት ሲገልፅ ይስማል። በዚህ መሰረት፣ አንደኛ፡- ትላንት ላይ ሕብረ-ብሄራዊ ስርዓት ስላልነበረ ሀገራዊ አንድነት አልነበረም፣ ሁለተኛ፡- ዛሬ ላይ ሕብረ-ብሄራዊ ስርዓት ስለተዘረጋ ሀገራዊ አንድነት አለ። ነገር ግን፣ ዛሬ ኢትዮጲያ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት እንዲኖራት ትላንት ላይ ሕዝቦቿ የጋራ ታሪክና የወደፊት አብሮነት ሊኖራቸው ይገባል። ትላንት ላይ ሕብረ-ብሔራዊነት ካልነበረን የወደፊት አብሮነት አይኖረንም፤ የወደፊት አብሮነት ካልነበረን ዛሬ ላይ አንድነት ሊኖረን አይችልም። ሃሳቡን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ሃሳቡን በዝርዝር መመልከት ያስፈልጋል።

በመጀመሪያ ደረጃ ከአፄ ሚኒሊክ ዘመን ጀምሮ ሕብረ-ብሔራዊነት ካልነበረ ሀገሪቱ ለአንድ ክፍለ ዘመን ያህል አንድነቷን ጠብቃ መቀጠል አትችልም ነበር። ምክንያቱም፣ አፄ ሚኒሊክ ወደ ደቡብ፥ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫዎች በመዝመት ከፊሉን በአስከፊ ጦርነት የተቀሩትን በሰላማዊ ድርድር የኢትዮጲያ አካል ያደረጓቸው የተለያዩ ጎሳዎች፥ ብሔሮችና ሕዝቦች ከተወሰነ ግዜ በኋላ ራሳቸውን ከአገዛዙ ነፃ ለማውጣት ትግል ይጀምራሉ። በተመሳሳይ ወቅት በአውሮፓ ቅኝ-ገዢዎች ስር የወደቁ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሕዝቦች ከግማሽ ክ/ዘመን በኋላ ራሳቸውን ከአገዛዙ ነፃ ማውጣት ችለዋል። የኢትዮጲያ ብሄሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች ግን የኢትዮጲያ አካል ከሆኑ አስር አመት ሳሞላቸው የኢጣሊያን የቅኝ-ግዛት ወረራ ለመመከት በጋራ ወደ አድዋ ዘምተዋል።

ኢትዮጲያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ልዩ የሚያደርጋት በአደዋ ጦርነት በነጮች ላይ የተቀዳጀችው ድል አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ ከሌሎች አፍሪካዊያን በተለየ በኢትዮጲያ ስር የነበሩት ነባር ግዛቶች፡- ሸዋ፥ ጎንደር፥ ትግራይ፥ ጎጃምና ወሎ በደቡብ፥ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ከነበሩት ሌሎች ብሄሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች በመቀናጀት የቅኝ-ገዢዎችን በጋራ ለመመከት መስማማታቸው ነው። ስለዚህ፣ ኢትዮጲያዊያን በኩራት የሚጠቅሱት የአደዋ ድል የመጨረሻ ውጤት እንጂ መነሻ ምክንያት አይደለም። ከአደዋ ድል እና ከኢትዮጲያ ነፃነት በስተጀርባ ያለው ሚስጥር የኢትዮጲያ ብሄሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች በጋራ በመሆን ራሳቸውን ከቅኝ-ግዛት ወረራ ለመከላከል የፈጠሩት የወደፊት አብሮነት (common future) ነው። ሌሎች አፍሪካዊያን ይህን የወደፊት አብሮነት መፍጠር ስለተሳናቸው ለቅኝ-ግዛት ተዳርገዋል። ኢትዮጲያዊያን ግን ራሳቸውን ከቅኝ-ገዢዎች ወረራ መከላከልን ዓላማ አድርገው የፈጠሩት አብሮነት ለአንድነታቸው መሰረት ሆኗል።

በሌላ በኩል፣ የአፄ ሚኒሊክ አገዛዝ ልክ እንደ ቅኝ-ገዢ ኃይሎች አህዳዊ ፖለቲካዊ ስርዓት የመዘርጋት ዓላማ ከነበረው በተለያዩ ብሄሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች ላይ አንድ ዓይነት ቋንቋ፥ ታሪክ፥ ባህልና ሃይማኖት ይጭኑ ነበር። ይህ ከሆነ ደግሞ በደቡብና መካከለኛው አሜሪካ እንደነበረው የስፔን አገዛዝ፣ እንዲሁም በአፍሪካ ኢሲያ እንደ ነበረው የፈረንሳይ አገዛዝ ለውድቀት ይዳረግ ነበር። አሊያም ደግሞ የሀገሪቱን ብሔሮች፥ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች አንድ ላይ በማቀናጀት የኢጣሊያን ወረራ መመከት ይሳነው ነበር። በመሆኑም፣ በአፄ ሚኒሊክ ዘመን የተዘረጋው አገዛዝ ሕብረ-ብሔራዊነት ካልነበረው፣ እንደ ኢህአዴግ መንግስት አገላለፅ ወይም እንደ ቀኝ-ገዢ ኃይሎች ፍፁም አህዳዊ ስርዓት ከነበረ ከግማሽ ከፍለ ዘመን በፊት በወደቀ፣ ሀገሪቷም አንድነቷን አስጠብቃ ማስቀጠል በተሳናት ነበር። ስለዚህ፣ ኢትዮጲያ እንደ ሀገር መቀጠል የቻለችው በሕብረ-ብሔራዊነት ላይ የተመሰረተ አንድነት ስለነበራት ነው።

የፈረሰ አንድነት

የኢህአዴግ መንግስት “ዛሬ ላይ በሀገራችን የብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች መብትና እኩልነት ተረጋግጧል” የሚለውን እውነት ነው ብለን እንቀበል። በሕገ-መንግስቱ መሰረት፣ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን እና ራስን በራስ የማስተዳደር መብታቸው ተከብሯል። የኢትዮጲያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች በራሳቸው ቋንቋ የመናገር፥ የመማርና የመፃፍ መብት፣ ባህላቸውን መግለጽና ማሳደግ ችለዋል። በመሆኑም፣ ሀገራችን ብዙሃንነት የሚንጸባረቅባት ሕብረ-ብሔራዊ ሆናለች። ይሄ ዛሬ ላይ ያለው፥ የሆነውና እየሆነ ያለ ነገር ነው። ነገ ግን ሌላ ቀን ነው። ዛሬ ላይ ያለው፣ የሆነው ወይም እየሆነ ባለው ነገር ብቻ መኖር አይቻልም።

ትላንት ላይ ሆነን የዛሬውን ህብረ-ብሔራዊነት ስንመኝ፥ ስናስብና ስናቅድ ስለነበር በተግባር እውን ማድረግ ችለናል። ነገር ግን፣ በትላንት ሃሳብ፥ ዕቅድና ምኞት ዛሬን መኖር አንችልም። ምክንያቱም፣ የሰው ልጅ ትላንትን የሚያስታውሰው ሆነ የዛሬ ተግባሩን የሚፈፅመው ነገ ላይ የተሻለ ነገር ለማግኘት ነው። የቀድሞውን የኢትዮጲያን የቀድሞ ታሪክ የምናስታውሰው፣ የዛሬውን ህብረ-ብሔራዊነት የምናወድሰው፣ ነገ ላይ የተሻለ ፖለቲካዊ ስርዓት ለመዘርጋት እንዲያስችለን ነው። ይሁን እንጂ፣ የኢህአዴግ መንግስት ከቀድሞ ስርዓት ስህተት እና ከአሁኑ ስርዓት ፍፁማዊነት ትርክት ባለፈ ለነገ ምን ሰንቋል?

የኢህአዴግ መንግስት የዘረጋው ፖለቲካዊ ስርዓት፤ የኢትዮጲያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች ትላንት ላይ የጋራ ታሪክና አብሮነት ወይም አንድነት አልነበራቸውም፣ ዛሬ ላይ ግን ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት አላቸው፣ ነገ ላይ ደግሞ በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 39(1) መሰረት በማንኛውም መልኩ የማይገደብ የራስ እድልን በራስ የመወሰን እስከ መገንጠል መብት አላቸው። ስለዚህ፣ ትላንት ላይ የጋራ አብሮነት አልነበረንም፣ ዛሬ ላይ በልዩነት አብረን አለን፣ ነገ ላይ መለያየት እንችላለን። በዚህ መሰረት፣ የኢህአዴግ መንግስት አቋምና አመለካከት ስህተት ነው።

አንደኛ፡- ዛሬ ላይ አብረን እንድንሆን ትላንት ላይ አብረን መሆን ነበረብን። ምክንያቱም፣ ትላንት ላይ አብረው ያልነበሩ ወገኖች ዛሬ ላይ ስለ ወደፊት አብሮነት ሆነ መለያየት ለመነጋገር መሰረት የላቸውም። ዛሬ ላይ አብረን እንድንሆን ትላንት ላይ በወደፊት አብሮነት (common future) የተመሰረተ አንድነት ሊኖረን ይገባል። ትላንት ላይ የወደፊት አብሮነት ከነበረን ደግሞ የጋራ አንድነት እንደነበረን መገመት ይቻላል። ስለዚህ፣ የኢህአዴግ መንግስት በህብረ-ብሄራዊነት ላይ የተመሰረተ አንድነት በ1987 ዓ.ም እንደሆነ የሚገልፀው ፍፁም ስህተት ነው።

ሁለተኛ፡- ዛሬ ላይ አንድነት እንዲኖረን የወደፊት አብሮነት ሊኖረን ይገባል። የወደፊት አብሮነት እንዲኖረን ስለ ወደፊቱ ግዜ በጋራ ማሰብ፥ መመኘት፥ ማቀድ፥ መነጋገርና መግባባት አለብን። ይህን ለማድረግ ደግሞ ለወደፊት በአብሮነት ለመኖር መወሰን አለብን። ነገር ግን፣ የትኛውም ብሔር፥ ብሔረሰብ ወይም ሕዝብ መቼና ለምን እንደሆነ ባልታወቀ ምክንያት ከሌሎች የኢትዮጲያ ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች፥ ሕዝቦች ጋር አብሮ መቀጠል ባለመፈለጉ ምክንያት ሊገነጠል ይችላል።

በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 39(1) ላይ በተደነገገው መሰረት፣ ማንኛውም የኢትዮጲያ ብሔር፥ ብሔረሰብ፥ ሕዝብ በማንኛውም መልኩ ያልተገደበ የመገንጠል መብት አለው። በድንጋጌው መስረት፣ “የራስን እድል በራስ የመወሰን እስከመገንጠል መብቱ በማንኛውም መልኩ ያለ ገደብ የተጠበቀ ነው” እንደማለቱ፣ ሌሎች ብሔሮች፥ ብሔረሰቦች ወይም ሕዝቦች፣ ወይም አግባብነት ያለው ማንኛውም አካል አንድን ብሔር እንዳይገነጠል ወይም ከሌሎች ጋር በአብሮነት እንዲቀጥል ሊያደርጉት አይችሉም። በአጠቃላይ፣ ትላንት ላይ አንድነት አልነበረንም፣ ዛሬ ላይ በልዩነት አለን፣ ነገ ላይ ግን ለመለያየት አቅደናል። ለመለያየት እቅዱ ባይኖር እንኳን መንገዱን አዘጋጅተናል። ስለዚህ፣ ዛሬ ላይ አብረን እያለን ነገ ላይ ተለያይተናል።

የኢህአዴግ መንግስት ስለ ቀድሞ ስርዓት የተሳሳ ተግንዛቤ አለው። ፖለቲካዊ ስርዓቱም በተሳሳተ መርህ ላይ የተመሰረተ ነው። ከምንም በላይ ደግሞ ፖለቲካዊ ስርዓቱ በትላንት እና ዛሬ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው። ይህ ማለት ስለ ትላንቱ የጋራ ታሪክ ወይም ዛሬ ላይ ስላለን የጋራ ጉዳይ አይደለም። “አንድነት” ማለት ነገ ላይ ያለን የጋራ ተስፋና አብሮነት ነው። በትላንቱ ወይም በዛሬ እሳቤ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካዊ ስርዓት የሀገር አንድነትን፥ ፍቅርንና የዜግነት ክብርን ያጠፋል፡-

“If the nation consisted only in past and present, no one would be concerned with defending it against an attack. Those who maintain the contrary are either hypocrites or lunatics. But what happens is that the national past projects its attractions- real or imaginary into the future. A future in which our nation continues to exist seems desirable. That is why we mobilise in its defence, not on account of blood or language or common past. In defending the nation we are defending our to-morrows, not our yesterdays.” The Revolt of the Masses, Ch. XIV: Who Rules the World?, Page 103.

የሀገር አንድነት የወደፊት አብሮነት ነው። ወደፊት ለመለያየት እቅድ ያለን ወይም መንገዱን ያዘጋጀን ሕዝቦች የወደፊት አብሮነት የለንም። የወደፊት አብሮነት ከሌለን ሀገራዊ አንድነት የለንም ወይም ሊኖረን አይችልም። በአጠቃላይ፣ የአሁኗ ኢትዮጲያ አንድነት የላትም። አሁን ያለው ፖለቲካዊ ስርዓት እስካለ ድረስ አንድነት ሊኖራት አይችልም። በዚህ ሁኔታ፣ ዜጎች የሀገር ፍቅር ሆነ የዜግነት ክብርና ኩራት ሊኖራቸው አይችልም። የላቸውም! ምክንያቱም፣ ሀገር የሚመሰረተው፣ አንድነት የሚረጋገጠው፣ እንዲሁም ዜጎች ሀገራዊ ፍቅርና ክብር የሚኖራቸው በሌላ ሳይሆን የወደፊት አብሮነት ሲኖራቸው ነው። ለወደፊት ለመለያየት እቅድ ያለን ሕዝቦች የወደፊት አብሮነት የለንም!!!

በመጨረሻም፣ “ኢትዮጲያዊነት” ማለት በወደፊት አብሮነት ላይ የተመሰረተ አንድነት፣ የሀገር ፍቅር እና የዜግነት ክብር ነው። የኢህአዴግ መንግስት የሀገር አንድነት፣ ፍቅርና የዜግነት ክብር ከአብዛኛው ኢትዮጲያዊ አመለካከት ውስጥ ተፍቆ እንዲወጣ በማድረግ ይህን የአብሮነት መንፈስ ለማጥፋት ተቃርቧል። ጎጠኝነትና ጠባብ ብሔርተንነት ገኖ እንዲወጣ በማድረግ ኢትዮጲያዊነትን ትርጉም አሳጥቶታል። በአንፃሩ፣ የውስን አመለካከት ነፀብራቅ የሆነው ብሔርተኝነትና ጎጠኝነት በብዙሃኑ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። በመሆኑም፣ በግብዝ ዕውቀትና ግንዛቤ ላይ ተመስርቶ ሀገር ማፍረሱን ቀጥሎበታል።

”የአማራ ህገ መንግስት እና ብሔራዊ ጭቆና” (lesane damote)


ከዘውዳዊ ስርዓቱ መዳከም አንስቶ በተለይ ደግሞ ከ1960ዎቹ ጀምሮ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግሮች ሁሉ ምንጩ ብሔራዊ ጭቆና ነው ተብሎ ፣ ጨቋኙና ተጨቋኞቹ ተለይተው ተጨቋኞቹ ከጭቆና ነፃ ለመውጣት የተራዘመ ጦርነት ተካሄደ ።

ከብዙ ወንድማማቾች ህይወት መስዕዋትነት እና ከበርካታ ንብረት ውድመት በኋላ አንፃራዊ ሰላም ተገኘ።
ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ጨቋኝ የተባለው ብሔር ዐማራ እንደሆነ በህወሓት ታውጆና ሰነድ ተሰንዶለት፣ በዚሁ የፖለቲካ ስሪት ክፉኛ ተጎዳ፤ዛሬም እየተጎዳ ነው። ለዚህ ችግር ችግር ዋነኞቹ ተጠያቂዎች ህወሓት እና ኢህዴን (ብአዴን) እንዲሁም አነግ ከነመላ አባሎቻቸው መሆናቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው።

አማራ ላይ የተሰራው እና እየተሰራ ያለው ሴራ የተጠናና ታስቦበት በመሆኑን የአማራን ህገመንግስት መግቢያ ሁለተኛውን አንቀፅ መመልከት ከበቂ በላይ ግንዛቤን ይፈጥራል። ”…በአብዛኛዎቹ በሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ላይ ሲፈፀም በቆየው አስከፊ ብሔራዊ ጭቆና ምክንያት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የጉዳቱ ሰለባዎች ሆነን መቆየታችን በማያዳግም ሁኔታ መታረም እንዳለበት በማመን …”(አዋጅ ቁጥር 59/1994 ዓ.ም )።
ይህንን በአብዛኞቹ በአብዛኛዎቹ በሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ላይ ሲፈፀም በቆየው አስከፊ ብሔራዊ ጭቆና ያደረሰው አማራ ነው እየተባለ ባለበት ሁኔታ ይህንን የመሰለ አደገኛ አገላለጽ በአማራ ህዝብ ህገመንግስት ላይ ሰፍሮ ማየት እጅጉን ያጨሳጫል። ከዚህ አገላለጽ መረዳት እንደምንችለው ብአዴን/አዴፓ ጨቋኙ አማራ ነው ባለዕዳውም አማራ ነው እያለን ያለው።
የአማራ ህገመንግስት በራሱ ህዝብ ላይ የዘመተ የመጀመሪያው ህገ መንግስት ነው። አዴፓ ይህንን ሳያስተካክል መቼም ቢሆን ለአማራ ህዝብ የህልውና ትግል አደርጋለሁ ሊለን ፈፅሞ አፍ አይኖረውም። ስለ ኢፌዴሪ ህገመንግስት መሻሻልም ሊያወራ አይገባውም ። ብአዴን አዴፓ ከሆነ በኋላም ይህንን ተርክት ከፕሮግራሙ እንኳን ያላስወገደ ተልካሻ ድርጅት ነው። እንደውም የፌደራሉ ህገመንግስት ደፍሮ ስለብሔራዊ ጭቆና እንደ አብክመው ህገ-መንግስት አላነሳም ፤ አባባሉን ለዘብ ባለ መልኩ እንዲህ ሲል ገልፆት እናገኘዋለን፤ ”መጪው የጋራ እድላችን መመስረት ያለበት ከታሪካችን የወረስነውን የተዛባ ግንኙነት በማረምና የጋራ ጥቅማችንን በማሳደግ ላይ መሆኑን በመቀበል…”(አዋጅ ቁጥር 1/1995 ዓ.ም ፤መግቢያ አንቀፅ 4)::

ቋንቋን በተመለከተ


የኢፌዲሪ ህገመንግስት አንቀጽ 5 ላይ ስለ ቋንቋ የሚከተለውን ደንግጎ እናገኘዋለን። ”ማነኛውም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በእኩልነት የመንግስት እውቅና ይኖራቸዋል ። አማረኛ የፌዴራሉ መንግስት የስራ ቋንቋ ይሆናል። የፌዴሬሽኑ አባላቶች የየራሳቸውን የስራ ቋንቋ በህግ ይወስናሉ”ይላል። እዚህ ጋር አማራኛ ለምን የሀገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ እንዳልሆነ ግልፅ ነው፤ተቀብለነው እየተሰራበትም ነው። ይህ ካላይ ያየነው የህገመንግስቱ መመሪያ በአማራ ክልል በአግባቡ ስራ ላይ ሲውል በሌሎች ክልሎች ግን ድምፁም አልተሰማም/አይሰማም ።!! ልብ አርጉ በሌሎች ክልሎች ውስጥ ሌላ ቋንቋ የሚናገሩ ብሔር ብሔረሰቦች ሳይኖሩ ቀርተው አይደለም ።

የአማራ ህገመንግስት በክልሉ ውስጥ ስለሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦችና ቋንቋቸው አንቀፅ 5 ላይ እንዲህ ሲል ይገልፃል፤”በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ቋንቋዎች በመንግስት ዘንድ እኩል እውቅና ይኖራቸዋል። አማራኛ የብሔራዊ ክልላዊ መንግስቱ የስራ ቋንቋ ይሆናል” ይላል። ይህ አገላለጽ ከፌዴራሉ ህገመንግስት ለውጥ ሳይደረግበት የተገለበጠ ለክልሉ ህዝብ አደገኛ አንቀፅ ነው። እዚህ ጋር አደገኛ የሚሆነው ለቋንቋዎች የሰጠው የእኩልነት ደረጃ አይደለም ፤ ነገር ግን አማራኛ በአማራ ክልል የክልሉ የስራ ቋንቋ ብቻ ሳይሆን 91% ነዋሪ ህዝብ አማራ በመሆኑ የክልሉ ብሔራዊ ቋንቋም አማርኛ መሆን ነበረበትና ነው።
የቀድሞው ብአዴን የዛሬው አዴፓ ህገመንግስቱን አሻሽሎ አማረኛን በክልሉ ብሔራዊ ቋንቋ በማድረግ፤ በአማራ ጠል አስተሳሰቦች እና አገላለጾች የተሞላውን የክልሉን ህገ መንግስት ሳያሻሽል የፌደራሉ ህገመንግስት ይሻላል ብሎ መጠየቁ እኔ እንደ ግለሰብ ሳየው ጥያቄው አግባብነት ያለው ቢሆንም አዴፓ መጀመሪያ በእጁ የለውን ቢሰራ የተሻለ ነው እላለሁ ።

ስህተት ወይስ መሸፋፈን፦ የጠ/ሚ አብይ ትዕግስት እና የሕግ የበላይነት (በያሬድ ሃይለማርያም)

እንደ እኔ እምነት ከሕግ የበላይነት ጋር በተያያዘ ይህ አይነቱ የተዛባ አስተሳሰብ በእርሶ ደረጃ ካለ ሰው ሊመነጭ የሚችለው በሁለት ምክንያቶች ይመስለኛል፤

አንድም ስለ ሕግ የበላይነት ያለዎት ግንዛቤ የተሳሳተ ነው። ሕግ ማስከበር ማለት አምባገነን ወይም ጨፍላቂ መሆን አይደለም። በሕግ ከተፈቀደው በላይ ኃይል እና ጉልበት መጠቀም እንጂ። መንግስት በሕግ ከተፈቀደው የኃይል እርምጃ በላ እንዲጠቀም የሚያስገድደው ሁኔታ ተፈጥሮ ነገር ግን እራሱብ በሕግ ብቻ ገድቦ ሥርዓት ለማስከበር እየጣረ ቢሆን የትዕግስት ነገር ሊነሳ ይችላል። በሕግ ከተቀመጠው በታች መሆን ደግሞ ትዕግስተኝነት ሳይሆን ሥርዓት አልበኝነት እንዲነግስ መፍቀድ ነው። እርሶ በትዕግስት የሚጠብቁት ዜጎቸ በፈቃደኝነት ሙሉ በሙሉ ሕግ አክባሪ የሚሆኑበትን ዘመን ከሆነ እሱ መቼም አይመጣም። ጭራሽ የዛሬዎቹ አጥፊዎች ሌሎች አዳዲስ አጥፊዎችን ያበረታቱ ይሆናል እንጂ። ትዕግስትዎ ባለቀ ጊዜም ለመቆጣጠርም አስቸጋሪ ይሆናል። በዚህ እረገድ ያሳዩት ትዕግስት የሕግ አክባሪነትን ሳይሆን የሥርዓት አልበኝነት ባህልም ያሰርጻል። ባንክ ሲዘረፍ፣ የንጹሃን አንገት ሲቀላ፣ በመቶ ሺዎች ሲፈናቀሉ እና በማንነታቸው ሲጠቁ እያዩ የምን ትዕግስት ነው? ትዕግስት ካስፈለገስ መብቱን በአግባቡ ለሚጠይቅ ሕዝብ እንጂ ዜጎችን ለሚያሳድድ እና ባንክ ለሚዘርፍ የተደራጀ ነፍሰ ገዳይ እና ዘራፊ ነው ወይ?

ሌላው ምክንያት ግን ከውስጥዎ ትንሽም ብትሆን የምትተናነቅዎት የአንባገነናዊ ስሜት ካለች እንዲህ እንዲያስቡ ልታስገድድዎት ትችላለች። ትዕግስት በሚለው ምሰጣዊ ንግግርዎት ጀርባ የትዕግስት ተቃራኒ የሆነው ጨፍላቂና አፋኝነትም ጎልቶ ይታያል። ይህንንም በገደምዳሜ በተለያዩ መድረኮች እና በትላንቱ ንግግርዎም ጠቆም አድርገውናል። መንግስት አቅም አለው፤ ልዩ ኃይልም በውጭ አገሮች ድጋፍ ጭምር እያሰለጠነ ነው የሚሉ እና ሌሎች ጥቆማዎችን ሰጥተውናል። ትዕግስትዎ ክርንዎ እስኪፈረጥም ከሆነ እሱም ጥሩ አይደለም። ሥርዓት አልበኝነት እና የፈረጠመ የመንግስት ጡንቻ ሲገናኙ መጨረሻው ግልጽ ነው። እሱን መንገድ ደግሞ እስኪያንገሸግሸን ስላየነው የምንጓጋለት አይደለም።

በዚሁ መድረክ ላይ መንግስት እርምጃ መውሰድ በፈለገ ጊዜ የሚሳነው ነገር እንደሌለ ገልጸው ጭራሽ ስላቅ በሚመስል አኳኋን አገሪቱ የሕግ የበላይነትን በማስከበር እረገድ የገጠማት ችግር በሚመከርበት መድረክ እርሶ መንገድ እናጽዳ የሚል የመፍትሔ ሃሳብ ማቅረብዎ አንድም ችግሩን ከቁጥጥሬ አይወጣም በሚል ስሜት ማቃለልዎት አለያም የውይይት አቅጣጫ ለማስሳቀየስ የተናገሩት ነው የሚመስለው።

አሁንም ደጋግመን የሕግ የበላይነት ይከበር ስንል አንባገነን ሁኑ ወይም የማይገባ እና ያልተመጣጠነ የኃይል እርምጃ ውሰዱ እያልን አይደለም። አጥፊዎች በሕግ አግባብ በወቅቱ ይቀጡ፣ መንግስት ያለውን ሰፊ መዋቅር ተጠቅሞ የቅድመ አደጋዎች እና ግጭቶች የመከላከያ እቅድ ነድፎ ይንቀሳቀስ፣ አደጋዎች መኖራቸው ሲገለጽ ዳር ቆማችሁ ይለይለት በሚመስል መንገድ ስትመለከቱ ከቆያችው በኋላ ተጎጂዎችን ማጽናናት እና ለቅሶ መድረስ ጥቅም የለውም። መንግስት የዜጎችን ደህንነት እና መብት የመጠበቅ እና የማስጠበቅ ግዴታውን ማክበር አለበት። ሕግ ሲጣስ ትዕግስተኛ መሆነ ግን ለጊዜው ወንበራችሁን ባይነቀንቀውም ሕዝቡን ግን የህይወት እና የንብረት ዋጋ እያስከፈለው መሆኑ ልታጤኑት ይገባል።

አሁንም የሕግ የበላይነት ይከበር!

ከአማራነት በፊት ኢትዮጵያዊነት ይቅደም ለሚሉ ለነታማኝ በየነ የተወሰኑ ነጥቦች ማንሳት እፈልጋለሁ፡-(lesane damote)

 1. የአንድነት ደጋፊ የሆኑ የአማራ ምሁራንና አክቲቪስት ነን የሚሉ ግለሰቦች ነባራዊ ሀቁን የተረዱ ግን ደግሞ ከሌላዉ ብሄር በተለዬ አማራ ለኢትዮጵያዊነት ራሱን መስዋዕት ማድረግ አለበት የሚሉ (የአማራን ህዝብ ጥቅም ለሌላዉ ብሄር ጥሎሽ የሚያቀርቡ) ናቸዉ፡፡ ይህ ግብዝነት ይባላል፡፡ እነዚህ እንደ አበበ ገላዉ ፣ታማኝ በየነ እና ዶክተር አንማው አንተነህ (ለጊዜዉ ራሳቸዉን ያጋለጡ የዚህ ሀሳብ አቀንቃኞች) ያሉ ግለሰቦች ያልተረዱት ነገር ቢኖር፣ አማራዉ እንኳን አሁን አቅም እንዳይኖረዉ በየአቅጣጫዉ በተዘመተበት ሰዓት፣ ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ አንድነት ለከፈለዉ መስዋዕትነትም ቢሆን ከምስጋና ይልቅ፣ እጁ አመድአፋሽ ሆኖ፣ እንደ ባለዕዳ ታይቶ ይቅርታ ይጠይቅ የሚባልበት ጊዜ ነዉ፡፡ ስለዚህ አማራ በአማራነቱ ብቻ ይዳራጃል፡፡
 2. አበበ ገላዉ፣ ታማኝ በየነ፣ አንማው አንተነህና ሌሎችም የአንድነት አቀንቃኝ አማራዎች (እነሱ አማራ አይደለሁም ጎጃሜ፣ ጎንደሬ፣ ወሎዬ፣ ሸዋ ነኝ ነዉ የሚሉት) በዕድሜ ስለገፉ እንጂ በአሁኑ ሰዓት ያለዉ 65% የአማራ ህዝብ እድሜዉ ከ24ዓመት በታች (ማለትም ህወሀት አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ የተወለደ) ነዉ፡፡ ወያኔ ሲገባ ከ 10ዓመት በታች እድሜ የነበራቸዉን ስናጠቃልል ወደ 80 በመቶ የሚሆነዉ ህዝብ እኮ አማራ ክልልን እንጂ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አይደለም የሚያዉቁት፣ ፓስፖርት ሲያወጡ” ወይም “ብሔራዊ ፈተና ሲፈተኑ” ብቻ ነዉ፡፡ አሁንኮ “ኢትዮጵያ ትቅደም” የሚል መፈክር የለም፡፡ አሁንኮ አማራ እንደ ኋላቀር፣ ድሀ፣ መሪ የሌለዉ፣ አርሶ ለገበያ ለማቅረብ ብቻ የሚመሳለቸዉ ብዙ ብሄሮች አሉ፡፡ አማራኮ ተንቋል፡፡ የራሱን ታታሪ ህዝብ፣ የተማረ ሀይል፣ እና ለም መሬት ይዞ፣ የራሱ ስትራቴጂ ኖሮት፣ ራሱን በኢኮኖሚ አሳድጎ፤ ታስፈልገናለህ ተብሎ ነዉ ኢትዮጵያዊ መሆን ያለበት፡፡ እንደ አንድ ግዛት እንጂ የግዞተኞች መሬት መሆንም አይችልም/አይሆንም፡፡
 3. የአንድነት አራማጆች አማራ በአማራነቱ ሲደራጅ “ወያኔ በቀደደዉ ቦይ” ገባችሁ ማለት ነዉ ይላሉ፡፡ ነገር ግን፣ በእኔ አስተያየት እነዚህ የአንድነት አቀንቃኞች ናቸዉ ወያኔ ከቀደደዉ ቦይ ዝንፍ ሳይሉ እየፈሰሱ የሚገኙት፡፡ ምክንያቱም “ወያኔ በቀደደዉ ቦይ” ማለት ወያኔ ከነዚህ ህዝቦች Expect የሚያደርገዉን ማድረግ ማለት ነዉ፡፡ የወያኔ Expectation ደግሞ አማራዉ አንድነት ላይ የሚያሳየዉ ግትር አቋም እና ኦሮሞዉ ነጻ ሀገር ለመሆን የሚያሳየዉ ፍላጎት ናቸዉ፡፡ ለነዚህ ሁለት ተቃራኒ ጉዳዮች ወያኔ ተፈትኖ የተረጋገጠ መድሀኒት አለዉ፡፡ አማራዉን ትምክተኛ፣ነፍጠኛ እያለ፤ ኦሮሞዉን ደግሞ ጠባብ እያለ ከሁሉም ብሄሮች ጋር ለማጣላት ሲጥር ኖሯል፡፡ ነገር ግን የወያኔን አከርካሪ የሰበረዉ ስትራቴጂ፣ አማራ በአማራነት ተደራጅቶ ከዚያ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲሰራ ነው።

የጀርመኑ ኦቶ ቮን ቢስማርክ እኮ ያለዉ– “Politics is the art of the possible” ነዉ፡፡ የታማኝ፣ የአበበ እና የሌሎች ፖለቲካ ግን “Politics is the art of forming a utopian society” ይመስላል፡፡ ያ ደግሞ በአንድ ሺ ዓመት እንኳ የሚሆን አይመስልም፡፡

 1. በቅርቡ አንድ ሪፖርተር ላይ የሚሰራ ጋዜጠኛ እኔ ትግሬ ነኝ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ብሎ ጽፎ ነበር፡፡ ትግሬ፣ አማራ፣ ኦሮሞ የሚባል ማንነት እንጂ ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት የለም ብሎ ነበር፡፡ ጃዋር ሞሀመድም እኔ ኦሮሞ እንጂ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ብሎ ነበር፡፡ መለስ ዜናዊም “እንኳን ከዚህ ከወርቅ ህዝብ ተወለድሁ” ያለዉ የትግራይን እንጂ የኢትዮጵያን ህዝብ አይደለም፡፡ ስለዚህ አማራ ከአማራ በፊት ኢትዮጵያዊ ነኝ ቢል የሚጠብቀዉ ያልተደራጀና የተበታተነ ለመጠቃት የተመቸ መሆን ነዉ፡፡ እየታየ ያለው ነባራዊ እውነታም ይህ ነው። ኪሳራዉም ብዙ ነዉ፡፡ የመለስ ዘመነኞች የተሸዱትን በድጋሜ ይሸወዳል፡፡ እንዲያዉም በዚያ ዘመን በአንድ ኢትዮጵያ የሚያምኑ ብዙ ትግሬዎች፣ ኦሮሞዎች ፣ ወላይታዎች፣ አፋሮች የነበሩበት ነዉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግን ኢትዮጵያዊ አንድነትን ቅድሚያ የሚሰጥ ብሄር የለም፡፡ ከአንዳንድ ዲያስፖራ አማራዎችና ፖለቲካ ከማይገባቸዉ ጨዋ ሰዎች በስተቀር፡፡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችም ኢትዮጵያዊ በሚለዉ ሳይሆን እንደብሄራቸዉ ይቀራረባሉ፡፡ ስለዚህ አማራዉ ቅድሚያ በአማራነት ተደራጅቶ ከዚያ ለኢትዮጵያዊነት ከሌሎች ብሄረሰቦች ጋር በተለይ ከኦሮሞዉ ጋር መተባበር እና መደራደር ይጠብቀዋል።
 2. በኃይለ ሥላሴ ዘምን ዘመኑ ኋላቀር በመሆኑ ሁሉንም ብሄሮች ለብሄር-ትግል ለማደራጀት አይመችም ነበረ፡፡ እንዲሁም ሁሉም ኢትዮጵያ ብሄሮች አንድ የሚያደርግ ነገር ነበራቸዉ፡፡ ይኸዉም አገሪቱ የንጉሱ ፋብሪካ ስትሆን ሁሉም ህዝቦች ደግሞ እንደ ወዛደር ነበሩ፡፡ አሁን ግን ሁሉም ነገር ተቀይሯል፡፡ ያለዉ የመከፋፈል ችግርም ቀላልና የሚጠገን አይደለም፡፡ ያለዉ ከ80 በላይ ብሄር ስለራሱ ነዉ የሚያስበዉ፡፡ ወጣቱም እየተማረ ያደገዉ ይህንኑ ነዉ፡፡ ስለዚህ በአማራ ፍላጎት ብቻ አንድነት ማምጣት አይቻልም፡፡አሁን ያለዉ ፈታኝ ችግር እንደ simultaneous equation አይደለም፣ ያሉት variables ከ80 በላይ ናቸዉ፡፡ ነገር ግን፣ አማራ የማይመራዉ (የአማራን ጥቅም እንደሁልጊዜዉ የማያስጠብቅ) የአንድነት መንግስት መመስረት ላይከብድ ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ጥያቄዉን ለማቅለል የአንድነት ሀይሎች boundary condition ሊያሰቀምጡ ይችላሉ፡፡ እናም ሁሌም የፖለቲካ ድርጅቶች ኢላማ የሆነዉን ህዝብ መስዋዕት በማድረግ Assume there is no Amhara ብለዉ ሊነሱ ይችላሉ፡፡
 3. በፊዚክስ ትምህርት ዉስጥ Entropy (it is a measure of disorder) የሚባል ንድፈ ሀሳብ አለ፡፡ Entropy ሁሌ እየሰፋ ይሄዳል፡፡ ለምሳሌ አንድ አሞሌ ጨዉ በአንድ ገንዳ ዉሀ ዉስጥ ብትጨምሩት፣ ጨዉ እየሟሟ ይሄዳል፣ ሞሎኪዉሎቹ እየተራራቁ ይሄዳሉ እንጂ የሚሰበሰቡበት አጋጣሚ የለም፡፡ አንድ የጋለ ብረት አንድ ክፍል ዉስጥ ብታስቀምጡ ሙቀቱ በክፍሉ ዉስጥ ይሰራጫል እንጂ የክፍሉ ሙቀት ተሰብስቦ ብርት አይሞቅም፡፡ የተፈጥሮ አካሄዱ መበታተን ነዉ፡፡ ይህን ንድፈ ሀሳብ ወደ ህብረተሰባችን መስተጋብርና ፖለቲካ አዉርደን ብናየዉ የኢትዮጵያ ብሄሮች ከዚህ በኋላ እንደድሮዉ እንድ ነን ይላሉ፣ ስለ አማራ ጭራቅነት ተነግሮት ያደገ ትዉልድ ስለአማራ ደግነት ያወራል ማለት ዘበት ነዉ፡፡ አብዛኛዉ አማራ ሌሎች ብሄሮች ይጠሉኛል ብሎ አያስብም፡፡ ሌሎች ብሄሮች ስለ አማራ ያላቸዉ አመለካከት ቢነገረዉ እንኳ አይሰማም፡፡ ነገር ግን እዉነታዉ ሌላ ነዉ፡፡ ስለዚህም ነዉ አማራ አንድነት ያስፈልገዋል ራሱን ለመጠበቅ፣ የልማቱ ተካፋይ ለመሆን፣ ባህሉን፣ እምነቱን፣ ትዉልዱን ለማስቀጠል የሚባለዉ፡፡ በተለይ ወያኔ ኢትዮጵያ ላይ ጢባ ጢቤ ከተጫወተ በኋላ በብሄሮች መካከል ያለዉ ያለመተማመን እየጨመረ ነዉ የመጣዉ፡፡ ተመልሰን ወደ ዘር ቆጠራ መግባት ግድ ይለናል፡፡ ይህን የማታምን አማራ አንገትህ ሲቆረጥ ይገባሀል፡፡ የአማራ ዲያስፖራዎች በኢትዮጵያዊነትህ ሻማ ያበሩልህ ይሆናል፡፡ በአማራነትህ ኢላማ ስትሆን ግን ቢያዉቁም አይነግሩህም፡፡ ለአለፉት አርባ አመታት አየተጨቆነ እየተገደለ እንኳን ምንም እንዳልተነካ ሁሉ ተሸፋፍኖ የተኛ እና ያልተደራጀ ህዝብ አሁንም ለህልዉናዉ በሚያሰጋ ሁኔታ ላይ ሆኖ እንኳን የራሷ አሮባት የጎረቤት ታማስላለች አይነት እንዝላልነት በተለይ በተማረዉ እና ከተጎሳቆለዉ የአማራ ገበሬ የተገኙ መሁራን በአዚም መጠቃት ያበሽቃል፡፡ እነዚህን እና የመሳሰሉትን ስታዩ ሚሚ ስብሀቱ “ሪታርድስ” ያለችዉ፣ ሌላዋ “አህዮቹ ሮቦሹኝ ኡኮ” ያለቸዉ፣ እንዲሁም እንዲሁም አባይ ጸሀየ “ኳላ ቀሮች” ያለዉ፣ እዉነታቸዉን ይሆን እንዴ እላለሁ፡፡ መቸም የተማረ አማራ ሁሉ ሀያ አምስት አመት ከብዙ ጥቅማ ጥቅም ሁሉ ተገልሎ እንኳን በአማራነት አልደራጂም ካለ ችግር ቢኖር ነዉ እላለሁ (በአሁኑ ሰዓት ያለዉ ምሬት እና መነሳሳት እንዳለ ሆኖ)፡፡
 4. በአሁኑ ሰዓት አንድነት ወይም ኢትዮጵያዊነት የሚል አማራ ካለ እሱ የድሮ ዘመን ሰዉ ነዉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚኖር አማራ ስለ ኢትዮጵያዊነት ምንም ስሜት የለዉም፡፡ ምናልባት እንደ አዲስ አበባ፣ ናዝሬት፣ ድሬዳዋ እና ሀዋሳ ያሉ ከተሞች የሚኖሩ አማራዎች አንድነት ሊሉ ይችልሉ፤ ነገር ግን እሾህን በእሾህ እንደሚባለዉ በአሁኑ ሰዓት በአማራነት፣ በኦሮሞነት፣ በሲዳማነት፣ በጉራጌነት ካልተደራጀን ህልዉናችን አደጋ ላይ ነዉ፡፡ እስኪ ታማኝ በየንን እዩት ሀያ አምስት አመት ሙሉ አንድ ኢትዮጵያ ብሎ ያተረፈዉ ነገር ምንድን ነዉ፡፡ ታማኝና መሰሎቹ አቋማቸዉን ቀይረው በአማራነት ካልተደራጀ ከታማኝ በፊት ቀድመዉ አማራ ክልል የሚገቡት የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) አባላት፣ ኦነግ፣ ወይም ሻዕቢያ ናቸዉ፡፡ ከዚያም አበበ ገላዉ “We need Freedom! Mr. X is a dictator.” ለማለት፣ ታማኝ በየነም የአንዱን ባለስልጣን በትግል ወቅትና በስልጣን ዘመን ያደረገዉን ንግግር ኤዲት እያደረገ ኮሜዲ ለመስራት የሚያደርስ መንገድ ነዉ፡፡

”አገው-አማራ/አማራ-አገው => ላይለያይ የተዋሐደ አንድ ሕዝብ” (መላኩ አላምረው)

በ18/09/2011ዓ.ም በዳንግላ ከተማ የአማራ ወጣቶች ህብረት ሲመሰረት

አገው-አማራ/አማራ-አገው ፈጽሞ የሚለያይና በሁለት ሕዝብነት የሚያቆም ማንነት የሌላቸው ሕዝቦች ናቸው። ከወንድማማችነትም ባለፈ አባትና ልጅ ናቸው። አገውና አማራ በቋንቋም ቢሆን አንዱ የአንዱን እየተለማመደና እርስ በርሱ እየተጋባ የተዋሐ ሕዝብ ነው። ከአገው ያልተጋባ አማራ ከአማራ ያልተዋለደ አገው ቢፈለግ ለመድኃኒትም አይገኝ። አንዱ ነፍስ ነው ብንል ሌላው ሥጋ ነው። ተለያይቶ የሚኖር ሕልውና የላቸውም። አንዱ ራስ ነው ብንል ሌላው ልብ ነው። አንዱ ያለሌላው ሕይወት አይታሰብም። አንዱን ከሌላው ለመለየት መሞከር ማለት የሁለቱንም ሕልውና ማሳጣት ነው። በሌላ አባባል ሕዝቡ ውሕደቱ ያለቀለት አንድ ሕዝብ ነው። (ይህ ታሪክ ማገላበጥ ሳያስፈልግ አሁን መሬት ላይ ያለ ነባራዊ ሐቅ ነው።) በታሪክም በእምነትም በባሕልም አይለያይም። የቋንቋ ልዩነቱን ውበት አድርጎ የሚኖር ሕዝብ ነው። አማርኛ ቋንቋ እንኳን የቤተ መንግሥትና የወታደር ቋንቋ ሆኖ በከፍተኛ ሁኔታ የተስፋፋው በዛግዌ ሥርዎ መንግሥት ነገሥታት ዘመን ነበር። ይህም አንዱ ሕዝብ ለሌላው ቋንቋ ያለውን ፍቅር በግልጽ ያሳያል። በሌላ አባባል አገው-አምራ/አማራ-አገው ሁለት ቋንቋ የሚናገር አንድ ሕዝብ ነው።

አገው እና አማራ በሰምና ፈትልነት በጋራ ጧፍ ሆኖ ለኢትዮጵያ የበራ/ያበራ ሕዝብ ነው። ሰምና ፈትልን በመለያየት ብርሃን ሰጭ ጧፍ ለማግኘት የሚሞክር ካለ የዋህ ነው። ሰምና ፈትልን ለመለየት መሞከር የሁለቱንም ሕልውና ለማሳጣት መሞከር ነው። ሰምና ፈትል አንዴ ከተዋሐደ በኋላ ልንለያይ ብንሞክር ውጤቱ ሁለቱንም ከጥቅም ውጭ ማድረግ ነው። ሰምና ፈትል እንደተዋሐደ ስንለኩሰው ነው ብርሃን የሚሰጠው። ሁለቱ ተለያይቶ ብርሃን የለም። የእኛ ብርሃን እውን የሚሆነው በአገውና አማራ ሰምና ፈትልነት ነው።

አገው እና አማራ ፍጹም የተጋመደ፣ የተዋለደና የተዋሐደ ብቻ ሳይሆን በሥነ ልቦናም በእምነትም ፍጹም አንድ የሆነ ሕዝብ ነው። ሺህ ዘመናትን አብሮ ኖሯል። አብሮ በኖረባቸው ሺህ ዘመናት ሁሉ የፍቅርና የመዋለድ እንጅ የጥልና የግጭት ታሪክ ኖሮት አያውቅም። ምክንያቱም አንዱን ካንዱ ሊለየው የሚችል የተለየ ነገር ስለሌለ ነው። እንዱን እንዲህ ነህ ብንለው ሌላውም አብሮ እንዲያ ነው።

የአማራንና የአገውን ሕዝብ ለይቶ ለየብቻ ለማስቀመጥ መሞከር አባትን ከልጅ ልጅን ከእናት የመለየት ሙከራ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ። አማራ እና አገው ወንድም ሕዝብ ከምንለው የዘለለ አንድነት አለው። አማራ አባት ብለን ዘር ብንቆጥር አገው ልጅ ሆኖ እናገኘዋለን። አይ የለም አገው ነው አባት ብለን ብንነሳም አማራን ልጅ ሆኖ እናገኘዋለን።

አሁን ላይ የመጡ አንዳንድ ልዩ ተልዕኮ ያላቸው እንቅስቃሴዎች ይታያሉ። አንዳንድ ሚዲያዎችም አገውን ከአማራ ለመነጠልና እንደተለየ ሕዝብ በማሳየት ሌላ ፖለቲካዊ አላማን በመሰነቅ እያራገቡት እንደሆነ እናውቃለን። ይሁንና ይህ ከንቱ ድካም መሆኑንም እንረዳለን። የአገው ሕዝብ ከአማራ ይህ ነው የሚባል ልዩነት የለውም። የአማራም ከአገው። “አገውና አማራ” እያሉ እንደ ሁለት ሕዝብ መጥራት ራሱ ይከብዳል። በተለይ ሀገራዊም ሆነ እምነታዊ ሥነ-ልቦናቸው አንድና ያው ነው። የቋንቋ ልዩነታቸውም ተከብሮ አንዱ በሌላው ቋንቋ እየተግባባ ነው የሚኖሩት። በብዛት አገውኛ (አዊኛ/ኽምጥኛ) የሚነገርባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ደግሞ በዞን ደረጃ ተፈራጅተው ራሳቸውን በራሳቸው እያስተዳደሩ ነው። ይህም የሆነው በመሠረታዊነት ከአማራ የሚለያቸው የተለየ ማንነት ስላላቸው ከአማራ ጋር አንኖርም አብረንም አንተዳደርም ብለው ሳይሆን ማንም ሰው በአፍ መፍቻ ቋንቋው የመግባባትና የመተዳደር መብት ስላለው የተደረገ ነው። ይህን ሕዝብ ለያይቶ ለማቆም እንደመድከም ያለ ከንቱ ድካም የለም።
አገውና አማራ ላይለያይ አንድ ሆኖ የተዋሐደ ሕዝብ ነው!!!

የመንግሥት ድርጅቶችን ወደ ግል ማዛወር አስመልክቶ ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ


ኢህአዴግ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ለግል ባለሀብቶች ለመሸጥ የሚያስችል የህዝብ ፈቃድ እና ይሁንታ የለውም።
ውሳኔው ከኢኮኖሚያዊ አዋጭነት አንጻርም ተቀባይነት የሌለው ነው።
**
ገዥው ፓርቲ ሀገር የሚመራበትን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስር ነቀል በሆነ መልኩ ለመቀየር የሚችለው አዲስ ምርጫ ሲደረግ እና አዲሱን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለምርጫ ውድድር አቅርቦ የህዝብ ፈቃድ እና ይሁንታ ሲያገኝ ብቻ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ከሀገር የተዘረፈ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር መኖሩን አምነው፣ የተዘረፈው ገንዘብ ተደብቆ የሚገኝባቸው ሀገራት ተለይተው እንደታወቁ እና ሀገራቱ ገንዘቡን ተመላሽ ለማድረግ ለትብብር ፈቃደኛ እንደሆኑ ገልጸው መንግስታቸው የተዘረፈውን ገንዘብ እንደሚያስመልስ ቃል ቢገቡም፣ አንድ ሽራፊ ሳንቲም ወደ መንግስት ካዝና ሳይመለስ የኢትዮጵያውን አንጡራ ሀብት የሆኑትን የንግድ ድርጅቶችን እና ብቸኛው ወደባችን በመሸጥ ፓርቲያቸው እና መንግስታቸው ለሌላ ዙር መንግስታዊ ዝርፊያ እየተዘጋጀ ይገኛል።

አየር መንገዳችን ካለው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባሻገር በኢህአዲግ የተለመደ የሀገር ጥቅምን አሳልፎ የመስጠት ፖለቲካዊ ባህል ምክንያት ወደብ አልባ ለሆነችው ሀገራችን ብቸኛ ወደብ ሆኖ ከመላው ዓለም ጋር የምንገናኝበት ነጻ በራችን በመሆኑ ለሉዓላዊነታችን እና ብሔራዊ ጥቅማችን መከበር የማይተካ ሚና የሚጫወት ነው፡፡

በአጠቃላይ የኢህአዴግን ያለፉት አመታት የሙስና እና የሀብት ብክነት የገነገነ ልማድ ልብ ላለ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ሽያጭ ሊገኝ የሚችለው በብዙ ቢሊየን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚባክን ከወዲሁ የሚያረጋግጥ ሲሆን ሽያጩ ጊዚያዊ የዶላር እጥረታችንን ይቀርፋል ቢባል እንኳ ገዣዎቹ ከሚገዟቸው ድርጅቶች የሚያገኙትን ዓመታዊ ትርፍ በየዓመቱ በውጭ ምንዛሬ የሚወስዱ በመሆኑ በመካከለኛ እና በረዥም ጊዜ ውስጥ የዶላር እጥረቱን የበለጠ የሚያብብስ ውሳኔ ነው፡፡

ኢህአዴግ በምርጫ ዋዜማ ላይ በምንገኝበት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ውሳኔ ቢወስንም ውሳኔውን የሚተችም ሆነ ውሳኔውን ለማስቆም ጥረት የሚያደርግ አንድም የተደራጀ የፖለቲካ ሀይል ባለመኖሩ አደጋውን የመቀልበስ ኃላፊነት በፓርቲያችን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) ትከሻ ላይ ወድቋል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ 4ኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ከጥቂት ወራት በኋላ ለማከናወን በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል። ላለፉት 28 አመታት በስልጣን ላይ የቆየው ኢህአዴግ በስልጣን ላይ በቆየበት ዘመን ሲመራበት የነበረውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በድንገት በመቀየር ለበርካታ አስርት ዓመታት በመንግስት ባለቤትነት እና ይዞታ ስር የቆዩ ስትራቴጅክ ሀገራዊ ሀብቶቻችንን ለውጭ ባለሃብቶች ለመሸጥ ውሳኔ አሳልፏል።

ኢህአዴግ ስልጣን የያዘው እና በስልጣን ላይ የቆየው በህዝብ ፈቃድ እና ይሁንታ እንዳልሆነ ቢታወቅም ከእነጉድለቱም ቢሆን የራሴ የሚለው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ቀርጾ ስራ ላይ በማዋል፣ ተለይቶ በሚታወቅ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሀገር ሲያስተዳድር መቆየቱ የሚታመን ነው። ኢህአዴግ ሲመራበት የቆየበት ዋነኛው የኢኮኖሚ ፖሊሲ “ልማታዊ መንግስት” በሚል ፍልስፍና የሚታወቀው እና ስልታዊ እና ዘለቄታዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ዋና ዋና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በመንግስት ይዞታ ስር ማቆየት የሚል የነበር ሲሆን በቅርቡ ወደ ስልጣን በመጡት ሊቀመንበሩ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ አመራር አማካኝነት ስር ነቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጥ በማድረግ በመንግስት ባለቤትነት እና ይዞታ ስር የሚገኙ ግዙፍ የኢኮኖሚ ዘዋሪ ድርጅቶችን ለውጭ ባለሀብቶች ለመሸጥ እና ድርጅቶችን ወደ ውጭ የግል ባለሃብቶች ለማዛወር መወሰኑን ለህዝብ በማሳወቅ ድርጅቶቹን ለመሸጥ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ይገኛል።
በመሰረቱ አንድ በስልጣን ላይ የሚገኝ ፓርቲ በድንገት ለዚያውም በምርጫ ዋዜማ ላይ ሀገር የሚመራበትን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ከመሰረቱ ለመለወጥ የሚያስችል ህጋዊም ሆነ ፖለቲካዊ የስልጣን መሰረት የለውም። ኢህአዴግ የህዝብ ይሁንታ አግኝቶ ስልጣን እንዳልያዘ ቢታወቅም፣ ስልጣን የያዘው በህዝብ ይሁንታ እና በምርጫ አሸንፎ ነው ቢባል እንኳ ገዥው ፓርቲ ሀገር የሚመራበትን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስር ነቀል በሆነ መልኩ ለመቀየር የሚችለው አዲስ ምርጫ ሲደረግ እና አዲሱን የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለምርጫ ውድድር አቅርቦ የህዝብ ፈቃድ እና ይሁንታ ሲያገኝ ብቻ ነው። ኢህአዴግ ምንም አይነት የህዝብ ይሁንታ እና ፈቃድ ሳያገኝ፣ ይልቁንም በህግ አግባብ የስልጣን ዘመኑ በሚጠናቀቅበት ዋዜማ ላይ ሆኖ ስር ነቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጥ በማድረግ ላለፉት 100 እና 75 አመታት በመንግስት ይዞታ ስር የቆዩ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ለውጭ ባለሃብቶች ለመሸጥ መወሰኑ የህግ፣ የሞራል እና የፖለቲካ ቅቡልነት (Legitimacy) የሌለው ውሳኔ ነው።

ሙስና እና ብልሹ አሰራር ዋነኛ መገለጫው የሆነው ኢህአዴግ ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታው በማታውቅ ከፍተኛ የውጭ መንግስታት እዳ /Sovereign Debt/ ውስጥ እንድትዘፈቅ አድርጓል፡፡ ኢህአዴግ በብድር የተገኝውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ያለምንም ተጠያቂነት ከአባከነ እና የግንባሩ አባል ድርጅቶች በህገወጥ መንገድ ለሚነግዱባቸው የፓርቲ የንግድ ድርጅቶች ገንዘቡን ካሸሸ በኋላ ተከታታይ ትውልዶች ተቸግረው ያቆዩንን ሀገራዊ ሀብቶቻችንን እና የብሔራዊ ኩራት ምንጭ የሆነውን አየር መንገዳችንን ለውጭ ባለሀብቶች ለመሸጥ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባቱ ፓርቲው ለሌላ ዙር ዝርፊያ ራሱን እያዘጋጀ እንደሚገኝ የሚያረጋግጥ ውሳኔ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ከሀገር የተዘረፈ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር መኖሩን፣ የተዘረፈው ገንዘብ ተደብቆ የሚገኝባቸው ሀገራት ተለይተው እንደሚታወቁ እና ሀገራቱ ገንዘቡን ተመላሽ ለማድረግ ለትብብር ፈቃደኛ እንደሆኑ ገልጸው መንግስታቸው የተዘረፈውን ገንዘብ እንደሚያስመልስ ቃል ቢገቡም አንድ ሽራፊ ሳንቲም ወደ መንግስት ካዝና ሳይመለስ የኢትዮጵያውን አንጡራ ሀብት የሆኑትን የንግድ ድርጅቶችን እና ብቸኛው ወደባችን እና የሉዓላዊነታችን መገለጫ የሆነውን አየር መንገዳችንን በመሸጥ ፓርቲያቸው እና መንግስታቸው ለሌላ ዙር መንግስታዊ ዝርፊያ እየተዘጋጀ ይገኛል። ለግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች እና ለመሰረታዊ ማህበራዊ ልማቶች በከፍተኛ ወለድ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር ከውጭ መንግስታት ተበድሮ (ዕዳችን ካጠቃላይ ሀገራዊ ምርት 60% ይሸፍናል)፣ ገንዘቡን በማባከን ሀገራችንን ለብድር አዙሪት የዳረገ ፓርቲ እና መንግስት፣ የሀገር አንጡራ ሀብት የሆኑ ድርጅቶቻችንን ከሙስና እና ብልሹ አሰራር በጸዳ ሁኔታ ለውጭ የግል ባልሀብት ለማስተላለፍም ሆነ ከሽያጩ የሚገኝውን በቢሊየን የሚቆጥር ዶላር በኃላፊነት ይገለገልበታል ተብሎ አይታመንም።

ስለሆነም ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ኢህአዴግ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ለመሸጥ ያሳለፈውን ውሳኔ በዋነኛነት የሚቃወመው ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ድርጅቶችን ለመሸጥ የሚያስችል የህዝብ ፈቃድ እና ይሁንታ /political legitimacy/ ስሌለው ቢሆንም አብን የመንግስት ውሳኔን ከኢኮኖሚ አዋጭነት አንጻር በመተንተን፦
የኢትዮ ቴሌኮምን ሽያጭ በተመለከተ ውሳኔው ጊዜውን ያልጠበቀ እና ከፈረሱ ጋሪውን ያስቀደመ ውሳኔ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን፤የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሽያጭን በተመለከተ ግን ውሳኔው ከስግብግብነት ውጭ ምንም አይነት ኢኮኖሚያዊ አመክንዮ የሌለው መሆኑን አረጋግጧል።

በመንግስት ባለቤትነት እና ይዞታ ስር ያሉ በተለይም በሕግ በብቸኝነት የመነገድ እና አገልግሎት የመስጠት መብት /Monopoly Rights/ የተሰጣቸው ግዙፍ የንግድ ተቋማት ከመሸጣቸው እና ወደ ግል ባሀብቱ ይዞታ ከመዞራቸው በፊት በቅድሚያ ድርጅቶቹ የተሰማሩበትን ዘርፍ ለውድድር ክፍት የማድረግ /Liberalization/ ስራ ሊሰራ ጠንካራ ተፎካካሪ አገልግሎት ሰጭ የንግድ ተቋማት ሊገነቡ እና ዘርፉን የማተስተዳር እና የመምራት ጠንካራ አቅም /Regulatory Framework and Capacity/ ሊገነባ እንደሚገነባ ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ያምናል፡፡ No Privatization before Liberalization!

፩. ኢትዮ ቴሌኮም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከ100 መቶ ዓመታት በላይ አገልግሎት የሰጠ ብሐራዊ ሀብት ሲሆን ተቋሙ አሁን ዓለም ከደረሰበት የቴሌኮም አገልግሎት ጥራት እና ደረጃ አንጻር ብዙ እጥረቶች እንዳሉበት ይታወቃል፡፡ ዘርፉ ሊዘምን እና ለግል ባለሀብቱ ውድድር ክፍት ሊሆን እንደሚገባው ፓርቲያችን ያምናል፡፡ ነገር ግን ዘርፉን የማስተዳደር እና የመምራት ጠንካራ አቅም (Regulatory Framework and Capacity) ሳይፈጠር እና ዘርፉ ለውድድር ክፍት (Liberalization) ሳይደረግ፣ በብቸኝነት ለመነገድ እና አገልግሎት ለመስጠት በህግ ከለላ የተሰጠውን ተቋም በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ወደግል ሀብት ይዞታ ለማዞር መንግስት ያሳለፈው ውሳኔ፣ ከፈረሱ ጋሪውን ያስቀደመ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም የሚጎዳ እና ህዝባችንን ለከፍተኛ ብዝበዛ የሚያጋላጥ ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ በመሆኑ ውሳኔው ሊቀለበስ የሚገባው ነው፡፡

፪. መንግስት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለመሸጥ ያሳለፈው ውሳኔ ፍጹም ሃላፊነት የጎደለው እና በየትኛውም የኢኮኖሚ ትንታኔ ስሜት የማይሰጥ ውሳኔ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስራ ላይ በቆየባቸው ላለፉት 75 አመታት አንድም ጊዜ የመክሰር እና የመፍረስ አደጋ ያላገጠመው ለኢትዮጵያውን ኩራት፣ ለአፍሪቃውያን ደግሞ በአለም መድረክ ላይ በሚደረግ የንግድ ውድድር አፍሪቃውን ብቁ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረብ እንደሚችሉ ያነቃቃ እና የይቻላልን መንፈስ በአፍሪቃውያን ላይ ያሳደረ ብሄራዊ ሀብታችን ብቻ ሳይሆን ህያው ቅርሳችን ጭምር ነው፡፡ አየር መንገዱ አሁን ባለው ወቅታዊ አቋሙ ከአስተዳደር ጋር በተያያዘ ብዙ ቅሬታዎች የሚነሱበት ቢሆንም ባለው ውጤታማነት እና ትራፋማነት ከአህጉራችን አፍሪቃ ቀዳሚው አየር መንገድ ሲሆን በዓለም ከሚገኙ ትርፋማ እና ምርጥ አየር መንገዶች አንዱ ነው፡፡ እውቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ በጥናታቸው እንዳረጋገጡት የኢትዮጵያ አየር መንገድን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ወደግል ባሀብቱ ለማዞር የሚያበቃ ምንም አይነት ስሜት የሚሰጥ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የለም፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እ.ኤ.አ ከ2013/14 እስከ 2015/16 ባለው ጊዜ ውስጥ ባማካኝ ከ8% በላይ የትርፍ ህዳግ ያስመዘገበ ሲሆን አለም ላይ አሉ ከሚባሉ ሰባት የአሜሪካ አየር መንገዶች ካስመዘገቡት 4.9% የትርፍ ህዳግ በእጥፍ የሚበልጥ ነው፡፡ አየር መንገዱ በአንድ መንገደኛ የሚያስገኝው የዶላር መጠንም የአውሮፓ እና የአሜሪካ አየር መንገዶች ከሚያስገኙት የዶላር መጠን የሚበልጥ ነው፡፡ የአየር መንገዳችን ዕዳ ከአየር መንገዱ ጠቅላላ ሀብት በእጅጉ የሚያንስ በመሆኑ አየር መንገዱን ለመሸጥ የሚያስገድድ አይደለም፡፡ አየር መንገዳችን ካለው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባሻገር በኢህአዲግ የተለመደ የሀገር ጥቅምን አሳልፎ የመስጠት ፖለቲካዊ ባህል ምክንያት ወደብ አልባ ለሆነችው ሀገራችን ብቸኛ ወደብ ሆኖ ከመላው ዓለም ጋር የምንገናኝነበት ነጻ በራችን በመሆኑ ለሉዓላዊነታችን እና ብሔራዊ ጥቅማችን መከበር የማይተካ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ የኢህአዴግን ያለፉት አመታት የሙስና እና የሀብት ብክነት የገነገነ ልማድ ልብ ላለ፣ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ሽያጭ የሚገኝውን በቢሊየን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚባክን ከወዲሁ የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ ሽያጩ ጊዚያዊ የዶላር እጥረታችንን ይቀርፋል ቢባል እንኳ ገዥዎቹ ከሚገዟቸው ድርጅቶች የሚያገኙትን ዓመታዊ ትርፍ በየዓመቱ በውጭ ምንዛሬ የሚወስዱ በመሆኑ በመካከለኛ እና በረዥም ጊዜ ውስጥ የዶላር እጥረቱን የበለጠ የሚያባብስ ውሳኔ ነው፡፡
ኢህአዴግ በምርጫ ዋዜማ ላይ በምንገኝበት በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ውሳኔ ቢወስንም ውሳኔውን የሚተችም ሆነ ውሳኔውን ለማስቆም ጥረት የሚያደርግ አንድም የተደራጀ የፖለቲካ ሀይል ባለመኖሩ አደጋውን የመቀልበስ ኃላፊነት በፓርቲያችን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ትከሻ ላይ ወድቋል።

በመሆኑም፦
ሀ) የሚቀጥለው ምርጫ ተደርጎ በህዝብ ፈቃድ እና ይሁንታ የቆመ መንግስት እስኪመሰረት ድረስ ኢህአዴግ የህዝብ ይሁንታን እና ፈቃድ ከሚጠይቁ ስር ነቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ለውጥና ውሳኔዎች እንዲታቀብ እና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ለውጭ የግል ባለሃብቶች ለመሸጥ እና ለማስተላለፍ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲሰርዝ ፓርቲያችን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ለ) ኢህአዴግ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ለውጭ ባለሀብቶች ለመሸጥ ያሳለፈው ውሳኔ፣ መላ ኢትዮጵያውንን በቋንቋ፣ በብሔር እና በሀይማኖት ሳይለይ የሚጎዳ፣ የሁላችንም ቤት የሆነችውን ኢትዮጵያ ለቅርጫ ያቀረበ እና በገዛ ሀገራችን እንደ ሁለተኛ ዜጋ የምንቆጠርበትን ሁኔታ የሚፈጥር ውሳኔ በመሆኑ መላው የሀገራችን ህዝብ ውሳኔውን እንዲያወግዝ እና እንዲቃወመው ፓርቲያችን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ጥሪውን ያስተላለፋል፡፡

ሐ) መንግስት ውሳኔውን እስኪቀለብስ ድረስ ፓርቲያችን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርግ እና ትግላችንን አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን እያስታወቅን፣ በሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመመከት በምናደርገው ትግል መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የትግላችን አጋር እንዲሆን አብን ጥሪውን ያስተላለፋል፡፡

ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ሸዋ